በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ሌሎችን የሚጎዳ ነገር ከማድረግ መቆጠብ ብቻውን በቂ ነው?

ሌሎችን የሚጎዳ ነገር ከማድረግ መቆጠብ ብቻውን በቂ ነው?

ሌሎችን የሚጎዳ ነገር ከማድረግ መቆጠብ ብቻውን በቂ ነው?

“እንዲደረግባችሁ የማትፈልጉትን በሌሎች ላይ አታድርጉ።” ይህንን የግብረ ገብ መርሕ የተናገረው ታዋቂው ቻይናዊ መምህርና ፈላስፋ ኮንፊሽየስ ነው። ይህ አባባል ከተነገረ ወደ 2,500 ዓመታት ገደማ ያለፉ ቢሆንም በዛሬው ጊዜ የሚገኙ ብዙ ሰዎች አንድ ሰው ሌሎችን የሚጎዳ ነገር ከማድረግ ከተቆጠበ የሥነ ምግባር ግዴታውን እንደተወጣ ይሰማቸዋል።

ኮንፊሽየስ የሰጠው የግብረ ገብነት መመሪያ መልካም ጎን እንዳለው አይካድም። በሌላ በኩል መጽሐፍ ቅዱስ ደግሞ የሰብዓዊውን ኅብረተሰብ የእርስ በርስ ግንኙነትና ባሕርይ አስመልክቶ ተጨማሪ ሐሳብ ይሰጣል። መጽሐፍ ቅዱስ በሌሎች ላይ መጥፎ ነገር ማድረግ ብቻ ሳይሆን ትክክል እንደሆነ የምናውቀውን ነገር አለማድረግም ኃጢአት እንደሆነ ይገልጻል። ክርስቲያኑ ደቀ መዝሙር ያዕቆብ “መልካም የሆነውን ነገር ማድረግ እንዳለበት እያወቀ የማያደርግ ሰው ኀጢአት ያደርጋል” ሲል ጽፏል። (ያዕቆብ 4:17) ኢየሱስ ክርስቶስም ክርስቲያኖች ሌሎችን የሚጎዳ ነገር ከማድረግ እንዲቆጠቡ በመምከር ብቻ ሳይወሰን “ሌሎች እንዲያደርጉላችሁ የምትፈልጉትን ነገር እናንተም አድርጉላቸው” ብሏል።—ማቴዎስ 7:12

የአምላክ የመጀመሪያ ዓላማ ሰዎች ለራሳቸው እንዲደረግላቸው የሚፈልጉትን ነገር ለሌሎችም እንዲያደርጉ ነበር። ሰዎችን የፈጠረበት መንገድ ለሌሎች ደኅንነት እንደሚያስብ የሚያሳይ ግሩም ምሳሌ ነው:- “እግዚአብሔር ሰውን በራሱ መልክ ፈጠረው፤ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፤ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው።” (ዘፍጥረት 1:27) አምላክ በፍቅር ተነሳስቶ ኅሊና ሰጥቶናል፤ ሕሊናችንን በሚገባ ካሰለጠንነው ለእኛ እንዲደረግልን የምንፈልገውን ነገር ለሌሎችም እንድናደርግ ያነሳሳናል።

ዛሬ፣ የሌሎች አሳቢነት ማጣትና ራስ ወዳድነት ለችግር የዳረጋቸው ብዙ ሰዎች ካሉበት ሁኔታ መገላገል እንደሚችሉ ተስፋ የሚሰጥ ነገርም ሆነ እርዳታ ማግኘት አልቻሉም። በግልጽ ለመመልከት እንደሚቻለው መጥፎና ሌሎችን የሚጎዳ ነገር ከማድረግ መቆጠብ ብቻውን በቂ አይደለም፤ ሰዎችን የሚጠቅም መልካም ነገር ማድረግም ያስፈልጋል። በዚህም የተነሳ የይሖዋ ምሥክሮች ራሳቸውን በፈቃደኝነት በማቅረብ በአምላክ ቃል ውስጥ ስለሚገኘው ድንቅ ተስፋ ለሰዎች ለማስተማር ይጥራሉ። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለሚገኘው ምሥራች ለሰዎች የሚናገሩት ፍቅራዊ በሆነ መንገድ ሲሆን በዚህም ለራሳቸው እንዲደረግላቸው የሚፈልጉትን ለሌሎችም እንደሚያደርጉ ያሳያሉ።