በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ከመጽሐፍ ቅዱስ ባገኘው እርዳታ ፈተናውን በድል ተወጣ

ከመጽሐፍ ቅዱስ ባገኘው እርዳታ ፈተናውን በድል ተወጣ

ከመጽሐፍ ቅዱስ ባገኘው እርዳታ ፈተናውን በድል ተወጣ

ይህ ዓለም በፈተና የተሞላ ነው። የመጽሐፍ ቅዱስን የሥነ ምግባር መስፈርቶች ጠብቆ መኖር እንዲህ ቀላል አይደለም። ለምሳሌ ያህል፣ “ከዝሙት ሽሹ” የሚለውን የመጽሐፍ ቅዱስ ምክር መከተል ፈታኝ ሊሆን ይችላል።—1 ቆሮንቶስ 6:18

ፖላንድ ውስጥ በሚገኝ የስካንዲኔቪያን ኩባንያ ውስጥ የሚሠራ አንድ የይሖዋ ምሥክር ንጹሕ አቋሙን ጠብቆ ለመኖር ትግል ጠይቆበት ነበር።

የሥራ ባልደረቦቹ የይሖዋ ምሥክር እንደሆነ ያውቃሉ። አለቆቹ ለትጋቱና ለመልካም ባሕርይው ያላቸውን አድናቆት ለመግለጽ የተለያዩ ኃላፊነቶችን ሰጡት። ይሁን እንጂ እነዚህ ኃላፊነቶች ከሥነ ምግባር ውጪ የሆኑ መዝናኛዎች ባሉባቸው ስብሰባዎች ላይ መገኘት እንደሚጨምሩ ተገነዘበ።

ብዙም ሳይቆይ ይህ ወንድም ከራሱ ጋር ሙግት ገጠመ። “አለቃዬ የይሖዋ ምሥክር መሆኔን ያውቃል። እምነት የጣለብኝና እነዚህን ሁሉ ኃላፊነቶች የሰጠኝም ለዚህ ነው። በስብሰባዎቹ ላይ አልገኝም ብል በስንት ችግር ያገኘሁትን ሥራዬን አጣለሁ። እንዲያው ታዛቢ ብቻ ሆኜ ብገኝስ?” ብሎ አሰበ።

ከዚያም ሌላም ነገር ማድረግ እንደሚጠበቅበት ተገነዘበ። ከውጭ አገር የሚመጡ ደንበኞቹን አብረዋቸው ከሚያድሩ ሴቶች ጋር በማገናኘት “ማስተናገድ” ነበረበት። ምን ያደርግ ይሆን?

ወንድም የጾታ ብልግናን በሚመለከት በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረተ አቋሙን ለአለቃው በድጋሚ ለመንገር ወሰነ። ብዙም ሳይቆይ ሥራው ለእርሱ እንደማይሆንና ውሎ አድሮ መልቀቅ እንደሚኖርበት ግልጽ ሆነ። ከዚያም አነስተኛ ደመወዝ ያለው ሆኖም ለሥነ ምግባር ፈተናዎች የማያጋልጥ አዲስ ሥራ አገኘ። አሁን ንጹሕ ሕሊናውን ጠብቆ ይኖራል።

አንድ ሰው በሥነ ምግባር ብልግና እንድትካፈል ወይም ዝም ብለህ እንድትመለከት ተጽዕኖ ቢያደርግብህ ምን ታደርጋለህ? ከእንዲህ ዓይነት ሁኔታ ለመሸሽ ወሳኝ እርምጃ ለመውሰድ ፈቃደኛ ነህ? በዘፍጥረት 39:7-12 ላይ ተመዝግቦ እንደሚገኘው በጥንት ዘመን የኖረው ዮሴፍ ያደረገው ይህንኑ ነበር።