ሚስዮናውያንን በማሠልጠን 60 ዓመታት ያስቆጠረው የጊልያድ ትምህርት ቤት
ሚስዮናውያንን በማሠልጠን 60 ዓመታት ያስቆጠረው የጊልያድ ትምህርት ቤት
“መጽሐፍ ቅዱስን በጥልቀት ስላጠናን ወደ ይሖዋ ይበልጥ መቅረብ የቻልን ሲሆን ስለ ድርጅቱም ተጨማሪ እውቀት አግኝተናል። ይህም በባዕድ አገር ለምናከናውነው አገልግሎት አዘጋጅቶናል።” የመጀመሪያው ክፍል ተማሪ የነበረች አንዲት እህት በጊልያድ የመጠበቂያ ግንብ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ቤት ስላገኘችው ሥልጠና የተሰማትን የገለጸችው እንዲህ በማለት ነበር። ከተቋቋመ 60 ዓመታት ያሳለፈው የጊልያድ ትምህርት ቤት ሚስዮናውያንን እያሠለጠነ ወደተለያዩ አገሮች ሲልክ ቆይቷል። የ114ኛው ክፍል ተማሪዎች የምረቃ ሥነ ሥርዓት በመጋቢት 8, 2003 ፓተርሰን፣ ኒው ዮርክ በሚገኘው የመጠበቂያ ግንብ ማኅበር የትምህርት ማዕከል ተካሄዶ ነበር። በምረቃው አዳራሽና ፕሮግራሙ በሳተላይት አማካኝነት በቴሌቪዥን በተላለፈባቸው ቦታዎች የተገኙ 6, 404 የሚያህሉ ተሰብሳቢዎች በንግግር፣ በቃለ ምልልስና በቡድን ውይይት የቀረበውን ፕሮግራም በጥሞና ተከታትለዋል።
የፕሮግራሙ ሊቀመንበር የአስተዳደር አካል አባል የሆነው ቴዎዶር ጃራዝ ነበር። በንግግሩ መክፈቻ ላይ ተሰብሳቢዎቹ ከእስያ፣ ከካሪቢያን አገሮች፣ ከመካከለኛውና ከደቡብ አሜሪካ እንዲሁም ከአውሮፓ የመጡ መሆናቸውን ገለጸ። ወንድም ጃራዝ በ2 ጢሞቴዎስ 4:5 ላይ በማተኮር በጊልያድ የሠለጠነ አንድ ሚስዮናዊ ዋነኛ ተግባሩ ‘የወንጌል ሰባኪነት ሥራ’ መሆኑን ጎላ አድርጎ ተናገረ። ሚስዮናውያኑ መጽሐፍ ቅዱስን ለሰዎች በማስተማር ለእውነት ይመሰክራሉ።
ተማሪዎቹ የመጨረሻ መመሪያ ተሰጣቸው
በተከታታይ ከቀረቡት አጫጭር ንግግሮች ውስጥ የመጀመሪያውን ያቀረበው የዩናይትድ ስቴትስ ቅርንጫፍ ኮሚቴ አባል የሆነው ጆን ላርሰን ሲሆን እምነት የሚያጠነክረው ንግግሩ “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ማን ይቃወመናል?” የሚል ርዕስ ነበረው። (ሮሜ 8:31) ወንድም ላርሰን ተማሪዎቹ በአገልግሎት ምድባቸው የሚያጋጥማቸውን ማንኛውንም እንቅፋት ለመቋቋም ትምክህታቸውን በይሖዋ ኃይል ላይ እንዲጥሉ የሚያደርጓቸውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃዎች ገለጸ። ከዚያም ሮሜ 8:38, 39ን ጠቅሶ “አምላክ እናንተን ለመርዳት ስለሚጠቀምበት ኃይል ቆም ብላችሁ አሰላስሉ፤ እንዲሁም ይሖዋ ለእናንተ ያለውን ፍቅር ምንም ነገር ሊያቀዘቅዘው እንደማይችል አትዘንጉ” በማለት ተማሪዎቹን አሳሰባቸው።
