ታማኝነትህን ጠብቀህ ትኖር ይሆን?
ታማኝነትህን ጠብቀህ ትኖር ይሆን?
በትናንትናው ዕለት ስንት ድንቢጦች ሞተዋል? ይህንን ሊያውቅ የሚችል ሰው አይኖርም። ምናልባትም ብዙ ወፎች ስላሉ ለጉዳዩ እምብዛም ትኩረት የሚሰጠው የለም። ይሖዋ ግን ያሳስበዋል። እነዚህ ወፎች ብዙም ዋጋ የማይሰጣቸው ሊመስሉ ይችላሉ። ኢየሱስ ግን እነርሱን አስመልክቶ ለደቀ መዛሙርቱ ሲናገር “ከእነርሱም አንዲቱ ያለ አባታችሁ ፈቃድ በምድር ላይ አትወድቅም” ካለ በኋላ “እንግዲህ አትፍሩ፤ ከብዙ ድንቢጦች እናንተ ትበልጣላችሁ” ብሏቸዋል።—ማቴዎስ 10:29, 31
ከጊዜ በኋላ ደቀ መዛሙርቱ ራሳቸው በይሖዋ ዘንድ ምን ያህል ዋጋ እንዳላቸው ተገንዝበው ነበር። ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ የነበረው ሐዋርያው ዮሐንስ እንዲህ በማለት ጽፏል:- “በዚህ የእግዚአብሔር ፍቅር በእኛ ዘንድ ተገለጠ፣ በእርሱ በኩል በሕይወት እንኖር ዘንድ እግዚአብሔር አንድ ልጁን ወደ ዓለም ልኮታልና።” (1 ዮሐንስ 4:9) ይሖዋ የቤዛውን ዝግጅት ከማድረጉም ሌላ ለእያንዳንዱ አገልጋዩ “አልለቅህም ከቶም አልተውህም” የሚል ማረጋገጫ ሰጥቷል።—ዕብራውያን 13:5
ከዚህ በግልጽ ለማየት እንደሚቻለው ይሖዋ ለሕዝቡ ያለው ፍቅር የጸና ነው። አሁን የሚነሳው ጥያቄ ‘እኛስ ከይሖዋ እንዳንርቅ የሚያደርግ የጠበቀ ፍቅር ለእርሱ አለን?’ የሚል ይሆናል።
ታማኝ ሆነን እንዳንገኝ ሰይጣን የሚያደርጋቸው ሙከራዎች
ይሖዋ ስለ ኢዮብ ታማኝነት በጠቀሰለት ጊዜ ሰይጣን “ጥቅም የማያገኝበት ቢሆን ኖሮ አንተን የሚፈራህ ይመስልሃልን?” በማለት መልሷል። (ኢዮብ 1:9 የ1980 ትርጉም ) ይህን ሲል ሰዎች ለአምላክ ታማኝ የሚሆኑት ‘የሆነ ጥቅም ስለሚያገኙ’ ነው ማለቱ ነበር። ይህ አባባሉ እውነት ነው ማለት ማንኛውም ክርስቲያን ልብ የሚያማልል ፈተና ከቀረበለት አቋሙን ያላላል ማለት ነው።
ኢዮብን በተመለከተ ሰይጣን መጀመሪያ ያነሳው ክርክር ውድ ንብረቶቹን ቢያጣ አምላክን ይክዳል የሚል ነበር። (ኢዮብ 1:10, 11) ይህ ነቀፋ ውሸት መሆኑ ሲረጋገጥበት ደግሞ “ሰው ያለውን ሁሉ ስለ ሕይወቱ ይሰጣል” ሲል ተከራከረ። (ኢዮብ 2:4) ይህ የሰይጣን አባባል በአንዳንዶች ላይ ሊሠራ የሚችል ቢሆንም ከታሪኩ እንደምንረዳው ኢዮብ ከአቋሙ ፍንክች አላለም። (ኢዮብ 27:5፤ 42:10-17) አንተስ እንደ ኢዮብ ታማኝ ነህ? ወይስ ሰይጣን አቋምህን እንዲያላላብህ ትፈቅድለታለህ? ከዚህ ቀጥሎ ሁሉንም ክርስቲያኖች የሚመለከቱ አንዳንድ እውነታዎችን ስንመረምር ስለ ራስህ አስብ።
