በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የመንግሥቱን መልእክት “እየሰሙ” ነው

የመንግሥቱን መልእክት “እየሰሙ” ነው

የመንግሥቱ አዋጅ ነጋሪዎች ሪፖርት

የመንግሥቱን መልእክት “እየሰሙ” ነው

በብራዚል ያሉ የይሖዋ ምሥክሮች በአገሪቱ ውስጥ ላሉት መስማት የተሳናቸው ሰዎች የመንግሥቱን ምሥራች ለማወጅ አስቸጋሪ የሆነውን የብራዚል የምልክት ቋንቋ ለመማር ከፍተኛ ጥረት አድርገዋል። የሚቀጥሉት ተሞክሮዎች እንደሚያሳዩት ጥረታቸው ግሩም ውጤቶች እያስገኘ ነው።

በሳኦ ፓውሎ የምትኖር ኤቫ a የተባለች አንዲት መስማት የተሳናት ሴት የምልክት ቋንቋ መማር የጀመረችው ሦስት ልጆቿን ይዛ ከአንድ መስማት ከተሳነው ሰው ጋር መኖር ከጀመረች በኋላ ነበር። ኤቫና ይህ የወንድ ጓደኛዋ በአንድ የገበያ ማዕከል ውስጥ መስማት ከተሳናቸው የይሖዋ ምሥክሮች ጋር ሲገናኙ ምሥክሮቹ በመንግሥት አዳራሽ ውስጥ በሚደረገው ስብሰባ ላይ እንዲገኙ ጋበዟቸው። ስብሰባው ሰዎች አንድ ላይ ተሰባስበው የሚጫወቱበት ግብዣ ይሆናል ብለው በማሰብ ግብዣውን ተቀበሉ።

ኤቫ የምልክት ቋንቋ እውቀቷ ውስን ስለነበር በስብሰባው ላይ ከተነገረው ውስጥ የተረዳችው በጣም ጥቂቱን ነበር። ከስብሰባው በኋላ አንድ ሁለት ምሥክሮች ቤታቸው መጥታ ሻይ ቡና እየጠጡ እንዲጫወቱ ጋበዟት። በምድር ላይ ለዘላለም በደስታ ኑር! በተባለው ብሮሹር ላይ ያሉትን ስዕሎች በመጠቀም አምላክ ወደፊት ምድርን ገነት ለማድረግ ስላለው ዓላማ ነገሯት። ኤቫ በተማረችው ነገር ስለተደሰተች አዘውትራ በስብሰባዎች ላይ መገኘት ጀመረች።

ከዚያ ብዙም ሳይቆይ ኤቫ ከመጽሐፍ ቅዱስ የሥነ ምግባር ደረጃዎች ጋር ተስማምታ ለመኖር ስትል ከወንድ ጓደኛዋ ጋር አንድ ላይ መኖሯን አቆመች። ከቤተሰቦቿ ከባድ ተቃውሞ ቢገጥማትም መንፈሳዊ እድገት በማድረግ በ1995 ተጠመቀች። ከስድስት ወራት በኋላ አቅኚ ማለትም የሙሉ ጊዜ የመንግሥቱ አዋጅ ነጋሪ የሆነች ሲሆን እስካሁን ድረስ አራት መስማት የተሳናቸው ሰዎች ራሳቸውን ለይሖዋ ወስነው እንዲጠመቁ ረድታለች።

ካርሎስ ሲወለድም መስማት የተሳነው ነበር። ከልጅነቱ ጀምሮ ዕፅ በመውሰድ፣ በጾታ ብልግናና በስርቆት የታወቀ ነበር። ሌሎች ዱርዬዎች የሰነዘሩበትን ዛቻ ፈርቶ ወደ ሳኦ ፓውሎ ሸሸና በዚያ ለተወሰነ ጊዜ ዠዋው ከተባለ ሰው ጋር ተዳብሎ መኖር ጀመረ። ዠዋውም እንደ ካርሎስ መስማት የተሳነው ሲሆን አኗኗሩም ሥነ ምግባር የጎደለው ነበር።

ከጥቂት ዓመታት በኋላ ካርሎስ የመንግሥቱን መልእክት ሰማና ሕይወቱን በመጽሐፍ ቅዱስ የሥነ ምግባር መመሪያዎች መሠረት አስተካከለ፤ እንዲሁም ትዳሩን ሕጋዊ አደረገ። ካርሎስ ቅዱስ ጽሑፋዊ ብቃቶችን ካሟላ በኋላ ራሱን ለይሖዋ መወሰኑን በውኃ በመጠመቅ አሳየ። ይህ በእንዲህ እንዳለ ካርሎስ ሳያውቅ ዠዋውም ምሥራቹን ሰምቶ በሕይወቱ ላይ ትልቅ ለውጥ አደረገ። ዠዋው ምስሎችን ለአምልኮ መጠቀምን ይሖዋ እንደማይደግፍ ሲገነዘብ የሰበሰባቸውን “የቅዱሳን” ምስሎች አስወገደ። የቀድሞ አኗኗሩን እርግፍ አድርጎ ከተወ በኋላ እርሱም ተጠመቀ።

ካርሎስና ዠዋው በአንድ የመንግሥት አዳራሽ ውስጥ ሲገናኙና ሁለቱም ያደረጓቸውን ለውጦች ሲመለከቱ ምን ያህል እንደተደሰቱ ገምቱ! አሁን ሁለቱም ኃላፊነት የሚሰማቸው የቤተሰብ ራሶች ሲሆኑ ቀናተኛ የመንግሥቱ አዋጅ ነጋሪዎች በመሆን ያገለግላሉ።

በአሁኑ ወቅት በብራዚል ውስጥ 2, 500 የሚያህሉ አስፋፊዎችን ያቀፉ 30 የምልክት ቋንቋ ጉባኤዎችና 154 ቡድኖች ያሉ ሲሆን ከአስፋፊዎቹ ውስጥ 1, 500 የሚያህሉት መስማት የተሳናቸው ናቸው። በ2001 በብራዚል በምልክት ቋንቋ በተደረጉት “የአምላክ ቃል አስተማሪዎች” የአውራጃ ስብሰባዎች ላይ ከ3, 000 የሚበልጡ ተሰብሳቢዎች ተገኝተው የነበረ ሲሆን 36 የሚያህሉ ሰዎች ተጠምቀዋል። የይሖዋ በረከት ታክሎበት መስማት የተሳናቸው ሌሎች በርካታ ሰዎች የመንግሥቱን መልእክት እንደሚቀበሉ ተስፋ እናደርጋለን።

[የግርጌ ማስታወሻ]

a ስሞቹ ተቀይረዋል።