በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የሰው ልጅ አምላክን ለማስደሰት ያለው ፍላጎት

የሰው ልጅ አምላክን ለማስደሰት ያለው ፍላጎት

የሰው ልጅ አምላክን ለማስደሰት ያለው ፍላጎት

“በአምላክ የሚያምን ኅብረተሰብ ያልነበረበት ዘመን የለም ለማለት ይቻላል፤ እንዲያውም አብዛኛውን ጊዜ የገዢነት ወይም የፈጣሪነት ቦታ ይሰጠዋል። በአምላክ መኖር በማያምኑ አገሮች ውስጥ እንኳ እንዲህ ያለው ሁኔታ ይታያል።” ጎድ—ኤ ብሪፍ ሂስትሪ በተባለው መጽሐፋቸው ላይ እንዲህ በማለት የተናገሩት ጆን ቦከር የተባሉ ደራሲ ናቸው። በዚህም ሆነ በዚያ አምላክን ለማግኘትና ሞገሱን ለማትረፍ የሚደረገው ጥረት የሰው ልጅ ስብዕና አንዱ ክፍል ሆኖ ቆይቷል። በዓለም ዙሪያ በርካታ ሰዎች አምላክን ለማስደሰት ከፍተኛ ፍላጎት አላቸው። እርግጥ አምላክን ለማስደሰት የሚጥሩበት መንገድ እንደ እምነታቸው ይለያያል።

አንዳንዶች አምላክን ለማስደሰት በሥነ ምግባር መልካም የሆነ አኗኗር መኖር ብቻ በቂ ነው ብለው ያምናሉ። ሌሎች ደግሞ ለድሆች መልካም በማድረግ የአምላክን ሞገስ ማግኘት እንደሚችሉ ይሰማቸዋል። ለሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓቶችና ክብረ በዓላት ትልቅ ቦታ የሚሰጡም በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች አሉ።

በሌላ በኩል ደግሞ አምላክ በጣም ሩቅ ነው ወይም በሌሎች ጉዳዮች ከመጠመዱ የተነሳ ለተራ ሰዎች ትኩረት አይሰጥም ብለው የሚያምኑ ሰዎች አሉ። ጥንታዊው የግሪክ ፈላስፋ ኤፊቆሮስ ‘አማልክት መልካምም ሆነ ክፉ ነገር ሊያደርጉብህ በማይችሉበት ሩቅ ቦታ ላይ ይገኛሉ’ ብሎ ያምን እንደነበር ይነገራል። ሆኖም እንዲህ ብለው ከሚያምኑት ውስጥ ብዙዎቹ ሃይማኖታዊ ዝንባሌ ያላቸው ናቸው። እንዲያውም አንዳንዶች በሕይወት የሌሉ የቀድሞ አባቶቻቸውን ሞገስ ለማግኘት በሚል መሥዋዕቶችን ያቀርባሉ፣ ሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓቶችንም ያከናውናሉ።

አንተስ በዚህ ጉዳይ ላይ ያለህ አመለካከት ምንድን ነው? አምላክ የእርሱን ሞገስ ለማግኘት የምናደርገውን ጥረት ልብ ብሎ ይመለከታል? አምላክን ማስደሰትስ እንችላለን?