በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

“እውነትሽን ነው፣ ሕይወት አስደሳች ነው!”

“እውነትሽን ነው፣ ሕይወት አስደሳች ነው!”

“እውነትሽን ነው፣ ሕይወት አስደሳች ነው!”

የሕይወትን እውነተኛ ትርጉም ለማወቅ ትፈልጋለህ? በሺቼቺን፣ ፖላንድ የምትኖር ማግዳሌና የተባለች የ18 ዓመት ወጣት የይሖዋ ምሥክር በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አብራት የምትማረውን ካታርዜናን የሕይወትን ትርጉም እንድታውቅ ረድታታለች። ካታርዜና በአምላክ መኖር የማታምን ብትሆንም ማግዳሌና ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ስታነጋግራት የማወቅ ፍላጎት አደረባት።

ማግዳሌና ከመጽሐፍ ቅዱስ የነገረቻት ሐሳብ ካታርዜናን ቢያስደስታትም ሙሉ በሙሉ መቀበል ግን አልፈለገችም። በአንድ ወቅት ከማግዳሌና ጋር ስለ እውነተኛ ጓደኞች ሲወያዩ ካታርዜና እንዲህ ብላ ነበር:- “አንቺ በመጽሐፍ ቅዱስ ስለምታምኚ የትኞቹን መመሪያዎች መከተል እንዳለብሽና ጥሩ ጓደኞችን የት እንደምታገኚ ታውቂያለሽ። ይሁን እንጂ ለጊዜውም ቢሆን እነዚህን መመሪያዎች የማያምኑ ሰዎችስ?”

ካታርዜና ወደ ለንደን፣ እንግሊዝ በሄደችበት ወቅት ሐሳቧን የሚያስቀይራት አንድ አጋጣሚ ተፈጠረ። በዚያ የሚገኘውን የይሖዋ ምሥክሮች ቅርንጫፍ ቢሮ ስትጎበኝ በተደረገላት ደግነት በጣም ተደነቀች። በር እንደመክፈትና የምትናገረውን በጥሞና እንደማዳመጥ ያሉት ቀላል ነገሮች ትኩረቷን ሳቡት።

በመስከረም 2001 ትምህርት ቤት ሲከፈት ካታርዜና ጓደኛዋ መጽሐፍ ቅዱስን እንድታስጠናት ተስማማች። ለመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓቶች ያላት አድናቆት እያደገ ሲሆን ምክሮቹንም በዕለታዊ ሕይወቷ ተግባራዊ ማድረግ ጀምራለች። በቅርቡ ለማግዳሌና “ዳግም የተወለድኩ ሆኖ ተሰማኝ” በማለት ስሜትዋን ገልጻላታለች። እንዲሁም መልእክት መቀበያ ባለው ስልክ አማካኝነት እንደዚህ የሚል መልእክት ተወችላት:- “ለዛሬው ጥናታችን በጣም አመሰግንሻለሁ! እውነትሽን ነው፣ ሕይወት አስደሳች ነው! ለሕይወት ስጦታ ሊመሰገን የሚገባው ማን እንደሆነ ማወቁም ያስደስታል።”