የምታነበውን በአእምሮህ መሳል ትችላለህ?
የምታነበውን በአእምሮህ መሳል ትችላለህ?
ስለምታነባቸው ቦታዎች የተወሰነ ግንዛቤ ማግኘትህ ታሪኩን በአእምሮህ ለመሳል ይረዳሃል። ለምሳሌ ያህል፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል በሆነው በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ውስጥ የተጠቀሱትን የሐዋርያው ጳውሎስ ሚስዮናዊ ጉዞዎች እንመልከት። በመጀመሪያው ሚስዮናዊ ጉዞው ወቅት የኢየሱስ ተከታዮች ክርስቲያኖች የሚለውን ስማቸውን ካገኙበት ከአንጾኪያ ተነሳ። ከዚያም ወደ ስልማና፣ በጲስድያ ወደምትገኘው አንጾኪያ፣ ወደ ኢቆንዮን፣ ወደ ልስጥራንና ወደ ደርቤን ተጉዟል። እነዚህ ቦታዎች የት እንደነበሩ ለመገመት ትችላለህ?
ምናልባት ካርታ ከሌለህ ሊያስቸግርህ ይችላል። በቅርቡ በወጣው ‘መልካሚቱን ምድር ተመልከት ’ በተሰኘው አዲስ ባለ 36 ገጽ ብሮሹር ውስጥ እነዚህን ቦታዎች የሚያሳይ ካርታ ተካትቷል። በዩናይትድ ስቴትስ፣ ሞንታና ግዛት የምትኖር አንዲት አንባቢ ለብሮሹሩ ያላትን አድናቆት ስትገልጽ እንዲህ ብላለች:- “ጳውሎስ የተጓዘበትን አቅጣጫ ማየትና የተጠቀመበትን መጓጓዣ እንዲሁም እርሱና ሌሎች ቀደምት ክርስቲያኖች ምሥራቹን በማስፋፋት ያከናወኑትን ሥራ በአእምሮዬ መሳል እችላለሁ። ይህን የመሰለ ግሩም የማጥኛ ካርታ ስላዘጋጃችሁ ላመሰግናችሁ እወዳለሁ።”
ስለ ጳውሎስ ጉዞዎች የሚያሳየው ካርታ አንባቢዎች የመጽሐፍ ቅዱስን ዘገባዎች በአእምሯቸው መሳል እንዲችሉ ከሚረዷቸው በርካታ ካርታዎች መካከል አንዱ ብቻ ነው። እርስዎም ‘መልካሚቱን ምድር ተመልከት ’ የተባለው ብሮሹር አንድ ቅጂ እንዲላክልዎ የሚፈልጉ ከሆነ ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተው በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ ወይም በዚህ መጽሔት በገጽ 2 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው መላክ ይችላሉ።
□ ‘መልካሚቱን ምድር ተመልከት ’ የተባለውን ብሮሹር አንድ ቅጂ ላኩልኝ። በየትኛው ቋንቋ እንደሚፈልጉ ይጥቀሱ።
□ መጽሐፍ ቅዱስን መማር ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።
[በገጽ 32 ላይ የሚገኝ የሥዕል ምንጭ]
Pictorial Archive (Near Eastern History) Est.