በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የዘላለም ሕይወትን ምረጥ

የዘላለም ሕይወትን ምረጥ

የዘላለም ሕይወትን ምረጥ

ሰዎች የአሁኑን ጊዜ ያህል የተለያዩ ምርጫዎችን የማድረግ አጋጣሚ ያገኙበት ዘመን የለም። ለምሳሌ ያህል የምንለብሰውን ልብስ፣ የምንመገበውን ምግብ፣ የምንሠማራበትን የሥራ መስክና የምንኖርበትን ቦታ እንመርጣለን። በአብዛኛው የዓለም ክፍል የትዳር ጓደኛን መምረጥም የተለመደ ነው። ይሁን እንጂ መጽሐፍ ቅዱስ ለመላው የሰው ዘር ከምንም ነገር የላቀ አንድ ምርጫ ያቀርባል።

መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል:- “መልካም ሥራ ለማድረግ ቁርጥ ውሳኔ ያደረገ ሰው፣ በሕይወት ይኖራል፤ ስሕተት በማድረግ የሚጸና ግን ይሞታል።” (ምሳሌ 11:​19 የ1980 ትርጉም ) እንዲሁም ኢየሱስ ክርስቶስ “እውነተኛ አምላክ ብቻ የሆንህ አንተን የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ሕይወት ናት” በማለት ተናግሯል።​—⁠ዮሐንስ 17:3

አዎን፣ ፈጣሪያችን ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራውን ጎዳና ለመከተል እንድንመርጥ ግብዣ አቅርቦልናል! የዘላለም ሕይወት ለማግኘት ምን ማድረግ ይኖርብናል?

መጽሐፍ ቅዱስ “በጽድቅ መንገድ ላይ ሕይወት አለ” በማለት ይናገራል። (ምሳሌ 12:28) እኛም ወደ ዘላለም ሕይወት የሚወስደውን ጎዳና ከሚከተሉት ጻድቃን መካከል ልንሆን እንችላለን። እንዴት? ሕይወታችንን ከአምላክ ፈቃድና ትእዛዛት ጋር በማስማማት ነው። (ማቴዎስ 7:​13, 14) እንግዲያው ትክክለኛ ምርጫ በማድረግ አምላክ ያዘጋጀልንን የዘላለም ሕይወት ስጦታ እንቀበል።​—⁠ሮሜ 6:​23