በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

‘ባገኘሁት ሥልጠና ተደስቻለሁ’

‘ባገኘሁት ሥልጠና ተደስቻለሁ’

‘ባገኘሁት ሥልጠና ተደስቻለሁ’

ወጣቷ ካዙና አስተማሪዋ በእንግሊዝኛ ቋንቋ ንግግር የማቅረብ ውድድር ላይ እንድትካፈል ሲጠይቃት በጣም ደነገጠች። በስተ ሰሜን በሚገኘው ሆካይዶ በተባለ የጃፓን ትልቅ ደሴት ውስጥ ያሉ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በሙሉ እንዲህ ባለው ውድድር መካፈል ይችሉ የነበረ ቢሆንም ካዙና የምትማርበት ትምህርት ቤት ከዚያ በፊት ተማሪዎቹን በውድድሩ እንዲካፈሉ አድርጎ አያውቅም። በውድድሩ ዕለት ካዙና 50 ከሚያህሉ ተማሪዎች ጋር እንደምትወዳደር ስታውቅ በጣም ተጨንቃ ነበር። በተለይ አፍ መፍቻ ቋንቋቸው እንግሊዝኛ የሆነ ሁለት ዳኞች በተመለከተች ጊዜ ይበልጥ ተደናገጠች።

ከውድድሩ በኋላ ዝቅተኛውን ሽልማት ካገኘው ተማሪ አንስቶ የአሸናፊዎቹ ስም ይጠራ ጀመር። ካዙና ስሟ መጨረሻ ላይ ሲጠራ ማመን አቃታት። አጠገቧ ተቀምጦ ከነበረው አስተማሪዋ ጋር በግርምት ተያዩ። ድንጋጤው ባይለቃትም ወደ መድረኩ ሄዳ አንደኛ ለሚወጣው ተማሪ የተዘጋጀውን ሽልማት ተቀበለች!

ካዙና በደስታ ስሜት “ለዚህ ውጤት የበቃሁት የይሖዋ ድርጅት ባዘጋጀው ቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ባገኘሁት ሥልጠና አማካኝነት ነው” ብላለች። አክላም “ይህን ሥልጠና በማግኘቴ በጣም ተደስቻለሁ” በማለት ተናግራለች። ካዙና ገና ከልጅነቷ አንስቶ የተካፈለችበት ይህ ትምህርት ቤት የይሖዋ ምሥክሮች ከሚያደርጓቸው ስብሰባዎች መካከል አንዱ ነው። ለውድድሩ ስትዘጋጅ ስለ ማይክሮፎን አጠቃቀም፣ በግለትና በቅንዓት ስለ መናገር፣ ስለ አካላዊ መግለጫዎች፣ አድማጮችን ቀና እያሉ ስለ መመልከት እንዲሁም ስለ ሌሎች ጉዳዮች ከቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ላገኘችው ትምህርት ትኩረት ሰጥታ ነበር።

በአካባቢህ በሚገኝ የይሖዋ ምሥክሮች የመንግሥት አዳራሽ የሚሰጠውን ይህን ትምህርት ሄደህ እንድታይ እንጋብዝሃለን። ይህ ትምህርት ቤት ወጣቶችንም ሆነ በዕድሜ የገፉትን እንዴት እንደሚጠቅም በዓይንህ ተመልከት። ማንም ሰው በስብሰባው ላይ መገኘት ይችላል። ስለ ትምህርት ቤቱ የበለጠ መረጃ ለማግኘት እባክህ በቅርብ የምታገኛቸውን የይሖዋ ምሥክሮች አነጋግር።