በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ታስታውሳለህን?

ታስታውሳለህን?

ታስታውሳለህን?

በቅርቡ የወጡትን የመጠበቂያ ግንብ እትሞች አንብበሃልን? እስቲ የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር:-

•  የሌላውን ችግር እንደ ራስ መመልከት ሲባል ምን ማለት ነው? ክርስቲያኖችስ ይህንን ባህርይ ማዳበር የሚገባቸው ለምንድን ነው?

የሌላውን ችግር እንደ ራስ መመልከት ሲባል ራስን በሌላው ቦታ ማስቀመጥ ማለት ሲሆን ይህም የሌላው ሰው ሥቃይ በልባችን ጠልቆ እንዲሰማን ማድረግን ይጨምራል። ክርስቲያኖች “የሌላው መከራ ለእናንተ እንደሚሆን አድርጉ፣ እንደ ወንድሞች ተዋደዱ፣ ርኅሩኆች . . . ሁኑ” ተብለው ተመክረዋል። (1 ጴጥሮስ 3:8) የሌላውን ችግር በመረዳት ረገድ ይሖዋ ልንኮርጀው የምንችለው ምሳሌ ትቶልናል። (መዝሙር 103:14፤ ዘካርያስ 2:8) በማዳመጥ፣ አስተውለን በመመልከትና ራሳችንን በሌሎች ቦታ በማስቀመጥ የሌሎችን ችግር የመረዳት ችሎታችንን ይበልጥ ማዳበር እንችላለን።​—4/15 ገጽ 24-6

•  እውነተኛ ደስታ ለማግኘት መንፈሳዊ ፈውስ ከአካላዊ ፈውስ መቅደም ያለበት ለምንድን ነው?

አካላዊ ጤንነት ያላቸው አብዛኞቹ ሰዎች ደስተኞች አይደሉም፤ ሕይወታቸውም በችግር የተሞላ ነው። ከዚህ በተቃራኒ በአሁኑ ጊዜ የአካል ጉዳተኞች የሆኑ በርካታ ክርስቲያኖች ደስተኛ ሆነው ይሖዋን ያገለግላሉ። ከመንፈሳዊው ፈውስ እየተጠቀሙ ያሉ ሰዎች በአዲሱ ዓለም ከአካል ጉዳተኝነት ነፃ ይሆናሉ።​—5/1 ገጽ 6-7

በዕብራውያን 12:​16 ላይ ኤሳው ከሴሰኞች ጋር የተመደበው ለምንድን ነው?

የመጽሐፍ ቅዱስ ዘገባ እንደሚገልጸው ኤሳው ፍላጎቱን ለማርካት በመጣደፍ ቅዱስ ነገሮችን የማቃለል ዝንባሌ አሳይቷል። ዛሬም አንድ ሰው የዚህ ዓይነት ዝንባሌ ካዳበረ እንደ ዝሙት ያለ ከባድ ኃጢአት ወደ መፈጸም ሊመራው ይችላል።​—5/1 ገጽ 10-11

ተርቱሊያን ማን ነበር? ተለይቶ የሚታወቀውስ በምንድን ነው?

ተርቱሊያን በሁለተኛውና በሦስተኛው መቶ ዘመን እዘአ ይኖር የነበረ ጸሐፊና የሃይማኖት ምሁር ነው። በሰፊው የሚታወቀው ለስመ ክርስትና ለመሟገት በተዘጋጁት በርካታ የጽሑፍ ሥራዎቹ ነው። ለክርስትና ይሟገት በነበረበት ወቅት ያቀረባቸው ሐሳቦችና ፍልስፍናዎች እንደ ሥላሴ ላሉ የተበረዙ መሠረተ ትምህርቶች በር ከፍተዋል።​—5/15 ገጽ 29-​31

ለሰው ልጅ በሽታ፣ ባሕርይና ሞት ጅኖች ሙሉ በሙሉ ተጠያቂ የማይሆኑት ለምንድን ነው?

ሳይንቲስቶች ለተለያዩ የሰው ልጅ በሽታዎች መንስኤው ጅኖች መሆን አለባቸው ብለው ደምድመዋል፤ አንዳንዶችም ባሕርያችን የሚወሰነው በጅናችን እንደሆነ ያምናሉ። ይሁን እንጂ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ሰው ልጅ አፈጣጠር እንዲሁም የሰው ልጅ ወደ ኃጢአትና አለፍጽምና እንዴት እንደወደቀ ይናገራል። ባሕርያችንን በመቅረጽ ረገድ ጅኖች የሚጫወቱት ሚና ቢኖርም ፍጹማን አለመሆናችንና አካባቢያችንም ከፍተኛ ተጽዕኖ ያሳድራሉ።​—6/1 ገጽ 9-​11

በኦክሲሪንኩስ ግብጽ የተገኘ የፓፒረስ ቁራጭ በአምላክ ስም አጠቃቀም ላይ ብርሃን የፈነጠቀው እንዴት ነው?

