በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ለማይታወቅ አምላክ የተሠራ መሠዊያ

ለማይታወቅ አምላክ የተሠራ መሠዊያ

ለማይታወቅ አምላክ የተሠራ መሠዊያ

ሐዋርያው ጳውሎስ በ50 እዘአ ገደማ በግሪክ የምትገኘውን አቴንስን ጎብኝቶ ነበር። እዚያም ለማይታወቅ አምላክ የተሠራ አንድ መሠዊያ የተመለከተ ሲሆን በኋላም ይሖዋን አስመልክቶ በሰጠው ግሩም ምሥክርነት ላይ ይህን መሠዊያ ጠቅሶ ተናግሯል።

ጳውሎስ የማርስ ኮረብታ ወይም አርዮስፋጎስ ተብሎ በሚጠራው ቦታ ላይ ንግግሩን የከፈተው እንዲህ በማለት ነበር:- “የአቴና ሰዎች ሆይ፣ እናንተ በሁሉ ነገር አማልክትን እጅግ እንደምትፈሩ እመለከታለሁ። የምታመልኩትን እየተመለከትሁ ሳልፍ:- ለማይታወቅ አምላክ የሚል ጽሕፈት ያለበትን መሠዊያ ደግሞ አግኝቼአለሁና። እንግዲህ ይህን ሳታውቁ የምታመልኩትን እኔ እነግራችኋለሁ።”​—⁠ሥራ 17:22-31

ይህ የአቴናውያን መሠዊያ ባይገኝም እንኳን ግሪክ ውስጥ ባሉ ሌሎች ቦታዎች ተመሳሳይ መሠዊያዎች ተገኝተዋል። ለምሳሌ ያህል፣ በሁለተኛው ክፍለ ዘመን የኖረው ግሪካዊው መልክዓ ምድር አጥኚ ፖሳኒየስ ከአቴንስ ብዙም በማይርቀው በፓሌሮን “ለማይታወቁ አማልክት” የተሠሩ መሠዊያዎች መኖ​ራቸውን ጠቅሶ ጽፏል። (Description of Greece, Attica I, 4) በዚሁ ጽሑፍ ላይ በኦሎምፒያም “ለማይታወቁ አማልክት የተሠራ መሠዊያ” ይገኝ እንደነበር ተገልጿል።​—⁠ኢሊያ I, XIV, 8

ግሪካዊው ደራሲ ፊሎስትራተስ (ከ170 ገደማ እስከ 245 ገደማ እዘአ) የትያናው አፖሎኒየስ የሕይወት ታሪክ (VI, III) (እንግሊዝኛ) በተሰኘው የሥነ ጽሑፍ ሥራው ላይ “ለማይታወቁ አማልክት ክብር ሳይቀር መሠዊያዎች ይቆሙ ነበር” ብሏል። ዳያጀኒስ ላሪሺየስ (ከ200 ገደማ እስከ 250 እዘአ) ደግሞ የፈላስፋዎች ሕይወት (1.110) (እንግሊዝኛ) በተባለው መጽሐፉ ላይ “ስም የሌላቸው መሠዊያዎችን” በተለያዩ የአቴንስ ክፍሎች መመልከት የተለመደ እንደሆነ ጽፏል።

ሮማውያንም ለማይታወቁ አማልክት መሠዊያዎችን ይሠሩ ነበር። በሥዕሉ ላይ የሚታየው በመጀመሪያው ወይም በሁለተኛው መቶ ዘመን ከዘአበ የተሠራ መሠዊያ ሲሆን በኢጣሊያ ሮም በፓላታይን አንቲኳሪየም ቤተ መዘክር ውስጥ ተቀምጦ ይገኛል። በላዩ ላይ የተቀረጸው የላቲን ጽሑፍ መሠዊያው “ለተባዕት ወይም ለእንስት አማልክት” የተሠራ እንደሆነ ይጠቁማል። ይህ ሐረግ በተቀረጹ ጽሑፎችና በሥነ ጽሑፍ ሥራዎች ውስጥ ሰፍረው በሚገኙ ጸሎቶች ላይ ብዙውን ጊዜ ይጠቀሳል።

አሁንም ቢሆን ‘ዓለምንና በእርሱ ያለውን ሁሉ የፈጠረው አምላክ’ በብዙዎች ዘንድ አይታወቅም። ይሁን እንጂ ጳውሎስ ለአቴናውያን እንደነገራቸው ይህ አምላክ ማለትም ይሖዋ “ከእያንዳንዳችን የራቀ አይደለም።”​—⁠ሥራ 17:24, 27

[በገጽ 32 ላይ የሚገኝ የሥዕል ምንጭ]

መሠዊያ:- Soprintendenza Archeologica di Roma