ቀጣዩን ንግግር ያቀረበው የአስተዳደር አካል አባል የሆነው ጋይ ፒርስ ሲሆን የንግግሩ ጭብጥ “ዓይናችሁ ደስተኛ ይሁን!” የሚል ነበር። (ሉቃስ 10:23) እውነተኛ ደስታ የሚገኘው ይሖዋን በማወቅና ዘላለማዊ ዓላማውን በመረዳት እንዲሁም የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶች ፍጻሜያቸውን ሲያገኙ በመመልከት መሆኑን ተናገረ። ተማሪዎቹ በሚሄዱበት ቦታ ሁሉ ደስተኛ ዓይን እንዲኖራቸው በማድረግ እውነተኛ ደስታ ማግኘት ይችላሉ። ወንድም ፒርስ ተማሪዎቹ በይሖዋ ጥሩነት ላይ በጥልቀት እንዲያሰላስሉና አእምሯቸውና ልባቸው ፈቃዱን በማድረግ ላይ ያተኮረ እንዲሆን አበረታታቸው። (መዝሙር 77:12) ተመራቂዎቹ አዎንታዊ አመለካከት በመያዝ ሊያጋጥማቸው የሚችለውን ማንኛውንም ችግር ማሸነፍ ይችላሉ።
ከዚያም በየዕለቱ ሲያስተምሯቸው ከነበሩት አስተማሪዎች ውስጥ ሁለቱ የመሰናበቻ ንግግር በማቅረብ ተማሪዎቹን አበረታቱ። ወንድም ሎውረንስ ቦወን ያቀረበው ንግግር “የራሳችሁን ክብር ትፈልጋላችሁን?” የሚል በጥያቄ መልክ የቀረበ ርዕስ ነበረው። ብዙ ሰዎች ክብርን አድናቆት ከማትመዝሙር 73:24, 25) ተመራቂዎቹ መጽሐፍ ቅዱስን ሳያሰልሱ በጥልቀት በማጥናት ከይሖዋ ጋር የመሠረቱትን የጠበቀ ዝምድና ይበልጥ እያጠናከሩ እንዲሄዱ ማበረታቻ ተሰጥቷቸዋል። መላእክት እንኳን ክርስቶስ የይሖዋን ዓላማ ስለሚያስፈጽምበት መንገድ በዝርዝር ለማወቅ “ይመኛሉ።” (1 ጴጥሮስ 1:12) ክብሩን ለማንጸባረቅ እንዲችሉ ስለ አባታቸው ብዙ ለማወቅ ይጥራሉ። ከዚያም ወንድም ቦወን ተማሪዎቹ በሚስዮናዊነት እንዲያገለግሉ በተመደቡባቸው ቦታዎች ሌሎች ከይሖዋ ጋር በዋጋ ሊተመን የማይችል ዝምድና ለመመሥረት እንዲችሉ በመርዳት እርሱን ከፍ ከፍ እንዲያደርጉት አበረታታቸው።
