በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

አስተማማኝ ሕይወት የምናገኝበት ዘመን ይመጣ ይሆን?

አስተማማኝ ሕይወት የምናገኝበት ዘመን ይመጣ ይሆን?

አስተማማኝ ሕይወት የምናገኝበት ዘመን ይመጣ ይሆን?

ልጆች አፍቃሪ ከሆኑ ወላጆቻቸው ጋር እየተጫወቱ ሲፈነድቁ መመልከት የማያስደስተው ማን አለ? ልጆቹ አሳቢ ከሆኑት ወላጆቻቸው ጋር እስካሉ ድረስ ፍጹም ተረጋግተው ይጫወታሉ። የሚያሳዝነው ግን ብዙ ልጆች እንደዚህ ያለ አስደሳች ጊዜ የማሳለፍ አጋጣሚ አያገኙም። ከዚህ በተቃራኒ አንዳንድ ልጆች በየዕለቱ ማደሪያ ፍለጋ ይንከራተታሉ። እንደነዚህ ያሉት የጐዳና ተዳዳሪ ልጆችና ሕይወታቸው አስተማማኝ ያልሆነ ሌሎች ሰዎች ተስፋ ይኖራቸው ይሆን?

የወደፊቱ ጊዜ የጨለመ ቢመስልም የአምላክ ቃል ተስፋ ይሰጣል። ነቢዩ ኢሳይያስ ሁሉም ሰው አስተማማኝ ሕይወት የሚያገኝበት ጊዜ እንደሚመጣ በትንቢት ሲናገር እንዲህ በማለት ጽፏል:- “ሰዎች ቤት ይሠራሉ፤ በውስጡም ይኖራሉ፤ ወይንን ይተክላሉ፤ ፍሬውንም ይበላሉ። ከእንግዲህ ለሌሎች መኖሪያ ቤት አይሠሩም፤ ወይም ሌላው እንዲበላው አይተክሉም።”—ኢሳይያስ 65:21, 22

ሆኖም ይህ ተስፋ እምነት ሊጣልበት የሚችል ነው? ለነገሩ “ተስፋ” የሚለው ቃል በራሱ ሁልጊዜ የተረጋገጠ ነገርን አያመለክትም። ለምሳሌ ያህል፣ በብራዚል ተዘውትሮ የሚሰማ “ኣ ኢስፔራንሳ ኢ ኣ ኡልቲማ ኪ ሞር” የሚል አባባል አለ። ቃል በቃል ሲተረጎም “ተስፋ እስከ መጨረሻው አይሞትም” ማለት ሲሆን ብዙ ሰዎች ተስፋ ለማድረግ የሚያስችል በቂ ምክንያት ባይኖርም እንኳ ተስፋ እንደማይቆርጡ የሚጠቁም ነው። ይሁን እንጂ ሕያው የሆነው አምላክ የሰጠን ተስፋ ከዚህ የተለየ ነው። ሐዋርያው ጳውሎስ “[በአምላክ] የሚያምን ሁሉ አያፍርም” ሲል ጽፏል። (ሮሜ 10:11) ከዚህ ቀደም ፍጻሜያቸውን ያገኙ የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶች ይሖዋ አምላክ የሚሰጣቸው ተስፋዎች በሙሉ ፍጻሜያቸውን እንደሚያገኙ ያረጋግጡልናል። እነዚህ ተስፋዎች ሲፈጸሙ ልጆችን የጎዳና ተዳዳሪዎች እንዲሆኑ የሚያስገድዷቸው ሁኔታዎችም ይወገዳሉ።

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙት ተግባራዊ ሊሆኑ የሚችሉ ምክሮች በዛሬው ጊዜም እንኳ ተስፋ አስቆራጭ በሆነ ሁኔታ ውስጥ የሚኖሩ ሰዎችን የተሻለና አስተማማኝ ሕይወት እንዲመሩ ይረዷቸዋል። ይህ የሚሆነው እንዴት ነው? በአካባቢህ የሚገኙ የይሖዋ ምሥክሮች ለዚህ ጥያቄ መልስ እንድታገኝ ሊረዱህ ፈቃደኞች ናቸው።