ሐዋርያው ጳውሎስ ክርስቲያኖች የሚያሳዩት እውነተኛ ታማኝነት ጠንካራ እንደሆነ ያምን ነበር። እንዲህ ሲል ጽፏል:- “ሞት ቢሆን፣ ሕይወትም ቢሆን፣ . . . ያለውም ቢሆን፣ የሚመጣውም ቢሆን፣ . . . ልዩ ፍጥረትም ቢሆን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን ካለ ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየን እንዳይችል ተረድቼአለሁ።” (ሮሜ 8:38, 39) ለይሖዋ ያለን ፍቅር ጠንካራ ከሆነ እኛም ተመሳሳይ የሆነ ጽኑ እምነት ሊኖረን ይችላል። እንዲህ ዓይነቱ ፍቅር ሞት እንኳን የማይበጥሰው ጠንካራ ማሰሪያ ነው።
ከአምላክ ጋር ይሄን የመሰለ ዝምድና ካለን ‘ከጥቂት ዓመታት በኋላም ይሖዋን ማምለኬን እቀጥል ይሆን?’ 2 ቆሮንቶስ 4:16-18) ይሖዋን ከልባችን የምንወደው ከሆነ መቼም ቢሆን ከእርሱ አንርቅም።—ማቴዎስ 22:37፤ 1 ቆሮንቶስ 13:8
የሚል ጥያቄ ጨርሶ ወደ አእምሯችን አይመጣም። እንዲህ ዓይነቱ ጥርጣሬ ካለን ለይሖዋ ታማኝ መሆናችን የተመካው በሕይወታችን ሊያጋጥመን በሚችለው ነገር ላይ ነው ማለት ነው። ውጫዊ ተጽዕኖዎች እውነተኛ ታማኝነትን ሊያናጉ አይችሉም። እውነተኛ ታማኝነት በውስጣዊ ማንነታችን ላይ የተመካ ነው። (ይሁን እንጂ ሰይጣን አቋማችንን ለማላላት ዘወትር እንደሚጥር መዘንጋት የለብንም። ለሥጋ ምኞቶች እንድንሸነፍ፣ ለእኩዮች ተጽዕኖ እንድንበረከክ፣ ወይም አንድ እንቅፋት ገጥሞን ከእውነት እንድንወጣ ሊፈትነን ይችላል። ይህንን የሰይጣን ጥቃት ይበልጥ የሚያከብዱት ደግሞ ከአምላክ የራቀው ዓለም እና የራሳችን አለፍጽምናም የሚያሳድሩት ብርቱ ተጽዕኖ ነው። (ሮሜ 7:19, 20፤ 1 ዮሐንስ 2:16) ይሁን እንጂ እኛም በዚህ ውጊያ አሸናፊዎች እንድንሆን የሚረዱን ብዙ ነገሮች አሉ። ከእነዚህም መካከል አንዱና ዋነኛው ሰይጣን የሚጠቀምባቸውን ዘዴዎች ማወቃችን ነው።—2 ቆሮንቶስ 2:11
ሰይጣን የሚጠቀምባቸው ዘዴዎች ምንድን ናቸው? ጳውሎስ ለኤፌሶን ክርስቲያኖች በጻፈው ደብዳቤ ላይ “ሽንገላ” ብሎ ጠርቷቸዋል። (ኤፌሶን 6:11) ሰይጣን ታማኝነታችንን እንድናላላ ለማድረግ መሠሪ ዘዴዎችን ይጠቀማል። ደስ የሚለው ግን ዲያብሎስ የሚጠቀምባቸው ዘዴዎች በአምላክ ቃል ውስጥ ስለተመዘገቡልን ለይተን ልናውቃቸው እንችላለን። ሰይጣን የኢየሱስንና የኢዮብን ታማኝነት ለማላላት ያደረጋቸው ሙከራዎች የእኛንም ክርስቲያናዊ አቋም ለማላላት ምን ዘዴ እንደሚጠቀም እንድናስተውል ይረዱናል።
ኢየሱስ ታማኝነቱን ጠብቋል
