በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ባለን ያለመርካት አባዜ

ባለን ያለመርካት አባዜ

ባለን ያለመርካት አባዜ

“ለምንፈልጋቸው ነገሮች ገደብ ካላበጀን በቃኝ የምንለው ነገር አይኖርም።”—የዎርልድዎች ኢንስቲትዩት ሪፖርት።

“ም እንፈልጋለን? ሁሉንም ነገር። መቼ ነው የምንፈልገው? አሁኑኑ።” ይህ መፈክር በ1960ዎቹ ዓመታት በአንዳንድ የኮሌጅ ተማሪዎች ዘንድ በጣም የተስፋፋ ነበር። በጊዜያችን እነዚህ ቃላት ሲነገሩ አንሰማ ይሆናል፤ አንድምታው ግን አሁንም አለ። በእርግጥም ባለን ያለመርካት አባዜ የዘመናችን ልዩ ምልክት የሆነ ይመስላል።

ብዙዎች ሃብትና ንብረት የማካበቱን ጉዳይ በሕይወታቸው ውስጥ ዋነኛውን ቦታ ሰጥተውታል። የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት የነበሩት ጂሚ ካርተር በአንድ ወቅት “የሰው ማንነቱ የሚለካው ባከናወናቸው ነገሮች መሆኑ ቀርቶ ባለው ሃብት እየሆነ መጥቷል” በማለት ተናግረዋል። ይሁን እንጂ ከሃብት የበለጠ ዋጋ ያላቸው ነገሮች ይኖሩ ይሆን? ካሉስ ምንድን ናቸው? ምን ጥቅምስ ያስገኛሉ?