በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ቸልተኛ መሆን ይኖርብሃልን?

ቸልተኛ መሆን ይኖርብሃልን?

ቸልተኛ መሆን ይኖርብሃልን?

ብዙ ሰዎች ዘና ያለ፣ የተረጋጋና ሆደ ሰፊ ሰው የሚደነቅ ባሕርይ እንዳለው ያስቡ ይሆናል። ይሁን እንጂ ይህ ባሕርይ ወደ ቸልተኝነትም ሊመራ ይችላል። መጽሐፍ ቅዱስ “ሰነፎችንም ቸልተኛ መሆን ያጠፋቸዋል” ይላል። (ምሳሌ 1:32) ይህ ምን ማለት ነው?

አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች በመጀመሪያው የዕብራይስጥ ጽሑፍ ላይ የተጠቀሰውን ቃል “ግዴለሽነት” (አሜሪካን ስታንዳርድ ቨርሽን ) እና “ግብዝነት” (ዘ ኒው አሜሪካን ባይብል ) በማለት ተርጉመውታል። ከዚህ አንጻር ስንመለከተው ቸልተኝነት ከስንፍናና ከግዴለሽነት ብሎም ከቂልነት ወይም ከሞኝነት ጋር ዝምድና አለው።

በመጀመሪያው መቶ ዘመን በሎዶቅያ ጉባኤ የነበሩት ክርስቲያኖች በቸልተኝነት መንፈሳዊ ድክመታቸውን ሳያስተውሉ ቀርተዋል፤ ወይም ምንም እንዳልጎደላቸው ያስቡ ነበር። በግብዝነት “አንድም ስንኳ አያስፈልገኝም” ብለው ነበር። ኢየሱስ ክርስቶስ ክርስቲያናዊ ቅንዓታቸውን እንደገና እንዲያቀጣጥሉት በማሳሰብ እርማት ሰጥቷቸዋል።​—⁠ራእይ 3:14-19

በኖህ ዘመን የነበሩት ሰዎችም ቸልተኞች ነበሩ። እንደ ‘መብላትና መጠጣት እንዲሁም እንደ ማግባትና መጋባት’ ባሉት የተለመዱ የሕይወት ጉዳዮች ተጠምደው ስለነበር ‘የጥፋት ውኃ መጥቶ ሁሉን እስከ ወሰደ ድረስ አላወቁም።’ ኢየሱስ አክሎም “የሰው ልጅ መምጣት [በሥልጣኑ ላይ በሚገኝበት ጊዜ] ደግሞ እንዲሁ ይሆናል” ብሏል።​—⁠ማቴዎስ 24:37-39

ፍጻሜያቸውን ያገኙ የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶች እንደሚያሳዩት የምንኖረው ‘የሰው ልጅ ማለትም ኢየሱስ ክርስቶስ በሥልጣኑ ላይ በተገኘበት’ ጊዜ ላይ ነው። ግዴለሾች፣ ግብዞች ወይም በሌላ አባባል ቸልተኞች እንዳንሆን እንጠንቀቅ።​—⁠ሉቃስ 21:29-36