ኢየሱስ አገልግሎቱን እንደጀመረ ድንጋዩን ወደ ዳቦ እንዲቀይር በመገዳደር ሰይጣን የአምላክን ልጅ ለመፈተን ተዳፍሮ ነበር። ምንኛ መሠሪ ነው! ኢየሱስ ለ40 ቀናት ምንም ነገር ስላልቀመሰ ተርቦ እንደነበር አያጠራጥርም። (ሉቃስ 4:2, 3) በሌላ አባባል ሰይጣን ያቀረበው ሐሳብ ኢየሱስ የይሖዋን ፈቃድ በሚቃረን መንገድ ተፈጥሯዊ ፍላጎቱን ወዲያውኑ እንዲያረካ የሚጋብዝ ነበር። በተመሳሳይም ዛሬ ያለው ዓለም ‘ድርጊትህ የሚያስከትለው መዘዝ ኖረም አልኖረም ፍላጎትህን ከማርካት ወደኋላ አትበል’ የሚል ፕሮፓጋንዳ ይነዛል።
ኢየሱስ ድርጊቱ የሚያስከትለውን መዘዝ ግምት ውስጥ ሳያስገባ ረሃቡን ወዲያውኑ ቢያስታግስ ኖሮ ሰይጣን የእርሱን ታማኝነት ለማላላት ያደረገው ጥረት ግቡን ይመታ ነበር። ኢየሱስ ግን ነገሮችን ይመለከት የነበረው በመንፈሳዊ ዓይን ስለሆነ “ሰው በእግዚአብሔር ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም ተብሎ ተጽፎአል” የሚል ቁርጥ ያለ መልስ ሰጠው።—ሉቃስ 4:4፤ ማቴዎስ 4:4
ከዚያም ሰይጣን ስልቱን ቀየረ። ኢየሱስ መልስ የሰጠው ከቅዱሳን ጽሑፎች ጠቅሶ ስለነበር ሰይጣንም አንዱን ጥቅስ በተጣመመ መንገድ ተጠቀመና “ይጠብቁህ ዘንድ መላእክቱን ስለ አንተ ያዝልሃል” ብሎ ኢየሱስ ራሱን ከቤተ መቅደሱ ጫፍ ላይ እንዲወረውር ገፋፋው። ኢየሱስ ግን አባቱ እንደሚንከባከበው ለማሳየት ሲል ብቻ ተአምራዊ ጥበቃ እንዲደረግለት መጠየቅ እንዳለበት አልተሰማውም። ስለሆነም “ጌታን አምላክህን አትፈታተነው” ሲል መልስ ሰጥቶታል።—ማቴዎስ 4:5-7፤ ሉቃስ 4:9-12
መጨረሻ ላይ ሰይጣን የተጠቀመበት ዘዴ ቀጥተኛ ማቴዎስ 4:8-11፤ ሉቃስ 4:5-8
ነበር። አንድ ጊዜ ብቻ ወድቆ ቢሰግድለት ዓለምንና ክብሩን እንደሚሰጠው በመግለጽ ለመደራደር ሞከረ። ሰይጣን ለድርድር ያቀረበው ያለውን ሁሉ ነበር ለማለት ይቻላል። ምንስ ቢሆን ኢየሱስ ለአባቱ ቀንደኛ ጠላት እንዴት ሊሰግድ ይችላል? ጨርሶ የማይታሰብ ነበር! ኢየሱስ “ለጌታ ለአምላክህ ስገድ እርሱንም ብቻ አምልክ” በማለት መልሶለታል።—ሰይጣን እነዚህ ሦስት ሙከራዎች ከከሸፉበት በኋላ ‘ሌላ አመቺ ጊዜ እስኪያገኝ ድረስ ከኢየሱስ ተለየ።’ (ሉቃስ 4:13 አ.መ.ት ) ይህ ሰይጣን የኢየሱስን ታማኝነት መፈተን የሚችልበትን አጋጣሚ ከመፈለግ እንደማይቦዝን ያሳያል። ከሁለት ዓመት ተኩል በኋላ ኢየሱስ የሚሞትበት ጊዜ እየተቃረበ ስለነበር ደቀ መዛሙርቱን ከፊታቸው ለሚጠብቃቸው ጊዜ ማዘጋጀት ሲጀምር ሰይጣን አንድ አመቺ አጋጣሚ አግኝቶ ነበር። ሐዋርያው ጴጥሮስ:- “አይሁንብህ ጌታ ሆይ፤ ይህ ከቶ አይደርስብህም” አለው።—ማቴዎስ 16:21, 22
ይህ የተሳሳተ ምክር ከራሱ ደቀ መዝሙር የመጣና በቅንነት የተነገረ መሆኑ የኢየሱስ ልብ እንዲከፈል ያደርግ ይሆን? ኢየሱስ እነዚህ ቃላት የይሖዋን ሳይሆን የሰይጣንን ሐሳቦች እንደሚያንጸባርቁ ለመገንዘብ ጊዜ አልወሰደበትም። “ወደ ኋላዬ ሂድ፣ አንተ ሰይጣን፤ የሰውን እንጂ የእግዚአብሔርን አታስብምና ዕንቅፋት ሆነህብኛል” በማለት ቁርጥ ያለ መልስ ሰጠው።—ማቴዎስ 16:23
