በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የአንባብያን ጥያቄዎች

የአንባብያን ጥያቄዎች

የአንባብያን ጥያቄዎች

ኢሳይያስ 30:20 “ዓይኖችህ ግን አስተማሪህን ያያሉ” በማለት ይሖዋ ከፊታችን እንዳለ እየተናገረ ቁጥር 21 የይሖዋ ቃል ‘ከበስተኋላ’ እንደሚመጣ አድርጎ የሚናገረው ለምንድን ነው?

ኢሳይያስ 30:20, 21 እንዲህ ይላል:- “አስተማሪህ እንግዲህ ከአንተ አይሰወርም፤ ዓይኖችህ ግን አስተማሪህን ያያሉ፣ ወደ ቀኝም ወደ ግራም ፈቀቅ ብትል ጆሮችህ በኋላህ:- መንገዱ ይህች ናት በእርስዋም ሂድ የሚለውን ቃል ይሰማሉ።”

ጥቅሱን ቃል በቃል ከተረዳነው አንባቢው ታላቁን አስተማሪ ይሖዋን ከፊት ለፊቱ እያየው ድምፁን የሚሰማው ግን ከበስተኋላው ነው። ይሁን እንጂ ቃላቱ ምሳሌያዊ ስለሆኑ ልንረዳቸው የሚገባንም በዚያ መንገድ ነው።

አንድ ሰው ቁጥር 20ን ሲያነብብ ወደ አእምሮው የሚመጣው የጌታውን ትእዛዝ ተቀብሎ ለመፈጸም ዝግጁ የሆነን አገልጋይ ነው። አንድ አገልጋይ የጌታውን መመሪያ ለመረዳት እጁ የሚያመለክትበትን አቅጣጫ በትኩረት እንደሚከታተል ሁሉ በዛሬው ጊዜም የይሖዋ ሕዝቦች ይሖዋ በምድራዊ ድርጅቱ በኩል በየጊዜው የሚሰጣቸውን በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረቱ መመሪያዎች በንቃት ይከታተላሉ። (መዝሙር 123:1, 2) አዎን፣ ይሖዋ ‘በታማኝና ልባም ባሪያ’ በኩል የሚሰጣቸውን ማንኛውንም መመሪያ በትኩረት በመከታተል ፈቃዱን ይፈጽማሉ።​—⁠ማቴዎስ 24:45-47

ታዲያ አገልጋዮቹ ከበስተኋላቸው እንደሚሰሙት ተደርጎ የተገለጸው ድምፅ ምን ያመለክታል? ከበስተኋላ የሚሰሙት ድምፅ አምላክ በጥንት ጊዜ የተናገረውና ‘በታማኝ መጋቢው’ በኩል የሚብራራው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሰፈረው ቃሉ ነው ብሎ መደምደሙ ምክንያታዊ ይመስላል። (ሉቃስ 12:42) በጊዜያችን ያሉት የአምላክ አገልጋዮች ‘በታማኝና ልባም ባሪያ’ ማለትም ‘በታማኝ መጋቢው’ ተዘጋጅተው በሚቀርቡላቸው ጽሑፎች እየታገዙ መጽሐፍ ቅዱስን በትጋት በማጥናትና በውስጡ የሰፈሩትን መሠረታዊ መመሪያዎች በሥራ ላይ በማዋል የአምላክን ድምፅ ይሰማሉ። ታላቁ አስተማሪ ወቅቱን ጠብቆ በሚሰጣቸው መመሪያ ላይ በመታመንና መመሪያውን በሚገባ በማስተዋል እንዲሁም ከብዙ መቶ ዘመናት በፊት የተጻፈውን ቃሉን በማጥናት በምሳሌያዊ ሁኔታ ከፊት ለፊታቸው እያዩት ድምፁን ከኋላቸው ይሰሙታል።​—⁠ሮሜ 15:4