በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መልካም ምግባር ‘የአምላክን ትምህርት ያስመሰግናል’

መልካም ምግባር ‘የአምላክን ትምህርት ያስመሰግናል’

መልካም ምግባር ‘የአምላክን ትምህርት ያስመሰግናል’

በሩሲያ የክራስነያርስክ ከተማ ነዋሪ የሆነችው ወጣቷ ማሪያ ግሩም የመዘመር ችሎታ ስላላት አስተማሪዋ በትምህርት ቤቱ የመዝሙር ክበብ ውስጥ እንድትሳተፍ አደረገቻት። ከትንሽ ጊዜ በኋላ ማሪያ ወደ አንዲት አስተማሪ በመቅረብ ከመዝሙሮቹ መካከል አንዳንዶቹን ለመዘመር እንደማትፈልግ በአክብሮት ገለጸችላት። ለምን? ምክንያቱም ሃይማኖታዊ ይዘት ያላቸውን መዝሙሮች መዘመር ከመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ከተማረችው እውነት ጋር ስለሚቃረን ነበር። አስተማሪዋ በመገረም ‘አምላክን በዝማሬ ማወደሱ ምን ስህተት አለው?’ ስትል ጠየቀቻት።

ማሪያ ሥላሴን የሚያወድሱ መዝሙሮች ለመዘመር ፈቃደኛ ያልሆነችበትን ምክንያት ለማስረዳት መጽሐፍ ቅዱስ እየጠቀሰች አምላክና ኢየሱስ የተለያዩ አካላት እንደሆኑ፤ እንዲሁም መንፈስ ቅዱስ የአምላክ ኃይል መሆኑን አብራራችላት። (ማቴዎስ 26:39፤ ዮሐንስ 14:28፤ የሐዋርያት ሥራ 4:31) ማሪያ “ከመምህሬ ጋር የነበረኝ ሰላማዊ ግንኙነት አልሻከረም። ሁሉም አስተማሪዎቻችን ለማለት ይቻላል በጣም ጥሩዎች ናቸው። የሚሰማንን እንድንናገር ያበረታቱናል” ብላለች።

ማሪያ የወሰደችው አቋም የትምህርት ዓመቱ እስኪጠናቀቅ ድረስ ከአስተማሪዎቿና አብረዋት ከሚማሩት ልጆች አክብሮት አስገኝቶላታል። ማሪያ ስለ ሁኔታው እንዲህ ትላለች:- “መጽሐፍ ቅዱሳዊ መመሪያዎችን ተግባራዊ ማድረጌ ጠቅሞኛል። ትምህርት ቤት ሊዘጋ ሲል ታማኝና ሥርዓታማ ለሆኑ ተማሪዎች የሚሠጠውን ሽልማት አግኝቻለሁ። ወላጆቼ ደግሞ ልጃቸውን በጥሩ ሁኔታ በማሳደጋቸው የምስጋና ደብዳቤ ተቀብለዋል።”

ማሪያ በነሐሴ 18, 2001 የተጠመቀች ሲሆን “ድንቅ አምላክ የሆነውን ይሖዋን ለማገልገል በመቻሌ ደስተኛ ነኝ!” ስትል ትናገራለች። በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ወጣት የይሖዋ ምሥክሮችም በቲቶ 2:9, 10 (የ1954 ትርጉም) ላይ የሚገኘውን “ስለ መድኃኒታችን ስለ እግዚአብሔር የሚሆነውን ትምህርት በሁሉ ነገር ያስመ[ስ]ግኑ” የሚለውን ምክር ይታዘዛሉ።

[በገጽ 32 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

ማሪያ በተጠመቀች ጊዜ ከወላጆቿ ጋር

[በገጽ 32 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

የምስጋና ደብዳቤና የመልካም ምግባር የምስክር ወረቀት