በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

አምላክን ለማስደሰት ቅንነት ብቻ በቂ ነው?

አምላክን ለማስደሰት ቅንነት ብቻ በቂ ነው?

አምላክን ለማስደሰት ቅንነት ብቻ በቂ ነው?

በዕለት ተዕለት ሕይወታችን ቅንነት ማሳየት በእርግጥ አስፈላጊ ነውን? አንድ መዝገበ ቃላት “ቅንነት” የሚለውን ቃል “ማስመሰል ወይም ግብዝነት የሌለበት፤ ሐቀኝነት፣ ግልጽነት፣ ሐሳበ ቀናነት” በማለት ተርጉሞታል። ይህ ባሕርይ ከሌሎች ጋር ያለንን ጥሩ ዝምድና በማጠናከር ረገድ ጠቃሚ መሆኑ ግልጽ ነው። ሐዋርያው ጳውሎስ “በቅን ልብ ጌታን እየፈራችሁ እንጂ፣ ለሰው ደስ እንደምታሰኙ ለታይታ የምትገዙ ሳትሆኑ፣ በሥጋ ጌቶቻችሁ ለሆኑ በሁሉ ታዘዙ” የሚል ምክር ሰጥቷል። (ቆላስይስ 3:22) እንዲህ ዓይነት ቅን ሠራተኛ ቢያገኝ የማይደሰት ማን አለ? በዛሬው ጊዜ ቅን የሆኑ ሰዎች ሥራ ለማግኘትም ሆነ በሥራቸው ላይ ለረጅም ጊዜ ለመቆየት ከሌሎች የተሻለ እድል አላቸው።

ቅንነትን በጣም ተፈላጊ ባሕርይ የሚያደርገው ግን ከአምላክ ጋር ያለንን ዝምድና የሚነካ መሆኑ ነው። የጥንት እስራኤላውያን ሕጉንና በዓላትን በጥንቃቄ ሲያከብሩ የአምላክን በረከት ያገኙ ነበር። ጳውሎስ የጉባኤውን ንጽሕና በሚመለከት ክርስቲያኖችን “በቅንነትና በእውነት ቂጣ በዓልን እናድርግ እንጂ በአሮጌ እርሾ በክፋትና በግፍ እርሾም አይደለም” በማለት አጥብቆ አሳስቧቸዋል። (1 ቆሮንቶስ 5:8) አምልኮታችን በአምላክ ዘንድ ተቀባይነት እንዲያገኝ ቅንነት የግድ አስፈላጊ ነው። ሆኖም ቅንነት ብቻውን እንደማይበቃ ልብ በል። በእውነት ላይ የተመሠረተ መሆን አለበት።

ታይታኒክ የተባለችውን መርከብ የሠሩት ሰዎችም ሆኑ ተሳፋሪዎቿ መርከቧ ፈጽሞ እንደማትሰጥም በቅንነት አምነው ሊሆን ይችላል። ይሁን እንጂ በ1912 የመጀመሪያ ጉዞዋን ስታደርግ ከበረዶ ዓለት ጋር ተጋጨችና 1, 517 የሚያህሉ ሰዎች ሕይወታቸውን አጡ። በመጀመሪያው መቶ ዘመን የነበሩ አንዳንድ አይሁዳውያንም አምላክን የሚያመልኩበት መንገድ ትክክል እንደሆነ በቅንነት ተሰምቷቸው ሊሆን ይችላል፤ ሆኖም ቅንዓታቸው “በትክክለኛ እውቀት” ላይ የተመሠረተ አልነበረም። (ሮሜ 10:2 የ1980 ትርጉም) እኛም በአምላክ ዘንድ ተቀባይነት ለማግኘት በቅንነት የምናምንባቸው ትምህርቶች በትክክለኛ መረጃ ላይ የተመሠረቱ መሆን አለባቸው። በአካባቢዎ ያሉት የይሖዋ ምሥክሮች አምላክን በቅንነትና በእውነት ማምለክ ሲባል ምን ማለት እንደሆነ እንዲያውቁ ለመርዳት ፈቃደኛ ናቸው።