በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

‘አምላክ እጅ በሠራው መቅደስ አይኖርም’

‘አምላክ እጅ በሠራው መቅደስ አይኖርም’

‘አምላክ እጅ በሠራው መቅደስ አይኖርም’

ሐዋርያው ጳውሎስ በሚስዮናዊ ጉዞው ወቅት በጎበኛቸው በአብዛኞቹ ከተሞች ውስጥ የአቴና ቤተ መቅደሶች ስለሚገኙ ለእርሱ እምብዛም አዲስ እንዳልነበሩ የታወቀ ነው። ኢንሳይክሎፒዲያ ብሪታኒካ እንደሚለው አቴና የምትታወቀው በጦርነትና በጥበብ አምላክነቷ ብቻ ሳይሆን “የእጅ ሙያዎች ብሎም በሰላሙ ወቅት የሚፈለጉ ክህሎቶች” አምላክ እንደሆነች ተደርጋ ነው።

ለአቴና ከተሠሩት ቤተ መቅደሶች ሁሉ በጣም ታዋቂው በስሟ በተሰየመችው በአቴንስ ከተማ የሚገኘው የፓርተኖን ቤተ መቅደስ ነው። ከጥንቱ ዓለም ታላላቅ ቤተ መቅደሶች መካከል የሚመደበው ፓርተኖን በውስጡ 12 ሜትር ቁመት ያለው ከወርቅና ከዝሆን ጥርስ የተሠራ የአቴና ሃውልት ይገኝበት ነበር። ጳውሎስ አቴንስን በጎበኘበት ወቅት ከነጭ እብነ በረድ የተሠራው ይህ ቤተ መቅደስ ለ500 ዓመታት ያህል በከተማዋ በጣም የታወቀ ሥፍራ ነበር።

ጳውሎስ አምላክ ሰው በሠራው ቤተ መቅደስ እንደማይኖር ለአቴንስ ነዋሪዎች የሰበከው በዚሁ ቤተ መቅደስ አቅራቢያ ነበር። (የሐዋርያት ሥራ 17:23, 24) ምናልባትም የጳውሎስ አድማጮች በዓይን ከማይታየው የማያውቁት አምላክ ይልቅ የአቴና ቤተ መቅደሶች ግርማ ሞገስ ወይም የምስሎቿ ውበት ይበልጥ ሳይማርካቸው አልቀረም። ይሁን እንጂ ጳውሎስ እንደገለጸው የሰው ልጆች ፈጣሪ “በሰው . . . የተቀረጸውን ወርቅ ወይም ብር ወይም ድንጋይ” ይመስላል ብሎ ማሰብ የማይመስል ነው።—የሐዋርያት ሥራ 17:29

በቤተ መቅደሶቻቸውና በምስሎቻቸው ውበት የሚከበሩት እንደ አቴና ያሉት አማልክት በአንድ ወቅት ብቅ ብለው ጠፍተዋል። በፓርተኖን ቤተ መቅደስ ለአቴና ቆሞ የነበረው ሐውልት በአምስተኛው መቶ ዘመን ከክርስቶስ ልደት በኋላ የጠፋ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ የሚገኘው የጥቂት ቤተ መቅደሶቿ ፍርስራሽ ብቻ ነው። በዛሬው ጊዜ ጥበብና መመሪያ ለማግኘት ወደ አቴና የሚጸልይ ማን አለ?

ማንም ሰው አይቶት የማያውቀው ‘የዘላለም አምላክ’ ይሖዋ ግን ከእነዚህ አማልክት በጣም የተለየ ነው። (ሮሜ 16:25, 26፤ 1 ዮሐንስ 4:12) የቆሬ ልጆች “ለዘላለም ይህ አምላካችን ነው፣ እርሱም ለዘላለም ይመራናል” በማለት ጽፈው ነበር። (መዝሙር 48:14) የይሖዋ አምላክን መመሪያ ማግኘት የሚቻልበት አንደኛው መንገድ ቃሉን መጽሐፍ ቅዱስን በማጥናትና በውስጡ የሚገኘውን ምክር በሥራ ላይ በማዋል ነው።