ረፍ፣ ታዋቂ ከመሆንና የሌሎችን ከበሬታ ከማግኘት ጋር ያያይዙታል። ይሁን እንጂ መዝሙራዊው አሳፍ እውነተኛ ክብር ከይሖዋ ጋር ያለን በዋጋ ሊተመን የማይችለው የተቀደሰ ዝምድና እንደሆነ ተገንዝቦ ነበር። (በተከታታይ ከቀረቡት የመክፈቻ ንግግሮች ውስጥ የመጨረሻውን ያቀረበው የትምህርት ቤቱ ሬጅስትራር የሆነው ዋላስ ሊቨራንስ ሲሆን የንግግሩ ጭብጥ “ቅዱስ ምሥጢር የሆነውን የአምላክን ጥበብ ተናገሩ” የሚል ነበር። (1 ቆሮንቶስ 2:7) ሐዋርያው ጳውሎስ ሚስዮናዊ ሆኖ ባገለገለበት ወቅት የተናገረለት ይህ አምላካዊ ጥበብ ምንድን ነው? ይሖዋ ዓለም አቀፋዊ ሰላምና አንድነት ለማምጣት የሚጠቀምበት ጥበቡና ኃይሉ ነው። ይህ ጥበብ በኢየሱስ ላይ ያተኮረ ነው። ጳውሎስ ማኅበራዊ ችግሮች ስለሚወገዱበት መንገድ አልሰበከም፤ ከዚህ ይልቅ አምላክ የአዳም ኃጢአት ያስከተለውን መዘዝ ስለሚያስተካክልበት መንገድ ሰዎች እንዲገነዘቡ ረድቷል። (ኤፌሶን 3:8, 9) ወንድም ሊቨራንስ “ጳውሎስ ሚስዮናዊ አገልግሎቱን የተመለከተው ይሖዋ ዓላማውን ስለሚያስፈጽምበት መንገድ ሰዎች እንዲገነዘቡ ለመርዳት የሚያስችል አጋጣሚ እንደሆነ አድርጎ ነበር። እናንተም ተመሳሳይ አመለካከት ይኑራችሁ” በማለት አድማጮቹን አሳሰባቸው።
ቀጥሎ የጊልያድ አስተማሪ የሆነው ማርክ ኑሜር በርከት ካሉ ተማሪዎች ጋር አስደሳች ውይይት አደረገ። ውይይቱ በሮሜ 10:10 ላይ በሚገኙት የጳውሎስ ቃላት ላይ የተመሠረተ ሲሆን “የአምላክን ቃል ማጥናት ቀናተኛ አገልጋዮችን ለማፍራት ያስችለናል” የሚል ጭብጥ ነበረው። ተማሪዎቹ በትምህርት ቤት ሥልጠናቸው ወቅት በመስክ አገልግሎት ሲካፈሉ ያገኟቸውን የተለያዩ ተሞክሮዎች ተናገሩ። ተሞክሮዎቹ የአምላክን ቃል ካጠናንና ባጠናነው ነገር ላይ ካሰላሰልን ልባችን ስለ ይሖዋ አምላክ እና ስለ መንግሥቱ በሚናገሩ ግሩም ተስፋዎች እንደሚሞላና እነዚህን ተስፋዎች ለሌሎች ሰዎች ለማስተማር እንደምንገፋፋ የሚያሳዩ ናቸው። ተማሪዎቹ በመጠበቂያ ግንብ ማኅበር የትምህርት ማዕከል በቆዩባቸው አምስት ወራት ውስጥ በአካባቢው ባሉ በተደጋጋሚ የተሠራባቸው የአገልግሎት ክልሎች ተሰማርተው ከ30 በላይ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶችን ለማስጀመር ችለዋል።
የጎለመሱ ወንድሞች የሰጡት ምክር
