በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የአድናቆት ስሜት አለህ?

የአድናቆት ስሜት አለህ?

የአድናቆት ስሜት አለህ?

የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊዎች ስለ አምላክ ሥራዎችና ባሕርያት ሲናገሩ አድናቆታቸውን በተደጋጋሚ እንደሚገልጹ አስተውለሃል? መዝሙራዊው ዳዊት “ድንቅ ሆኜ ተፈጥሬአለሁና” በማለት ተናግሯል። (መዝሙር 139:14) ነቢዩ ኢሳይያስ ደግሞ “አቤቱ፣ አንተ አምላኬ ነህ፤ ድንቅን . . . አድርገሃልና ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ ስምህንም አመሰግናለሁ” ብሎ ነበር። (ኢሳይያስ 25:1) እንዲሁም ሐዋርያው ጳውሎስ “የእግዚአብሔር ባለ ጠግነትና ጥበብ እውቀቱም እንዴት ጥልቅ ነው” በማለት በአድናቆት እንደተናገረ ልብ በል።​—⁠ሮሜ 11:33

ዚ ኦክስፎርድ ኢንሳይክሎፒዲክ ኢንግሊሽ ዲክሽነሪ “መደነቅ” የሚለውን ቃል “ያልተጠበቀ፣ እንግዳ ወይም በቃላት ልንገልጸው የማንችለው ነገር ሲያጋጥመን የሚሰማን የመገረምና የማወቅ ጉጉት የተቀላቀለበት ስሜት” በማለት ይፈታዋል።

ትንንሽ ልጆች ለእነርሱ አዲስ የሆነ ነገር ሲያዩ፣ ሲሰሙ ወይም ሲያገኙ በአድናቆት ስሜት ዓይናቸውን ሲያፈጡ መመልከት አያስደስትህም? የሚያሳዝነው ግን አዲስ ወይም እንግዳ ነገር ከማየት የሚመነጨው እንዲህ ያለው የአድናቆት ስሜት በአብዛኛው ዕድሜ እየጨመረ ሲመጣ እየቀነሰ ይሄዳል።

ይሁን እንጂ ከላይ የተጠቀሱት የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊዎች ጥልቅ የአድናቆት ስሜት ነበራቸው። ይህ የአድናቆት ስሜታቸው በጊዜ ሒደት አልጠፋም። ለምን? በአምላክ ሥራዎች ላይ በማሰላሰል የአድናቆት ስሜታቸውን ስላዳበሩ ነው። መዝሙራዊው ዳዊት “የቀድሞውን ዘመን አስታወስሁ፤ ሥራህንም ሁሉ አሰላሰልሁ፤ የእጅህንም ሥራ አውጠነጠንሁ” በማለት ጸልዮአል።​—⁠መዝሙር 143:5 አ.መ.ት

በዚህ ዘመን ያሉ የአምላክ አገልጋዮችም እንዲህ ያለ የአድናቆት ስሜት ያላቸው መሆኑ በጣም የሚያስደስት ነው! አንተስ እንዲህ ያለ የአድናቆት ስሜት አለህ? ደግሞስ እያዳበርከው ነው?