በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

አስደሳች ዘገባ

አስደሳች ዘገባ

አስደሳች ዘገባ

ሪቻርድ ኤቭሊን በርድ የተባለው አሳሽ ከ1928 እስከ 1956 ባሉት ዓመታት አምስት ጊዜ ወደ አንታርክቲካ ጉዞ አድርጓል። ጉዞውን በተመለከተ ያሰፈረው የግል ማስታወሻ እርሱና ጓደኞቹ የንፋስ አቅጣጫን ለማወቅ፣ ካርታዎችን ለማዘጋጀትና ስለ አንታርክቲካ አህጉር በቂ መረጃ እንዲያገኙ አስችሏቸዋል።

በርድ ስላደረገው ጉዞ ያሰፈረው ዘገባ የግል ማስታወሻ መያዝ ምን ያህል ጥቅም እንዳለው ያስገነዝበናል። ብዙውን ጊዜ አሳሾች በመርከብ ወይም በአውሮፕላን ስላደረጉት ጉዞ ዝርዝር ማስታወሻ የሚይዙ ሲሆን ይህም በወቅቱ ምን ነገሮች እንደተከናወኑና ምን ሁኔታዎች እንዳጋጠሟቸው ለማወቅ ከመርዳቱም በላይ ለቀጣይ ጉዞ መረጃ ለማግኘት ያስችላል።

ቅዱሳን ጽሑፎች በኖኅ ዘመን ስለደረሰው የጥፋት ውኃ የሚተርኩ አስደናቂ ዘገባዎችን ይዘዋል። ይህ ዓለም አቀፍ የውኃ መጥለቅለቅ ከአንድ ዓመት በላይ ቆይቷል። ይህ የጥፋት ውኃ ከመድረሱ በፊት ኖኅ፣ ሚስቱና ሦስት ወንዶች ልጆቹ ከነሚስቶቻቸው 40, 000 ሜትር ኩብ ስፋት ያለው አንድ ግዙፍ መርከብ ለመሥራት 50 ወይም 60 ዓመት ፈጅቶባቸዋል። ይህንን መርከብ መሥራት ያስፈለጋቸው ለምንድን ነው? ከሚመጣው የጥፋት ውኃ ሰዎችንና እንስሳትን ለማዳን ነው።​—⁠ዘፍጥረት 7:1-3

በዚህም መሠረት የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል በሆነው በዘፍጥረት መጽሐፍ ውስጥ የሚገኘው የጥፋት ውኃው ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶ ኖኅና ቤተሰቡ ከመርከቡ እስከወጡበት ጊዜ ድረስ የሚተርከው ዘገባ ኖኅ ያሰፈረው የግል ማስታወሻ እንደሆነ ተደርጎ ሊቆጠር ይችላል። ታዲያ ይህ ማስታወሻ በዛሬ ጊዜ ለምንኖረው ለእኛ የሚሰጠው ጥቅም ይኖራልን?