ተማሪዎቹ በሥልጠናው ወቅት ከዩናይትድ ስቴትስ የቤቴል ቤተሰብ አባላት ጋር የተቀራረበ ወዳጅነት ለመመሥረት በመቻላቸው ጥቅም አግኝተዋል። የዩናይትድ ስቴትስ ቅርንጫፍ ቢሮ አባላት የሆኑት ሮበርት ሲራንኮ እና ሮበርት ፒ ጆንሰን በመጠበቂያ ግንብ ማኅበር የትምህርት ማዕከል ልዩ ሥልጠና በመውሰድ ላይ ለነበሩ ተጓዥ የበላይ ተመልካቾችና ለረጅም ዓመታት ይሖዋን በታማኝነት ላገለገሉ ወንድሞች ቃለ ምልልስ አደረጉላቸው። እነዚህ ወንድሞች የጊልያድ ምሩቅ ሲሆኑ በአንድ ወቅት በሚስዮናዊነት አገልግለዋል። ተማሪዎቹ፣ ቤተሰቦቻቸውና ወዳጆቻቸው ከእነዚህ በመንፈሳዊ የጎለመሱ ወንድሞች ግሩም ምክሮችን መስማታቸው አስደስቷቸዋል።
ከምክሮቹ መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል:- “በአገልግሎትና በጉባኤ ሥራዎች የተጠመዳችሁ ሁኑ።” “ራሳችሁን ከፍ አድርጋችሁ አትመልከቱ። በሚስዮናዊነት ለምታከናውኑት ሥራ ትኩረት ስጡ። እንዲሁም የተመደባችሁበትን ቦታ እንደ ትውልድ አገራችሁ አድርጋችሁ ቁጠሩት።” ሌሎች ምክሮች ደግሞ አንድ የአምላክ አገልጋይ ከጊልያድ ትምህርት ቤት ያገኘው ሥልጠና በተመደበበት ቦታ ሁሉ መልካም ሥራ ለማከናወን እንዴት እንደሚያስታጥቀው የሚጠቁሙ ነበሩ። አንዳንዶቹ የሚከተሉት ናቸው:- “በኅብረት እንዴት መሥራት እንደምንችል ተምረናል።” “ትምህርት ቤቱ ከማናውቃቸው ባሕሎች ጋር እንድንላመድ አስችሎናል።” “የቅዱሳን ጽሑፎችን አጠቃቀም በተመለከተ አዲስ ግንዛቤ አግኝተናል።”
የአስተዳደር አካል አባል ሆኖ ለረጅም ዓመታት ያገለገለው ወንድም ጆን ኢ ባር “ድምፃቸው በምድር ሁሉ ላይ ወጣ” በሚል ጭብጥ የፕሮግራሙን ዋነኛ ንግግር አቀረበ። (ሮሜ 10:18) የአምላክ ሕዝቦች በዛሬው ጊዜ ይህን ተልዕኮ መወጣት ችለው ይሆን? የሚል ጥያቄ አቀረበ። መልሱ አዎን የሚል ነው። በ1881 ለመጠበቂያ ግንብ አንባቢዎች “ምሥራቹን እየሰበካችሁ ነው?” የሚል ጥያቄ ቀርቦላቸው ነበር። ከዚያም ወንድም ባር አድማጮቹን በ1922 በሴዳር ፖይንት፣ ኦሃዮ፣ ዩ ኤስ ኤ በተደረገው የአውራጃ ስብሰባ ላይ የቀረበውን “ንጉሡንና መንግሥቱን አስታውቁ!” የሚል ታሪካዊ ጥሪ አስታወሳቸው። ጊዜ እያለፈ ሲሄድ የአምላክ ታማኝ አገልጋዮች የነበራቸው ቅንዓት የመንግሥቱን ግሩም እውነቶች ለአሕዛብ ሁሉ እንዲያውጁ ገፋፍቷቸዋል። ምሥራቹ በጽሑፎችና በቃል እስከ ምድር ዳርቻ የተዳረሰ ሲሆን ይህም ለይሖዋ ክብርና ውዳሴ አምጥቷል። ወንድም ባር ንግግሩን ስሜት ቀስቃሽ በሆነ ሁኔታ ሲደመድም “በተመደባችሁበት ቦታ ሆናችሁ በየዕለቱ ወደ ይሖዋ ስትጸልዩ ‘ድምፃቸው በምድር ሁሉ ላይ ወጣ’ በሚሉት ቃላት ፍጻሜ ረገድ ለምትጫወቱት ሚና ከልባችሁ አመስግኑት” በማለት ተመራቂዎቹ ከይሖዋ የሚያገኙትን በረከት ከፍ አድርገው እንዲመለከቱ መከራቸው።
