በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

እርዳታ ለሚሹ የሚሆን መጽናኛ

እርዳታ ለሚሹ የሚሆን መጽናኛ

እርዳታ ለሚሹ የሚሆን መጽናኛ

መጽሐፍ ቅዱስ የሥነ ልቦና መመሪያ መጽሐፍ አይደለም። ይሁን እንጂ መጽናኛ የሚሰጠን ከመሆኑም በላይ ችግሮች ቢያጋጥሙንም ለሕይወት አድናቆት እንዲኖረን ይረዳናል። ቅዱሳን ጽሑፎች “ከሴት የተወለደ ሰው የሕይወቱ ዘመን ጥቂት ቀን ነው፣ መከራም ይሞላዋል” በማለት ሐቁን ይናገራሉ። (ኢዮብ 14:1) አንዳንድ ጊዜ መከራ የሚደርስብን በራሳችን አለፍጽምና የተነሳ ነው። ይሁን እንጂ በሰው ልጆች ላይ ለሚደርሰው ሥቃይና መከራ በዋነኝነት የሚጠየቀው ማን ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ ተጠያቂው ሰይጣን ዲያብሎስ የሚባል ክፉ መንፈሳዊ ፍጡር እንደሆነ ይናገራል። ‘ዓለሙን ሁሉ ያስታል’፤ እንዲሁም በሰው ልጆች ላይ የተለያዩ መከራዎች ያመጣል። ሆኖም የቀረው ዕድሜ አጭር እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ይነግረናል። (ራእይ 12:9, 12) አምላክ በቅርቡ ጣልቃ በመግባት ሰይጣን በምድር ነዋሪዎች ላይ ያስከተለውን ሥቃይ ሙሉ በሙሉ ያስወግዳል። መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚናገረው አምላክ በሚያመጣው ጽድቅ የሰፈነበት አዲስ ዓለም ውስጥ ተስፋ መቁረጥ አይኖርም።—2 ጴጥሮስ 3:13

በሰው ልጆች ላይ የሚደርሰው ሥቃይና መከራ ጊዜያዊ መሆኑን ማወቅ ምንኛ ያጽናናል! የአምላክ ሰማያዊ መንግሥት ንጉሥ በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ አገዛዝ ሥር የፍትሕ መጓደልና መከራ አይኖርም። መጽሐፍ ቅዱስ በአምላክ የተሾመውን ይህን ንጉሥ በሚመለከት እንዲህ ይላል:- “ችግረኛውን ከቀማኛው እጅ፣ ረዳት የሌለውንም ምስኪን ያድነዋልና። ለችግረኛና ለምስኪን ይራራል፣ የችግረኞችንም ነፍስ ያድናል። ከግፍና ከጭንቀት ነፍሳቸውን ያድናል፤ ስማቸው በፊቱ ክቡር ነው።”—መዝሙር 72:12-14

እነዚህ ትንቢታዊ ቃላት ፍጻሜያቸውን የሚያገኙበት ጊዜ በጣም ቀርቧል። አስደሳች ሁኔታዎች በሚሰፍኑባት ምድራዊ ገነት ውስጥ ለዘላለም መኖር እንችላለን። (ሉቃስ 23:43፤ ዮሐንስ 17:3) እርዳታ የሚሹ ሰዎች ስለ እነዚህ ቅዱስ ጽሑፋዊ ተስፋዎች ማወቃቸው ያጽናናቸዋል።

[ምንጭ]

ያዘነች ልጅ:- Photo ILO/J. Maillard