በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

በቅርቡ ከወንጀል የጸዳ ዓለም ይመጣል

በቅርቡ ከወንጀል የጸዳ ዓለም ይመጣል

በቅርቡ ከወንጀል የጸዳ ዓለም ይመጣል

እስቲ ወንጀለኞች የሌሉበት ዓለም በአእምሮህ ለመሳል ሞክር! ፖሊሶች፣ ወኅኒ ቤቶች ወይም ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቁና የተወሳሰቡ የፍትሕ ሥርዓቶች አያስፈልጉም። እያንዳንዱ ሰው ለሌሎች ሕይወትና ንብረት አክብሮት ይኖረው ነበር። እንዲህ ዓይነቱ ዓለም የሕልም እንጀራ ነው? ምናልባት ሊመስልህ ይችላል፤ ሆኖም መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ዓይነት አስደናቂ ለውጥ እንደሚመጣ ተስፋ ይሰጣል። ቅዱሳን ጽሑፎች በዚህች ምድር ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎችንና ሌሎች መጥፎ ድርጊቶችን በተመለከተ ምን እንደሚሉ ለምን አትመረምርም?

በመዝሙር መጽሐፍ ውስጥ “በክፉዎች ላይ አትቅና፣ ዓመፃንም በሚያደርጉ ላይ አትቅና፤ እንደ ሣር ፈጥነው ይደርቃሉና፣ እንደ ለመለመ ቅጠልም ይረግፋሉና። ገሮች ግን ምድርን ይወርሳሉ፣ በብዙም ሰላም ደስ ይላቸዋል” የሚል ሐሳብ እናገኛለን። (መዝሙር 37:​1, 2, 11) አምላክ ይህንንም ሆነ ሌሎች የሚያበረታቱ ተስፋዎቹን እንዳይፈጽም ሊያግደው የሚችል ማንም የለም።

አምላክ እነዚህን ተስፋዎች የሚያስፈጽመው በመንግሥቱ አማካኝነት ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ በጌታ ጸሎት ላይ ይህ መንግሥት እንዲመጣና የአምላክ ፈቃድ ‘በሰማይ እንደሆነ በምድርም እንዲሆን’ እንዲጸልዩ ደቀ መዛሙርቱን አስተምሯቸዋል። (ማቴዎስ 6:​9, 10) በቅርቡ በዚህ መንግሥት አገዛዝ ሥር በድህነት፣ በጭቆና ወይም በራስ ወዳድነት ተነሳስቶ ወንጀል የሚፈጽም አይኖርም። በአንጻሩ የአምላክ ቃል “በምድሪቱ ላይ እህል ይትረፍረፍ፤ በተራሮችም ዐናት ላይ ይወዛወዝ” ይላል። (መዝሙር 72:​16 አ.መ.ት ) አዎን፣ ይሖዋ አምላክ በምድር ላይ ለሚኖሩት ሁሉ መልካም ነገሮችን አትረፍርፎ ይሰጣቸዋል። ከሁሉም በላይ ሰዎች ለአምላክና ለጎረቤታቸው ፍቅር ስለሚኖራቸው ከዚያ በኋላ በዓለም ላይ ፈጽሞ ወንጀል አይኖርም።