በግሪክኛው ሴፕቱጀንት ትርጉም ውስጥ የሚገኘውን የኢዮብ 42:​11, 12 ጥቅስ በያዘው በዚህ ቁራጭ ውስጥ ቴትራግራማተን (የአምላክን ስም የሚወክሉት አራት የዕብራይስጥ ፊደላት) ይገኛሉ። ይህም የክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን ጽሑፎችን የጻፉት ሰዎች አብዛኛውን ጊዜ ይጠቅሱት በነበረው የሴፕቱጀንት ትርጉም ውስጥ የአምላክ ስም በዕብራይስጥ ይገኝ እንደነበረ የሚያሳይ ተጨማሪ ማስረጃ ነው።​—6/1 ገጽ 30

በሮማ ግዛት ይከናወኑ የነበሩት ዓመፅ የሞላባቸውና በነፍስ ግድያ የታወቁ የግላዲያተር ትዕይንቶች በዘመናዊው ስፖርት ከሚታየው ከየትኛው ሁኔታ ጋር ተነጻጽረዋል?

በቅርቡ በኢጣሊያ ሮም በሚገኝ አንድ ጥንታዊ አምፊቲያትር ውስጥ በቀረበ ኤግዚቢሽን ላይ የኮርማ ትግል፣ ፕሮፌሽናል የቦክስ ውድድር፣ የመኪናና የሞተር ብስክሌት ውድድሮች እንዲሁም በሌሎች ዘመናዊ የስፖርት ውድድሮች ላይ በተመልካቾች መካከል የሚደረጉ ድብድቦችን የሚያሳዩ የቪድዮ ፊልሞች መቅረባቸው እነዚህ ዘመናዊ ስፖርቶች ከጥንቶቹ ፍልሚያዎች ጋር ተመሳሳይነት እንዳላቸው የሚያመለክት ነው። የጥንት ክርስቲያኖች ይሖዋ ዓመፅንም ሆነ ዓመፀኞችን እንደማይወድ ተገንዝበው ነበር፤ ዛሬ ያሉ ክርስቲያኖችም ዓመፅን መውደድ የለባቸውም። (መዝሙር 11:5)​—6/15 ገጽ 29

•  ውጤታማ አስተማሪዎች ለመሆን ስንጥር ከዕዝራ ምሳሌ ምን ልንማር እንችላለን?

ዕዝራ 7:​10 ላይ ዕዝራ የወሰዳቸው አራት እርምጃዎች የተዘረዘሩ ሲሆን እነዚህን እርምጃዎች እኛም ልንኮርጃቸው እንችላለን። ጥቅሱ እንዲህ ይላል:- ‘ዕዝራም [1] የእግዚአብሔርን ሕግ ይፈልግና [2] ያደርግ ዘንድ፣ [3] ለእስራኤልም ሥርዓትንና ፍርድን ያስተምር ዘንድ [4] ልቡን አዘጋጅቶ ነበር።’​—7/1 ገጽ 20

አንዲት ክርስቲያን ሴት ራስዋን መሸፈን የሚገባት በየትኞቹ ሁለት አጋጣሚዎች ነው?

አንደኛው አጋጣሚ ሊፈጠር የሚችለው በቤተሰብ ውስጥ ነው። የራስ መሸፈኛ ማድረግዋ ቤተሰቡን በመወከል መጸለይና መጽሐፍ ቅዱሳዊ መመሪያዎች መስጠት የባልዋ ኃላፊነት መሆኑን እንደምትገነዘብ ያሳያል። ሌላው አጋጣሚ ሊፈጠር የሚችለው ደግሞ ከጉባኤ እንቅስቃሴዎች ጋር በተያያዘ ሲሆን ይህም የተጠመቁ ወንዶች የማስተማርና የመምራት ቅዱስ ጽሑፋዊ ሥልጣን እንዳላቸው እንደምትገነዘብ ያሳያል። (1 ቆሮንቶስ 11:3-10)​—7/15 ገጽ 26-7

ክርስቲያኖች ዮጋ ከተራ የሰውነት ማጎልመሻ እንቅስቃሴ ያለፈ አደገኛ ነገር እንደሆነ አድርገው የሚመለከቱት ለምንድን ነው?

ዮጋ የሚሠራበት ዓላማ አንድን ግለሰብ ራሱን በመግራት ከሰው በላይ ኃይል ካለው መንፈስ ጋር እንዲጣመር ማድረግ ነው። ከአምላክ መመሪያ ጋር በሚጻረር መልኩ ዮጋ አእምሮ ማሰብ እንዲያቆም ማድረግን ይጠይቃል። (ሮሜ 12:1, 2) ዮጋ አደገኛ ለሆኑት መናፍስታዊና የአስማት ድርጊቶች ሊያጋልጥ ይችላል። (ዘዳግም 18:10, 11)​—8/1 ገጽ 20-2