ኢየሱስ ለይሖዋ ጽኑ ፍቅር ስለነበረው ሰይጣን አቋሙን እንዲያላላ ሊያደርገው አልቻለም። ሰይጣን የሚያቀርበው የትኛውም ማባበያ ወይም የቱንም ያህል ከባድ የሆነ ፈተና ኢየሱስ ለሰማያዊ አባቱ ያለውን ታማኝነት እንዲያጎድል ሊያደርገው አልቻለም። እኛስ ጽኑ አቋማችንን ጠብቀን እንዳንኖር የሚያደርጉ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙን ተመሳሳይ የሆነ ቁርጠኝነት እናሳያለን? ምን ዓይነት ፈተናዎች ሊገጥሙን እንደሚችሉ ከኢዮብ ምሳሌ መማር እንችላለን።
መከራን ተቋቁሞ ታማኝ መሆን
በኢዮብ ላይ እንደደረሰው ሁሉ እኛም በማንኛውም ጊዜ መከራ ሊያጋጥመን ይችላል። ኢዮብ የአሥር ልጆች አባትና በትዳሩ የሚደሰት መንፈሳዊ ሰው ነበር። (ኢዮብ 1:5) ይሁን እንጂ ኢዮብ ስለ ጉዳዩ ባያውቅም ለአምላክ የነበረው ታማኝነት በሰማያዊው ችሎት ፊት የመከራከሪያ አጀንዳ ሆኖ ተነስቶ ነበር። ከዚያም ሰይጣን የሚችለውን ሁሉ አድርጎ የኢዮብን ታማኝነት ለማላላት ታጥቆ ተነሳ።
ኢዮብ በአንድ ጀንበር ሃብቱን ሁሉ አጣ። (ኢዮብ 1:14-17) ሆኖም እምነቱን የጣለው በገንዘብ ላይ ስላልነበረ ፈተናውን ተቋቁሞ አለፈ። ኢዮብ ባለጠጋ የነበረበትን ጊዜ አስመልክቶ ሲናገር እንዲህ ብሎ ነበር:- “ወርቅን ተስፋ አድርጌ . . . ፤ ሀብቴ ስለ በዛ . . . ደስ ብሎኝ እንደ ሆነ፤ ልዑል እግዚአብሔርን በካድሁ ነበርና ይህ ደግሞ . . . በደል በሆነ ነበር።”—ኢዮብ 31:24, 25, 28
በዛሬው ጊዜም ሃብታችንን በሙሉ በአንድ ጊዜ ልናጣ እንችላለን። በንግድ ሥራ ይተዳደር የነበረ አንድ የይሖዋ ምሥክር በጣም ብዙ ገንዘብ ተጭበረበረና ለኪሳራ ተዳረገ። የተሰማውን ስሜት እንደሚከተለው በማለት ሳይሸሽግ ተናግሯል:- “በድንጋጤ ልቤ ቀጥ ሊል ነበር። ደግሞም ከአምላክ ጋር ጥሩ ዝምድና ባይኖረኝ ኖሮ ልቤ ቀጥ ማለቱ አይቀርም ነበር። የሆነ ሆኖ ይህ ገጠመኝ በሕይወቴ ውስጥ ለመንፈሳዊ ነገሮች ቅድሚያ እየሰጠሁ እንዳልነበረ እንዳስተውል አድርጎኛል። ገንዘብ ማግኘት የሚፈጥረው ደስታ ከምንም ነገር በልጦብኝ ነበር።” ይህ ወንድም ከዚያ በኋላ ለንግድ ሥራው ገደብ በማበጀት በክርስቲያናዊ አገልግሎት በወር 50 ወይም ከዚያ በላይ ሰዓት በማሳለፍ በቋሚነት ረዳት አቅኚ ሆኖ ያገለግላል። ይሁን እንጂ ሀብትን ከማጣት ይበልጥ የከፉ ሌሎች ችግሮችም አሉ።
