በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

አምላክ ስለ እኛ ያስባል?

አምላክ ስለ እኛ ያስባል?

አምላክ ስለ እኛ ያስባል?

ከቤተሰብህ፣ ከጤንነትህና ከሥራህ ወይም ካሉብህ ሌሎች ከባድ ኃላፊነቶች ጋር በተያያዘ የሚያጋጥሙህ ችግሮች የስሜት ጫና እንዳስከተሉብህ ይሰማሃል? ብዙ ሰዎች እንደዚህ ይሰማቸዋል። ደግሞስ ዛሬ የፍትሕ መጓደል፣ ወንጀልና ዓመጽ ያልነካው ማን አለ? በእርግጥም ሁኔታው መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚናገረው ነው:- “ፍጥረት ሁሉ እስከ አሁን ድረስ አብሮ በመቃተትና በምጥ [ይኖራል]።” (ሮሜ 8:22) ብዙ ሰዎች ‘አምላክ ስለ እኛ ያስባል? እኛን ለመርዳት እርምጃ ይወስድ ይሆን?’ ብለው መጠየቃቸው ምንም አያስገርምም።

ጠቢቡ ንጉሥ ሰሎሞን ለአምላክ ባቀረበው ጸሎት ላይ “አንተ ብቻ የሰውን ልጆች ልብ ታውቃለህና” ብሏል። ሰሎሞን አምላክ እኛን ከማወቅም በላይ በግለሰብ ደረጃ እንደሚያስብልን እርግጠኛ ነበር። አምላክ ‘በሰማይ ሆኖ እንዲሰማ’ እንዲሁም እርሱን የሚፈራ እያንዳንዱ ግለሰብ “ሕመሙንና ኀዘኑን” በጸሎት ቢያቀርብ ሰምቶ እንዲመልስ ለምኖታል።—2 ዜና መዋዕል 6:29, 30

ዛሬም ቢሆን ይሖዋ አምላክ ስለ እኛ የሚያስብ ከመሆኑም በላይ ወደ እርሱ እንድንጸልይ ያበረታታናል። (መዝሙር 50:15) ከፈቃዱ ጋር ለሚስማሙ ከልብ የመነጩ ጸሎቶች ምላሽ እንደሚሰጥ ቃል ገብቷል። (መዝሙር 55:16, 22፤ ሉቃስ 11:5-13፤ 2 ቆሮንቶስ 4:7) በእርግጥም ይሖዋ ‘ማንም ሰው ወይም ሕዝቦቹ ጸሎትና ልመና ቢያደርጉ’ ይሰማል። በመሆኑም በአምላክ ከታመንን፣ እንዲረዳን ከጸለይንና ወደ እርሱ ከቀረብን ፍቅራዊ እንክብካቤውንና መመሪያውን እናገኛለን። (ምሳሌ 3:5, 6) የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊ የሆነው ያዕቆብ “ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ ወደ እናንተም ይቀርባል” የሚል ዋስትና ሰጥቶናል።—ያዕቆብ 4:8