በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

‘እውነተኛዋ ቤተ ክርስቲያን’ አንዲት ብቻ ናት?

‘እውነተኛዋ ቤተ ክርስቲያን’ አንዲት ብቻ ናት?

‘እውነተኛዋ ቤተ ክርስቲያን’ አንዲት ብቻ ናት?

“ክርስቶስ አንድ ብቻ እንደሆነ ሁሉ የክርስቶስ አካልም አንድ ብቻ ነው፤ የክርስቶስ ሙሽራ አንዲት ብቻ ስትሆን እርሷም ሐዋርያዊቷ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ናት።”​—ዶሚኑስ ዬሱስ

የሮማ ካቶሊክ ካርዲናል የሆኑት ዮዜፍ ራትሲንገር እውነተኛዋ ቤተ ክርስቲያን አንዲት ብቻ ናት የሚለውን የቤተ ክርስቲያናቸውን ትምህርት የገለጹት በዚህ መንገድ ነበር። እንደ እርሳቸው አባባል ይህቺ ቤተ ክርስቲያን “የክርስቶስ ብቸኛ ቤተ ክርስቲያን የሆነችው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ናት።”

“ትክክለኛ አብያተ ክርስቲያናት አይደሉም”

ሊቀ ጳጳስ ጆን ፖል ዳግማዊ ዶሚኑስ ዬሱስ በተባለው ጽሑፍ ላይ የሰፈረው ሐሳብ “ሌሎች ሃይማኖቶችን የሚያንኳስስ ወይም የሚያቃልል” ምንም መልእክት እንደማያስተላልፍ ቢከራከሩም የፕሮቴስታንት ቤተ ክርስቲያን መሪዎች ግን አጥብቀው ተቃውመውታል። ለምሳሌ ያህል፣ ሰኔ 2001 በሰሜናዊ አየርላንድ፣ ቤልፋስት በተደረገው የፕሪስባይቴሪያን ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ንግግር ያቀረቡ አንድ ቄስ በጽሑፉ ላይ የሰፈረው ሐሳብ “በ2ኛው የቫቲካን ጉባኤ ላይ የቀረበው አዳዲስ ሐሳቦችን መቀበል አስፈላጊ ነው የሚለው አዝማሚያ ያስፈራው . . . በሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ሥር የሚገኝ አንድ ወገን” ያመነጨው እንደሆነ ተናግረዋል።

የአየርላንድ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ የሆኑት ራቢን ኢምስ ይህ ጽሑፍ ‘ቤተ ክርስቲያኗ ከ2ኛው የቫቲካን ጉባኤ በፊት ወደነበራት አመለካከት መመለሷን የሚያሳይ ከሆነ’ “በጣም አዝናለሁ” በማለት ተናግረዋል። ኢምስ አንዳንድ የካቶሊክ ሃይማኖታዊ ትምህርቶችን የማይቀበሉ አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ “ትክክለኛ አብያተ ክርስቲያናት አይደሉም” በሚለው የቫቲካን አመለካከት ላይ ሐሳብ ሲሰጡ “ይህ ለእኔ ስድብ ነው” ብለዋል።

ዶሚኑስ ዬሱስ የተባለው ጽሑፍ እንዲዘጋጅ ምክንያት የሆነው ምንድን ነው? ሃይማኖታዊ እውነቶች አንጻራዊ ናቸው የሚለው አመለካከት የሮማ ካቶሊክ መሪዎችን ስጋት ላይ የጣላቸው ይመስላል። ዚ አይሪሽ ታይምስ የተባለው መጽሔት ‘ሁሉም ሃይማኖቶች ጥሩ ናቸው የሚል ሃይማኖታዊ ትምህርት ብቅ ማለቱ ካርዲናል ራትሲንገርን እረፍት ነስቷቸዋል’ በማለት ዘግቧል። እውነተኛዋ ቤተ ክርስቲያን አንዲት ብቻ እንደሆነች እንዲናገሩ ያነሳሳቸው ይህ ሳይሆን አይቀርም።

የየትኛውም ቤተ ክርስቲያን አባል ብትሆን ለውጥ ያመጣል?

እርግጥ ነው፣ አንዳንዶች እውነተኛዋ ቤተ ክርስቲያን አንዲት ብቻ ናት ከሚለው ሐሳብ ይልቅ “ሃይማኖታዊ እውነቶች አንጻራዊ ናቸው” ወይም “ሁሉም ሃይማኖቶች ጥሩ ናቸው” የሚሉት አመለካከቶች ይበልጥ ምክንያታዊና ማራኪ እንደሆኑ ሊያስቡ ይችላሉ። እነዚህ ሰዎች ሃይማኖት ሙሉ በሙሉ የግል ምርጫ እንደሆነ ያምናሉ። ‘የየትኛውም ቤተ ክርስቲያን አባል ብትሆን ዞሮ ዞሮ የሚያመጣው ለውጥ የለም’ ብለው ይናገራሉ።

ይህ ዓይነቱ አመለካከት ሃይማኖቶች እንዲከፋፈሉና እንዲበዙ ምክንያት ቢሆንም ይበልጥ የመቻቻልን መንፈስ የሚያሰፍን ሊመስል ይችላል። ብዙዎች ‘በዚህ መንገድ ሃይማኖቶች መብዛታቸው ሰዎች ነጻነታቸውን በሚገባ እየተጠቀሙበት እንዳለ የሚያሳይ ነው’ ይላሉ። ይሁን እንጂ ስቲቭ ብሩስ የተባሉ አንድ ጸሐፊ እንዲህ ዓይነቱ “ሃይማኖታዊ መቻቻል . . . ከሃይማኖታዊ ግዴለሽነት” የመነጨ እንደሆነ ተናግረዋል።​—ኤ ሃውስ ዲቫይድድ :- ፕሮቴስታንቲዝም፣ ሲዝም ኤንድ ሴክዩላራይዜሽን

ታዲያ ትክክለኛው አመለካከት የትኛው ነው? እውነተኛዋ ቤተ ክርስቲያን አንዲት ብቻ ናት? ይህቺ እውነተኛ ቤተ ክርስቲያን የሮማ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ልትሆን ትችላለች? ሌሎች አብያተ ክርስቲያናትም በአምላክ ዘንድ እኩል ተቀባይነት አላቸው? እነዚህ ጥያቄዎች ከፈጣሪያችን ጋር ያለንን ዝምድና ስለሚነኩ በጉዳዩ ላይ የእርሱን አመለካከት ማወቁ አስፈላጊ ነው። ይህንን ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው? በአምላክ መንፈስ አነሳሽነት የተጻፈውን መጽሐፍ ቅዱስን በመመርመር ነው። (ሥራ 17:11፤ 2 ጢሞቴዎስ 3:16, 17) እውነተኛዋ ቤተ ክርስቲያን አንዲት ብቻ ናት የሚለውን አመለካከት በተመለከተ መጽሐፍ ቅዱስ ምን እንደሚል እንመልከት።

[በገጽ 2 ላይ የሚገኝ የሥዕል ምንጭ]

COVER: Mark Gibson/Index Stock Photography