ኢዮብ አሥር ልጆቹ የመሞታቸው መርዶ የተነገረው ሃብቱን ማጣቱ ካስከተለበት ድንጋጤ በቅጡ እንኳን ሳያገግም ነበር። ቢሆንም:- “የእግዚአብሔር ስም የተባረከ ይሁን” በማለት ተናግሯል። (ኢዮብ 1:18-21) ከቤተሰባችን አባላት ውስጥ በርከት ያሉትን በሞት ብናጣ ታማኝነታችንን ጠብቀን እንኖር ይሆን? በስፔይን የሚኖር ፍራንሲስኮ የተባለ አንድ ክርስቲያን የበላይ ተመልካች ሁለት ልጆቹን በአውቶቡስ አደጋ ባጣበት ወቅት መጽናናት የቻለው ወደ ይሖዋ ይበልጥ በመቅረብና በክርስቲያናዊ አገልግሎት የሚያደርገውን ተሳትፎ በመጨመር ነበር።
ኢዮብ ልጆቹ በአሰቃቂ ሁኔታ ከሞቱበት በኋላም ቢሆን መከራው ገና አላበቃም ነበር። ሰይጣን አስከፊ በሆነ የሚያሰቃይ በሽታ መታው። በዚያው ወቅት ሚስቱ ‘እግዚአብሔርን ስደብና ሙት’ በማለት መጥፎ ምክር ኢዮብ 2:9, 10) በታማኝነት መጽናቱ የተመካው ከይሖዋ ጋር ባለው የግል ዝምድና ላይ እንጂ ከቤተሰቡ በሚያገኘው ስሜታዊ ድጋፍ አልነበረም።
መከረችው። ኢዮብ ምክሯን አልሰማም፤ ‘በከንፈሩም አልበደለም።’ (ከአሥር ዓመታት በፊት ባሏና ትልቁ ልጅዋ እውነትን ሲተዉ የተመለከተችው ፍሎራ ኢዮብ ምን ዓይነት ስሜት ተሰምቶት ሊሆን እንደሚችል ይገባታል። “የቤተሰባችሁን ድጋፍ በድንገት ማጣት የስሜት መቃወስ ሊያስከትልባችሁ ይችላል።” በማለት ትናገራለች። “ቢሆንም ከይሖዋ ድርጅት ውጪ ደስተኛ ሆኜ መኖር እንደማልችል አውቅ ነበር። ስለዚህ ጥሩ ሚስትና እናት ለመሆን የማደርገውን ጥረት ሳላቋርጥ ለይሖዋ ቀዳሚውን ቦታ በመስጠት ጸናሁ። አዘውትሬ እጸልይ ስለነበረ ይሖዋ ብርታት ሰጥቶኛል። ባለቤቴ በተቃውሞው ቢገፋበትም ሙሉ በሙሉ በይሖዋ መታመንን ስለተማርኩ ደስተኛ ነኝ።”
ቀጥሎ ሰይጣን የኢዮብን ጽኑ አቋም ለማላላት መሣሪያ አድርጎ የተጠቀመው ሦስቱን ወዳጆቹን ነበር። (ኢዮብ 2:11-13) እነዚህ ወዳጆቹ ሊተቹት ሲጀምሩ ኢዮብ ምንኛ አዝኖ ይሆን? ንዝነዛቸውን ሰምቶ ቢሆን ኖሮ በይሖዋ አምላክ ላይ የነበረውን ትምክህት ሊያጣ ይችል ነበር። ተስፋ አስቆራጭ የሆነው ምክራቸው ነገር ዓለሙን እንዲተወውና አቋሙን እንዲያላላ ሊያደርገው ስለሚችል የሰይጣን መሠሪ እቅድ ግቡን ይመታ ነበር።
ኢዮብ ግን ‘እስክሞት ድረስ ታማኝነቴን ከእኔ አላርቅም’ በማለት ተናግሯል። (ኢዮብ 27:5) ኢዮብ ‘ታማኝነቴን እንድታላሉብኝ አልፈቅድላችሁም!’ እንዳላለ ልብ በል። ታማኝ መሆኑ የተመካው በራሱና ለይሖዋ ባለው ፍቅር ላይ እንደሆነ ያውቅ ነበር።
ሰይጣን የጥንቱን ዘዴ ዛሬም ይጠቀማል
