በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ተራ ልማድ ወይስ ጉቦ?

ተራ ልማድ ወይስ ጉቦ?

ተራ ልማድ ወይስ ጉቦ?

ፖላንድ ውስጥ በአንዳንድ ኮሌጆች ተማሪዎች የተሻለ የፈተና ውጤት እናገኛለን በሚል ተስፋ ለአስተማሪዎቻቸው ስጦታ ለመስጠት ገንዘብ የማዋጣት ልማድ አላቸው። ከዚህም የተነሳ ካታርዚና የተባለች ወጣት ክርስቲያን ፈታኝ ሁኔታ ያጋጠማት ሲሆን “ገንዘብ ልስጥ ወይስ አልስጥ?” የሚል ጥያቄም ተደቀነባት። ጓደኞቿ እንዲህ በማለት ሊያሳምኗት ሞከሩ:- “ይሄ እንደሆነ ድሮም የነበረ ልማድ ነው። ደግሞም ትጠቀሚያለሽ እንጂ አትጎጂም፤ ለምን ታመነቻለሽ ታዲያ?”

ካታርዚና “እውነቱን ለመናገር የአንደኛ ዓመት ተማሪ በነበርኩበት ጊዜ እኔም ገንዘብ አዋጥቼ ነበር” በማለት ሳትሸሽግ ተናግራለች። “እንዲህ ማድረግ መጽሐፍ ቅዱስ በሚያወግዘው ጉቦ በመስጠት ተግባር መሳተፍ እንደሆነ የገባኝ ከጊዜ በኋላ ነበር።” ይሖዋ ጉቦን ፈጽሞ እንደሚያወግዝ የሚናገሩ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን አስታወሰች። (ዘዳግም 10:​17፤ 16:​19፤ 2 ዜና መዋዕል 19:​7) ካታርዚና እንዲህ ትላለች:- “አንድ ሰው በእኩዮች ተጽዕኖ በቀላሉ ሊሸነፍ እንደሚችል ተገንዝቤያለሁ። በጉዳዩ ላይ በጥሞና ካሰብኩበት በኋላ ከዚያ ጊዜ ወዲህ በዚህ ልማድ ተካፍዬ አላውቅም።” ባለፉት ሦስት ዓመታት፣ ተማሪዎቹ ቢያፌዙባትም እንኳ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ በተመሠረተ እምነቷ የተነሳ “ለስጦታ” መግዣ ገንዘብ በማዋጣቱ ተግባር መሳተፍ እንደማትፈልግ ለአንዳንዶቹ ማስረዳት ችላለች።

አንዳንዶች ካታርዚና ራስ ወዳድና ለሌሎች የማታስብ እንደሆነች ይናገራሉ። “አሁንም ቢሆን አንዳንዶቹ ፊት ይነሱኛል። በአንጻሩ ደግሞ ብዙዎች አመለካከቴን ያከብሩልኛል፤ በዚህም እደሰታለሁ” ብላለች። ካታርዚና የይሖዋ ምሥክር እንደሆነችና በዕለታዊ ሕይወቷ የመጽሐፍ ቅዱስን መሠረታዊ ሥርዓቶች እንደምታከብር ሌሎች ማወቅ ችለዋል።