በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

“እርስ በርስ የሚፋቀሩና የሚተሳሰቡ ሰዎች”

“እርስ በርስ የሚፋቀሩና የሚተሳሰቡ ሰዎች”

“እርስ በርስ የሚፋቀሩና የሚተሳሰቡ ሰዎች”

እርስ በርሳችሁ ፍቅር ቢኖራችሁ፣ ደቀ መዛሙርቴ እንደ ሆናችሁ ሰዎች ሁሉ በዚህ ያውቃሉ።” (ዮሐንስ 13:35) ከኢየሱስ ቃላት ጋር በሚስማማ መልኩ ፍቅር የመጀመሪያዎቹ ክርስቲያኖች ተለይተው የሚታወቁበት ምልክት ነበር። ተርቱሊያን፣ ክርስቶስ ከሞተ ከአንድ መቶ ዓመታት በላይ ካለፉ በኋላ ‘ምን ያህል እንደሚዋደዱና አንዳቸው ለሌላው ለመሞት እንኳ ሳይቀር ዝግጁ እንደሆኑ ተመልከቱ’ ሲሉ ታዛቢዎች መናገራቸውን ጽፏል።

እንዲህ ዓይነት ፍቅር አሁንም በዓለም ላይ ሊገኝ ይችላል? አዎን። በብራዚል የሚገኘው የይሖዋ ምሥክሮች ቅርንጫፍ ቢሮ የደረሰው አንድ ደብዳቤ ለዚህ ምሳሌ ይሆነናል። ማሪሊያ የተባለች አንዲት ሴት እንዲህ ስትል ጽፋለች:-

“በቢያ መርሴቴስ፣ አርጀንቲና በነበርንበት ጊዜ እናቴ (የይሖዋ ምሥክር ናት) የአርትራይተስ በሽታ ይይዛታል፤ በሽታው ከወገቧ በታች ሽባ አድርጓት ነበር። ታምማ በተኛችባቸው በመጀመሪያዎቹ ስምንት ወራት በፍቅርና በአሳቢነት የተንከባከቧት በቢያ መርሴቴስ የነበሩ የይሖዋ ምሥክሮች ናቸው። ቤቷን ማጽዳትና ምግብ ማዘጋጀትን ጨምሮ አስፈላጊውን ነገር ሁሉ ያደርጉላት ነበር። እማዬ ሆስፒታል በነበረችበት ጊዜ እንኳ ቀንም ሆነ ማታ የሚያስታምማት ሰው ከአጠገቧ አይጠፋም ነበር።

“እኔና እማዬ ከዚያ በኋላ ወደ ብራዚል የመጣን ሲሆን አሁንም ገና ከሕመሟ እያገገመች ነው። አሁን በምንኖርበት ቦታ ያሉ የይሖዋ ምሥክሮች እማዬ ከበሽታዋ ቶሎ እንድትድን ለመርዳት የቻሉትን ሁሉ እያደረጉ ናቸው።”

ማሪሊያ እንዲህ ስትል ደብዳቤዋን ቋጭታለች:- “እኔ የይሖዋ ምሥክር አይደለሁም። ሆኖም የይሖዋ ምሥክሮች እርስ በርስ የሚፋቀሩና የሚተሳሰቡ ሰዎች መሆናቸውን ተመልክቻለሁ።”

አዎን፣ በዛሬውም ጊዜ እውነተኛ ክርስቲያናዊ ፍቅር የሚያሳዩ ሰዎች አሉ። በዚህ መንገድ ኢየሱስ የሰጣቸው ትምህርቶች በሕይወታችን ላይ ያላቸውን ኃይል ያሳያሉ።