በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የታመሙ ሰዎች የሚፈወሱት በእምነታቸው ነው?

የታመሙ ሰዎች የሚፈወሱት በእምነታቸው ነው?

የታመሙ ሰዎች የሚፈወሱት በእምነታቸው ነው?

ሁላችንም ስንታመም ከሥቃያችን እፎይ የምንልበትን ጊዜ እንናፍቃለን። ኢየሱስ ክርስቶስ ሁሉንም ዓይነት በሽታዎች በመፈወስ ለብዙ ሕሙማን እፎይታ አስገኝቶላቸው እንደነበር የሚገልጹ በርካታ ታሪኮችን ከመጽሐፍ ቅዱስ ላይ አንብበህ ይሆናል። እነዚህ ሰዎች ሊፈወሱ የቻሉት እንዴት ነበር? መጽሐፍ ቅዱስ በአምላክ ኃይል እንደሆነ ይገልጽልናል። (ሉቃስ 9:42, 43፤ የሐዋርያት ሥራ 19:11, 12) ስለሆነም ሰዎቹን እንዲፈወሱ ያስቻላቸው እምነታቸው ብቻ ሳይሆን የአምላክ ቅዱስ መንፈስ ነበር። (የሐዋርያት ሥራ 28:7-9) ኢየሱስ የታመሙ ሰዎች ከሕመማቸው ለመፈወስ በእርሱ ማመናቸውን እንዲናገሩ የማይጠብቅባቸው ለዚህ ነበር።

‘ተአምራዊ ፈውስ ጊዜ ያለፈበት ነገር ነው? ወይስ ኢየሱስ ያከናወናቸው ዓይነት ፈውሶች ወደፊትም ይኖራሉ? በሕመም የሚሰቃዩ ወይም ሊድን በማይችል በሽታ የተያዙ ሰዎች ምን ተስፋ አላቸው?’ ብለህ ትጠይቅ ይሆናል።

አምላክ ጽድቅ በሚሰፍንበት አዲስ ዓለም ውስጥ ኢየሱስ ምድር ሳለ ያከናወናቸውን ዓይነት ተአምራዊ ፈውሶች እንደገና እንደሚፈጽም መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል። በአካባቢህ የሚኖሩ የይሖዋ ምሥክሮች አምላክ ሁሉንም ዓይነት በሽታዎች አልፎ ተርፎም ሞትን በማስቀረት ማንኛውም የእምነት ፈዋሽ ማከናወን የማይችለውን ፈውስ የሚፈጽመው እንዴትና መቼ እንደሆነ እንድታውቅ ሊረዱህ ፈቃደኞች ናቸው። አዎን፣ አምላክ “ሞትንም ለዘላለም ይውጣል።”—ኢሳይያስ 25:8