ሊታወስ የሚገባው ክንውን
ሊታወስ የሚገባው ክንውን
ክንውን ምንድን ነው? ወደ 2,000 ከሚጠጉ ዓመታት በፊት የሞተ የአንድ ሰው መታሰቢያ ነው። ይህ ሰው “መልሼ ለማንሳት ሕይወቴን አሳልፌ [እሰጣለሁ]” እንዲሁም “ሕይወቴን በራሴ ፈቃድ አሳልፌ እሰጣለሁ እንጂ ከእኔ ማንም አይወስዳትም” በማለት የተናገረው ኢየሱስ ክርስቶስ ነበር።—ዮሐንስ 10:17, 18
ኢየሱስ ተከታዮቹ የሞቱን መታሰቢያ በዓል እንዲያከብሩ አዝዟቸው ነበር። ይህ በዓል ‘የጌታ እራት’ ተብሎም ይጠራል። (1 ቆሮንቶስ 11:20) የይሖዋ ምሥክሮችና ተባባሪዎቻቸው ኢየሱስ ሞቱን ለማስታወስ ያቋቋመውን የመታሰቢያ በዓል ሐሙስ መጋቢት 24, 2005 ፀሐይ ከጠለቀች በኋላ ያከብራሉ።
በበዓሉ ላይ የሚቀርበው ያልቦካ ቂጣም ሆነ ቀይ ወይን ምን ትርጉም እንዳለው የሚያብራራ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ንግግር ይኖራል። (ማቴዎስ 26:26-28) በንግግሩ ላይ እንደሚከተሉት ያሉ ጥያቄዎችም መልስ ያገኛሉ:- ክርስቲያኖች በዓሉን በየስንት ጊዜ ሊያከብሩት ይገባል? ከቂጣውና ከወይኑ የመካፈል መብት ያላቸው እነማን ናቸው? ከኢየሱስ ሞት ጥቅም የሚያገኙት እነማን ናቸው? ይህ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው በዓል ኢየሱስ በምድር ላይ የኖረበትንና በኋላም ሕይወቱን በሞት አሳልፎ የሰጠበትን ምክንያት ሁሉም ሰው እንዲገነዘብ ያስችላል።
እርስዎም በኢየሱስ ሞት መታሰቢያ በዓል ላይ እንዲገኙ ሞቅ ያለ ግብዣ ቀርቦልዎታል። በዓሉ የሚከበርበትን ቦታና ሰዓት ለማወቅ በአካባቢዎ የሚገኙ የይሖዋ ምሥክሮችን መጠየቅ ይችላሉ።