በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መጸለይ ለችግሮችህ መፍትሔ ያስገኛል?

መጸለይ ለችግሮችህ መፍትሔ ያስገኛል?

መጸለይ ለችግሮችህ መፍትሔ ያስገኛል?

ከአቅሙ በላይ የሆነ ችግር አጋጥሞት የማያውቅ ማን አለ? ሐዋርያው ጳውሎስ እንደዚህ ዓይነት ሁኔታ በሚያጋጥመን ወቅት መጸለያችን እንደሚጠቅመን ያውቅ ነበር።

ጳውሎስ ያለ በቂ ምክንያት በሮም ታስሮ በነበረበት ወቅት የእምነት ባልንጀሮቹን እንዲጸልዩለት ከጠየቃቸው በኋላ አክሎ “በተለይም ወደ እናንተ በፍጥነት ተመልሼ እንድመጣ ትጸልዩልኝ ዘንድ ዐደራ እላችኋለሁ” ብሏል። (ዕብራውያን 13:18, 19) በሌላ ጊዜም በቶሎ እንዲለቀቅ ወንድሞቹ ላቀረቡት ጸሎት አምላክ መልስ እንደሚሰጥ ያለውን እምነት ገልጿል። (ፊልሞና 22) ብዙም ሳይቆይ ጳውሎስ ከእስር ተፈትቶ ወደ ሚስዮናዊነት ሥራው መመለስ ችሏል።

ይሁን እንጂ አንተ ላጋጠሙህ ችግሮች ጸሎት መፍትሔ ያስገኛል? ያስገኝ ይሆናል። ሆኖም ጸሎት እንዲያው በተለምዶ የሚደረግ ሃይማኖታዊ ሥርዓት እንዳልሆነ አስታውስ። በሰማይ ከሚኖረው አፍቃሪና ኃያል አባታችን ጋር የምንነጋገርበት መንገድ ነው። በጸሎታችን ዝርዝር ጉዳዮችን ለመጥቀስ ነጻነት ሊሰማን ይገባል፤ ከዚያም ይሖዋ የሚሰጠውን ምላሽ በትዕግሥት እንጠባበቅ።

አምላክ ለሁሉም ጸሎቶች ቀጥተኛ መልስ ላይሰጥ ይችላል፤ እንዲሁም ሁልጊዜ እኛ ባሰብነው መንገድ ወይም በጠበቅነው ጊዜ ምላሽ አይሰጠን ይሆናል። ለአብነት ያህል፣ ሐዋርያው ጳውሎስ ‘ስለ ሥጋው መውጊያ’ ደጋግሞ ጸልዮ ነበር። የጳውሎስ ችግር ምንም ይሁን ምን አምላክ አላስወገደለትም፤ ከዚህ ይልቅ “ጸጋዬ ይበቃሃል፤ ኀይሌ ፍጹም የሚሆነው በድካም ጊዜ ነውና” በማለት አጽናንቶታል።—2 ቆሮንቶስ 12:7-9

እኛም አምላክ አንድን ችግር ባያስወግድልንም እንኳ ‘ፈተናውን መታገሥ እንድንችል፣ መውጫ መንገዱን እንደሚያዘጋጅልን’ እርግጠኞች መሆን እንችላለን። (1 ቆሮንቶስ 10:13) በቅርቡ አምላክ የሰው ልጆችን ችግሮች በሙሉ ጠራርጎ ያስወግዳል። እስከዚያው ድረስ ግን ‘ጸሎትን ወደሚሰማው’ አምላክ መጸለያችን ይጠቅመናል።—መዝሙር 65:2