በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

“ይህ ለእኔ አዲስ ነገር ነው!”

“ይህ ለእኔ አዲስ ነገር ነው!”

የመንግሥቱ አዋጅ ነጋሪዎች ሪፖርት

“ይህ ለእኔ አዲስ ነገር ነው!”

በፖላንድ የምትኖር የሙሉ ጊዜ ሰባኪ የሆነች ዶሮታ የተባለች የይሖዋ ምሥክር የ14 ዓመት ልጅዋ በየጊዜው የሚከታተለውን የጤና ምርመራ እንዲያደርግ ወደ ትምህርት ቤቱ ክሊኒክ ይዛው ሄደች። በምርመራው ወቅት ያኒና a የተባለችው ዶክተር ዶሮታን ልጅዋ ቤት ውስጥ ምን ሥራዎችን እንደሚያከናውን ጠየቀቻት።

“እኔ ሳልችል ከቀረሁ በቤት ውስጥ ላለነው ለስድስታችንም እራት ያዘጋጃል። ከዚህም በላይ ቤት ያጸዳል እንዲሁም አንዳንድ ነገሮችን ይጠግናል። ማንበብም ይወድዳል፤ ጎበዝ ተማሪ ነው” ስትል መለሰችላት።

ያኒና “በጣም የሚደንቅ ነገር ነው። እዚህ በሠራሁባቸው 12 ዓመታት ውስጥ እንዲህ ያለ ነገር ሰምቼ አላውቅም” አለች።

ዶሮታ ምሥክርነት ለመስጠት የሚያስችል አጋጣሚ እንደተከፈተላት ስለተሰማት “በዛሬው ጊዜ ብዙ ወላጆች ለልጆቻቸው ተገቢውን ሥልጠና አይሰጡም። በአብዛኛው ልጆች ለራሳቸው ጥሩ ግምት የማይኖራቸው ለዚህ ነው” አለቻት።

“ብዙ ወላጆች ስለነዚህ ነገሮች ምንም አያውቁም። አንቺ ይሄን ሁሉ እንዴት አወቅሽ?” ስትል ያኒና ጠየቀቻት።

ዶሮታ እንዲህ ስትል መለሰችላት:- “በዚህ ጉዳይ መጽሐፍ ቅዱስ ከፍተኛ ትምህርት ይዟል። ለምሳሌ ያህል ዘዳግም 6:​6-9 ልጆቻችንን ከማስተማራችን በፊት እኛው ራሳችን መማር እንዳለብን ይናገራል። በልጆቻችን ውስጥ መቅረጽ የምንፈልገውን ጥሩ ባሕርይ በመጀመሪያ እኛው ራሳችን ልናዳብረው አይገባም?”

ያኒና “ጉድ ነው! በጣም ይገርማል!” አለች። ከዚያም ልጆቿን ለማሳደግና ለማስተማር መጽሐፍ ቅዱስ እንዴት እንደጠቀማት ዶሮታን ጠየቀቻት።

ዶሮታ እንዲህ አለቻት:- “ከልጆቻችን ጋር በየሳምንቱ መጽሐፍ ቅዱስ እናጠናለን። ለዚህም ወጣቶች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎችና ተግባራዊ መሆን የሚችሉ መልሶች b የተባለ መጽሐፍ እንጠቀማለን።” ከዚያም ስለ መጽሐፉና በውስጡ ስለሚገኙት አንዳንድ ርዕሶች ነገረቻት።

ያኒናም “ይህ ለእኔ አዲስ ነገር ነው! መጽሐፉን ልታሳዪኝ ትችያለሽ?” አለቻት።

ከአንድ ሰዓት በኋላ ዶሮታ መጽሐፉን ይዛ ተመለሰች።

ያኒና መጽሐፉን ገለጥ ገለጥ አድርጋ እያየች “ሃይማኖትሽ ምንድን ነው?” ስትል ጠየቀቻት።

“የይሖዋ ምሥክር ነኝ።”

“የይሖዋ ምሥክሮች የሌላ እምነት ተከታይ ከሆኑ ሰዎች ጋር ያላቸው ግንኙነት ምን ይመስላል?”

“አንቺን በአክብሮት እንዳነጋገርኩሽ ሁሉ ለሌሎችም አክብሮት እናሳያለን። እርግጥ ሰዎች የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት ቢያውቁ ደስ ይለናል” ስትል ዶሮታ መለሰችላት።

“በዚህች አጭር ጊዜ ውስጥ እንኳ ብዙ ነገር አውቄያለሁ” ስትል ያኒና በግልጽ ነገረቻት።

ዶሮታ ከመሄዷ በፊት ያኒናን መጽሐፍ ቅዱስን እንድታነብብ አበረታታቻት። “ትርጉም ያለው ሕይወት እንድትኖሪ ያስችልሻል። ለሥራሽም ቢሆን ይጠቅምሻል።”

ያኒና “ገና ከአሁኑ መጽሐፍ ቅዱስን የማንበብ ፍላጎት አሳድረሽብኛል” አለቻት።

ዶሮታ ልጅዋን ለማሳከም ዶክተሯ ጋር በምትሄድበት ጊዜ ዘዴ በመጠቀምና በድፍረት ግሩም ምሥክርነት ሰጥታለች።​—⁠1 ጴጥሮስ 3:​15

[የግርጌ ማስታወሻ]

a ትክክለኛ ስሟ አይደለም።

b በይሖዋ ምሥክሮች የተዘጋጀ።