በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

“‘አዎን!’ ብለን መመለስ እንፈልጋለን”

“‘አዎን!’ ብለን መመለስ እንፈልጋለን”

“‘አዎን!’ ብለን መመለስ እንፈልጋለን”

በቅርቡ በናይጄሪያ የሚገኘው የይሖዋ ምሥክሮች ቅርንጫፍ ቢሮ አንድ ደብዳቤ ደረሰው። ደብዳቤው በከፊል እንዲህ ይነበባል:-

“ልጃችን አንደርሰን የሞተው የ14 ዓመት ልጅ እያለ ነበር። ከመሞቱ በፊት ሁለት ዶሮዎች ያረባ ነበር። ዶሮዎቹን ሸጦ ገንዘቡን ለዓለም አቀፉ የስብከት ሥራ አስተዋጽኦ እንዲሆን ለቅርንጫፍ ቢሮው የመላክ ፍላጎት ነበረው። ይሁን እንጂ ዶሮዎቹ አድገው ከመሸጣቸው በፊት ሞተ።

“እኛ ወላጆቹ ምኞቱን ለመፈጸም ዶሮዎቹን አሳድገን ሸጥናቸው። ገንዘቡን የአንደርሰን መዋጮ እንዲሆን ልከንላችኋል። ይሖዋ ቃል በገባልን መሠረት በጣም በቅርቡ አንደርሰንን ዳግመኛ ለማየት እንደምንታደል እርግጠኞች ነን። ምኞቱን ፈጽመንለት እንደሆነ ሲጠይቀን ‘አዎን!’ ብለን መመለስ እንፈልጋለን። በእርግጥም አንደርሰንን ብቻ ሳይሆን ትንሣኤ የሚያገኙትን ‘እንደ ደመና ያሉ ብዙ ምሥክሮችንም’ ለማየት እንናፍቃለን።”—ዕብራውያን 12:1፤ ዮሐንስ 5:28, 29

በዚህ ደብዳቤ ላይ በግልጽ እንደተቀመጠው ለእውነተኛ ክርስቲያኖች ብርታት የሚሰጣቸው በትንሣኤ ላይ ያላቸው ተስፋ ነው። በሚሊዮን የሚቆጠሩ ቤተሰቦች እንደ አንደርሰን ቤተሰብ የሰው ዘር ጠላት የሆነው ሞት የወሰደባቸውን የሚወዷቸውን ሰዎች በትንሣኤ ሲያገኟቸው ምንኛ ይደሰታሉ!—1 ቆሮንቶስ 15:24-26

መጽሐፍ ቅዱስ በአምላክ መንግሥት አገዛዝ ሥር በሚኖረው ጽድቅ የሰፈነበት ዓለም ከሚፈጸሙት በርካታ ድንቅ ነገሮች መካከል አንዱ የሆነውን ይህን የሚያጽናና የትንሣኤ ተስፋ ይዟል። (2 ጴጥሮስ 3:13) በዚያን ጊዜ አምላክ ለሰዎች ስለሚያደርግላቸው ነገር ሲናገር እንዲህ ይላል:- “እንባን ሁሉ ከዐይናቸው ያብሳል፤ ከእንግዲህ ወዲህ ሞት ወይም ሐዘን ወይም ልቅሶ ወይም ሥቃይ አይኖርም፤ የቀድሞው ሥርዐት ዐልፎአልና።”—ራእይ 21:4