ሰይጣን አሁንም ከጓደኞችና ከእምነት አጋሮቻችን የሚሰነዘሩ የተሳሳቱ ምክሮችን ወይም በግዴለሽነት የሚሰጡ አስተያየቶችን እንደ መሣሪያ አድርጎ ይጠቀማል። ከውጭ ከሚመጣ ስደት ይልቅ ከጉባኤ አባላት የሚሰነዘር ተስፋ አስቆራጭ አስተያየት ውስጣዊ ጥንካሬያችንን በቀላሉ ሊያዳክምብን ይችላል። ቀደም ሲል ወታደር ስለነበር በውጊያ ተካፍሎ የሚያውቅ አንድ ክርስቲያን ሽማግሌ ጦርነትን አንዳንድ ክርስቲያን ወንድሞቹ በግዴለሽነት ንግግራቸው ወይም ድርጊታቸው ከሚያደርሱበት ስቃይ ጋር አወዳድሮታል። ክርስቲያን ወንድሞቹ በንግግራቸው ወይም በድርጊታቸው የሚያደርሱበትን ሥቃይ አስመልክቶ ሲናገር “በሕይወቴ ካጋጠሙኝ ነገሮች ሁሉ ይበልጥ ከባድ ነው” ብሏል።
ጉዳዩን ከሌላ አቅጣጫ ከተመለከትነው ደግሞ አንዳንድ ጊዜ የእምነት አጋሮቻችን በሠሩት ስሕተት ልንበሳጭና አንዳንዶቹን ማነጋገር ልንተው አልፎ ተርፎም ከክርስቲያናዊ ስብሰባዎች ልንቀር እንችላለን። በዚህ ጊዜ ለእኛ እንደ ዋና ነገር ሆኖ የሚታየን የተጎዳውን ስሜታችንን ማስታመም ሊሆን ይችላል። ይሁን እንጂ ከፊታችን ያለውን ነገር ብቻ በማየት በሌሎች ንግግር ወይም ድርጊት ተጎድተናል ብለን ከይሖዋ ጋር ያለን ውድ ዝምድና እንዲዳከም መፍቀዳችን ምንኛ የሚያሳዝን ይሆናል። ይህ እንዲሆን ከፈቀድን ሰይጣን ከጥንት ጀምሮ ሲጠቀምበት ለኖረው የማታለያ ወጥመድ እንሸነፋለን።
በክርስቲያን ጉባኤ ውስጥ የላቁ የሥነ ምግባር ደረጃዎች ሊኖሩ ይገባል ብለን መጠበቃችን የተገባ ነው። ሆኖም ፍጽምና ከሌላቸው የእምነት አጋሮቻችን ብዙ የምንጠብቅ ከሆነ ነገሮች እንዳሰብናቸው ሳይሆኑ ሲቀሩ ልናዝን እንችላለን። በተቃራኒው ይሖዋ ከአገልጋዮቹ የሚጠብቀው ምክንያታዊ ነገር ነው። እኛም የእሱን አስተሳሰብ የምንኮርጅ ከሆነ ወንድሞቻችን ባለፍጽምና ምክንያት የሚፈጽሙትን ስህተት ችለን ማለፍ አይከብደንም። (ኤፌሶን 4:2, 32) ሐዋርያው ጳውሎስ የሚከተለውን ምክር ሰጥቷል:- “ተቈጡ ቁጣችሁ ኃጢአትን ወደ ማድረግ እንዲመራችሁ አትፍቀዱለት፤ ተቆጥታችሁ እንዳለ ፀሐይ እንዳትጠልቅባችሁ፣ ለዲያብሎስም መግቢያ ቀዳዳ አትስጡት።”—ኤፌሶን 4:26, 27 ዘ ኒው ኢንግሊሽ ባይብል
መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ እንደሚያሳየው ሰይጣን አንድ ክርስቲያን ታማኝነቱን እንዲያላላ ማድረግ የሚችልበትን መንገድ ለማግኘት የተለያዩ መሠሪ ዘዴዎችን ይጠቀማል። አንዳንዶቹ ወጥመዶች ፍጹም ላልሆነው ሥጋችን የሚያጓጉ ሆነው ሲታዩ ሌሎቹ ደግሞ ስቃይ የሚያስከትሉ ናቸው። ፈጽሞ መዘናጋት የሌለብህ ለምን እንደሆነ እስካሁን ካነሳናቸው ነጥቦች መረዳት ትችላለህ። ለአምላክ ልባዊ ፍቅር በማዳበር የዲያብሎስን ሐሰተኝነት ለማረጋገጥና የይሖዋን ልብ ደስ ለማሰኘት ቁርጥ ውሳኔ አድርግ። (ምሳሌ 27:11፤ ዮሐንስ 8:44) ምንም ዓይነት መከራ ቢደርስብን በእውነተኛ ክርስቲያናዊ ታማኝነታችን መጽናት እንዳለብን አስታውስ።