ከዚህ ንግግር በኋላ ከተለያዩ ቅርንጫፍ ቢሮዎች የተላኩ ሰላምታዎች የተነበቡ ሲሆን ተመራቂዎቹ ከሊቀ መንበሩ ዲፕሎማቸውን ተቀበሉ። አንድ የክፍሉ ተወካይ ለአስተዳደር አካል እንዲሁም ለመላው የቤቴል ቤተሰብ የተጻፈና ተመራቂዎቹ ይሖዋን “ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘላለም” ለመባረክ ያላቸውን ቁርጠኝነት የሚገልጽ ደብዳቤ ደስታና ሐዘን በተቀላቀለበት ስሜት አነበበ።—መዝሙር 115:18
እነዚህ አዲስ ተመራቂዎች የተመደቡበትን አገር እንዲለምዱና ባለፉት 60 ዓመታት የተላኩት ሚስዮናውያን እንዳከናወኑት ሁሉ እነርሱም ዓለም አቀፋዊው የስብከት ሥራ እድገት እንዲያደርግ የበኩላቸውን እገዛ እንዲያበረክቱ እንጸልያለን።
[በገጽ 23 ላይ የሚገኝ ሣጥን]
ስለ ተማሪዎቹ የቀረበ አኃዛዊ መረጃ
የተውጣጡባቸው አገሮች ብዛት:- 12
የተመደቡባቸው አገሮች ብዛት:- 16
የተማሪዎቹ ብዛት:- 48
አማካይ ዕድሜ:- 34.4
በእውነት ውስጥ የቆዩባቸው ዓመታት በአማካይ:- 17.6
በሙሉ ጊዜ አገልግሎት የቆዩባቸው ዓመታት በአማካይ:- 13.5
[በገጽ 24 ላይ የሚገኝ ሥዕል]
የጊልያድ የመጠበቂያ ግንብ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ቤት 114ኛ ክፍል ተመራቂዎች
ከዚህ በታች ባለው ዝርዝር ለእያንዳንዱ ረድፍ ቁጥር የተሰጠው ከፊት ወደ ኋላ ሲሆን ስሞቹ የሰፈሩት ከግራ ወደ ቀኝ ነው።
(1) ሮዛ ዲ፣ ጋሪጎላስ ጄ፣ ሊንድስትረም አር፣ ፓቨኔሎ ፒ፣ ቴት ኤን፤ (2) ቫን ሃውት ኤም፣ ዶናባውር ሲ፣ ማርቲኔስ ኤል፣ ሚለር ዲ፣ ፌስትሬ ዋይ፣ ነተር ኤስ፤ (3) ማርቲኔስ ፒ፣ ክላርክ ኤል፣ ማውን ቢ፣ ፊሸር ኤል፣ ሮሞ ጂ፤ (4) ሮሞ አር፣ ኢዲ ኤስ፣ ታይመን ሲ፣ ካምፕቤል ፒ፣ ሚለር ዲ፣ ሮዛ ደብሊው፤ (5) ሊንድስትረም ሲ፣ ጋሪጎላስ ጄ፣ ማርክቪች ኤን፣ ሊንዳላ ኬ፣ ቫን ዴን ሆይቨል ጄ፣ ቴት ኤስ፣ ነተር ፒ፤ (6) ማውን ፒ፣ ፓቨኔሎ ቪ፣ ኢዲ ኤን፣ ዌስት ኤ፣ ክላርክ ዲ፣ ማርክቪች ጄ፤ (7) ፊሸር ዲ፣ ዶናባውር አር፣ ከሪ ፒ፣ ከሪ ዋይ፣ ካርፋኖ ደብሊው፣ ዌስት ኤም፣ ታይመን ኤ፤ (8) ቫን ሃውት ኤም፣ ካምፕቤል ሲ፣ ፌስትሬ ዋይ፣ ካርፋኖ ሲ፣ ቫን ዴን ሆይቨል ኬ፣ ሊንዳላ ዲ።