በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የልጆች ጨዋታ ከጊዜ ማሳለፊያነት የበለጠ ጥቅም አለው

የልጆች ጨዋታ ከጊዜ ማሳለፊያነት የበለጠ ጥቅም አለው

የልጆች ጨዋታ ከጊዜ ማሳለፊያነት የበለጠ ጥቅም አለው

ልጆች መጫወት ይወዳሉ። ዘ ዴቨሎፒንግ ቻይልድ የተሰኘው መጽሐፍ እንደሚለው “ይህ ምንም እርባና የሌለው ከንቱ ነገር አይደለም። ልጁ በዙሪያው ስላለው ዓለም ያለው አመለካከት የሚገነባው በዚህ ወቅት በሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ላይ ተመሥርቶ ነው።” ልጆች በሚጫወቱበት ወቅት የስሜት ሕዋሳታቸውን መጠቀምን፣ በዙሪያቸው ያለውን ዓለም መረዳትንና ከሌሎች ጋር መግባባትን ይማራሉ።

ልጆች ከአራት ወይም ከአምስት ዓመት ዕድሜያቸው ጀምሮ የአዋቂዎችን ገጸ ባሕርይ ወክለው በተለምዶ “እቃ እቃ” የሚባለውን ጨዋታ መጫወት ይጀምራሉ። በአንድ ወቅት ኢየሱስ በጨዋታ ላይ ስላሉ ልጆች ተናግሯል። አንዳንዶች “ሠርግን” ሌሎች ደግሞ “ቀብርን” አስመስለው ለመጫወት ይፈልጋሉ። ብዙውን ጊዜ እንደሚያጋጥመው አንዱ የፈለገውን ጨዋታ ሌላው ለመጫወት ፈቃደኛ ሳይሆን ሲቀር አለመግባባት ይፈጠራል። (ማቴዎስ 11:16, 17) እንዲህ ዓይነት ጨዋታዎች እያንዳንዱ የኅብረተሰቡ ክፍል ያለውን ወሳኝ ሚና በልጆች ለጋ አእምሮ ውስጥ ለመቅረጽ ያስችላሉ።

በስዕሉ ላይ የምትመለከቷቸው ሕፃናት የመጽሐፍ ቅዱስ አስተማሪንና ተማሪን ገጸ ባሕርይ ወክለው እየተጫወቱ ነው። ይህ እውነተኛ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ባይሆንም የመጽሐፍ ቅዱስን መልእክት ለሌሎች የማካፈሉ አስፈላጊነት በአእምሯቸው ውስጥ መቀረጹን ያሳያል። ይህ ደግሞ በጣም አስፈላጊ ትምህርት ነው፤ ምክንያቱም ኢየሱስ ተከታዮቹን በሙሉ ደቀ መዛሙርት እንዲያደርጉና ያዘዛቸውን ሁሉ እንዲጠብቁ ሰዎችን እንዲያስተምሯቸው አዟቸዋል።—ማቴዎስ 28:19, 20

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት እንደሚመሩ፣ ንግግር እንደሚያቀርቡ ወይም ከቤት ወደ ቤት እንደሚሰብኩ እያስመሰሉ የሚጫወቱ ልጆች ያሏቸው ወላጆች ሊኮሩ ይገባቸዋል። ልጆች በተፈጥሯቸው በዙሪያቸው ያሉ አዋቂዎች ሲያደርጉ የሚያዩትን ይኮርጃሉ። ልጆች የሚጫወቷቸው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጨዋታዎች “በጌታ ዘንድ ተቀባይነት ባለው ትምህርትና ምክር” ተኮትኩተው ማደጋቸውን ያሳያሉ።—ኤፌሶን 6:4 ቻርልስ ቢ ዊሊያምስ ትርጉም

ይሖዋ፣ ልጆች በእውነተኛው አምልኮ ውስጥ ቦታ እንዲኖራቸው ይፈልጋል። ሕጉ በሚነበብበት ወቅት “ልጆችን” ጭምር እንዲሰበስብ ለሙሴ ነግሮት ነበር። (ዘዳግም 31:12) ትናንሽ ልጆች በእውነተኛው አምልኮ ውስጥ ቦታ እንዳላቸው የሚሰማቸው ከሆነ ይህ በሚጫወቷቸው ጨዋታዎች ላይ ይንጸባረቃል። የአምላክ አገልጋይ እንደሆነ አስመስሎ የሚጫወት ልጅ የአምላክ አገልጋይ ለመሆን የመጀመሪያውን እርምጃ ወስዷል ለማለት ይቻላል።