በመቄዶንያ የሚገኙትን መርዳት
በመቄዶንያ የሚገኙትን መርዳት
“ወደ መቄዶንያ ተሻግረህ ርዳን።” (የሐዋርያት ሥራ 16:9) ለሐዋርያው ጳውሎስ በራእይ የታየው ሰው ያቀረበው ይህ ልመና የአምላክ መንግሥት ምሥራች ባልተሰበከበት ክልል ማለትም በአሁኗ ግሪክ ውስጥ በሚገኙ ከተሞች መታወጅ እንዳለበት የሚጠቁም ነበር።
በአሁኗ መቄዶንያ ከ1,840 ነዋሪዎች አንዱ የይሖዋ ምሥክር ነው። አብዛኞቹ ሰዎች ስለ ይሖዋ አምላክ ፈጽሞ ሰምተው አያውቁም። በእርግጥም የዚህች አገር ነዋሪዎች የሰላሙን መልእክት እንዲሰሙ አስቸኳይ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል።—ማቴዎስ 24:14
በኅዳር 2003፣ ይሖዋ አምላክ እነዚህ ሰዎች እርዳታ ማግኘት የሚችሉበትን መንገድ ከፍቷል። በዚህ ወር አንድ ቀን በስኮፕዬ የሚገኘው የመቄዶንያ የይሖዋ ምሥክሮች ቢሮ ያልተጠበቀ የስልክ ጥሪ ደረሰው። ስልኩ የተደወለው ከመቄዶንያ ዓለም አቀፍ ትብብር ማዕከል ሲሆን ምሥክሮቹ ከኅዳር 20 ጀምሮ ለሦስት ቀናት በሚቆየው ትርኢት ላይ ተገኝተው ስለ እምነታቸው ለመግለጽ የሚያስችላቸው ዝግጅት እንዲያደርጉ ጥሪ ቀረበላቸው። የመንግሥቱን ምሥራች ጨርሶ ሰምተው የማያውቁ በሺህ የሚቆጠሩ ሰዎችን ለማግኘት የሚያስችል እንዴት ያለ ግሩም አጋጣሚ ነው!
ፈቃደኛ የሆኑ የይሖዋ ምሥክሮች በመቄዶንያ ቋንቋ የሚገኙትን በይሖዋ ድርጅት የተዘጋጁ የተለያዩ ጽሑፎች ለማሰባሰብና ለመደርደር በትጋት ሠርተዋል። ጎብኚዎች ለራሳቸው ቅጂ ማግኘት ከፈለጉ ለመውሰድ እንዲችሉ ጽሑፎቹ ለእይታ ቀርበው ነበር። እነዚህ ጽሑፎች ብዙዎች በመንፈሳዊ የሚያድስ ውኃ በነጻ እንዲያገኙ አስችለዋቸዋል።—ራእይ 22:17
የጎብኚዎቹን ትኩረት ይበልጥ የሳቡት ወጣቶች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎችና ተግባራዊ መሆን የሚችሉ መልሶች እንዲሁም ለቤተሰብ ደስታ ቁልፉ ምንድን ነው? እንደሚሉት ያሉ በሕይወታቸው ዙሪያ ያተኮሩ ጉዳዮችን የሚዳስሱ ጽሑፎች ነበሩ።* ዘጠና ስምንት የሚያህሉ ሰዎች የይሖዋ ምሥክሮች መጥተው እንዲጠይቋቸው አድራሻቸውን ሰጥተዋል። በተጨማሪም በርካታ ሰዎች የይሖዋ ምሥክሮች ለሚሠሩት መልካም ሥራና ለጽሑፉ ጥራት ያላቸውን አድናቆት የሚገልጹ አስተያየቶች ሰጥተዋል።
አንድ ሰው ትንሽ ልጁን ይዞ ጽሑፎች ለእይታ ወደቀረቡበት ቦታ መጣና ለልጆች ተብሎ የተዘጋጀ ጽሑፍ እንዳለ ጠየቀ። ምሥክሮቹ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ* የሚለውን መጽሐፍ አሳዩት። አባትየው አገላብጦ ከተመለከተው በኋላ በጣም በመደሰት ዋጋው ስንት እንደሆነ ጠየቀ። የይሖዋ ማቴዎስ 10:8) መጽሐፉን ለልጁ እያሳየው “እንዴት ደስ የሚል መጽሐፍ ነው! በየቀኑ ከዚህ መጽሐፍ አንድ ታሪክ አነብልሃለሁ!” አለው።
ምሥክሮች የማስተማር ሥራ በፈቃደኝነት በሚደረግ መዋጮ እንደሚደገፍ ሲሰማ ይበልጥ ተደሰተ። (አንድ የፍልስፍና ፕሮፌሰርም ለእይታ የቀረቡ በርካታ ጽሑፎች ወደሚገኙበት ቦታ መጡ። እኚህ ሰው በአጠቃላይ ስለ ሃይማኖት በተለይ ደግሞ ስለ ይሖዋ ምሥክሮች እምነት ለማወቅ ይፈልጋሉ። ፕሮፌሰሩ የሰው ዘር አምላክን ለማግኘት ያደረገው ፍለጋ* (እንግሊዝኛ) የተባለውን መጽሐፍ ገለጥ ገለጥ አድርገው እየተመለከቱ እንዲህ አሉ:- “በጣም ምክንያታዊ በሆነ መንገድ የተዘጋጀ መጽሐፍ ነው! ነጥቦቹም ልክ እኔ በማስበው መንገድ ቀርበዋል።” ከዚያም ፕሮፌሰሩ በሚያስተምሩበት ትምህርት ቤት የሚማሩ አንዳንድ ተማሪዎች ጽሑፎቹ ወዳሉበት ቦታ መጥተው መምህሩ የወሰዱትን መጽሐፍ እያንዳንዳቸው ማግኘት ይችሉ እንደሆነ ጠየቁ። አስተማሪያቸው የወሰዱትን መጽሐፍ በትምህርት ክፍለ ጊዜያቸው ሊጠቀሙበት እንደሚችሉ ስለተሰማቸው መጽሐፉን ማጥናት ፈልገው ነበር።
አንዳንዶች በዚህ ትርኢት አማካኝነት ለመጀመሪያ ጊዜ ቅዱስ ጽሑፋዊ እውነቶችን ለማንበብም ሆነ ለመስማት አጋጣሚ አግኝተዋል። መስማት የተሳናቸው የተወሰኑ ወጣቶች ሰብሰብ ብለው ጽሑፎቹን ለማየት መጡ። አንድ ምሥክር አንዲት ልጅ ወደ ምልክት ቋንቋ እየተረጎመችለት ለወጣቶቹ አጭር ንግግር አደረገላቸው። እስከ ዛሬ ከኖሩት ሁሉ የሚበልጠው ታላቅ ሰው a ከተባለው መጽሐፍ ላይ ሥዕሎቹን በማሳየት ኢየሱስ የታመሙትን እንዲሁም መስማት የማይችሉ ሰዎችን እንደፈወሰ ነገራቸው። ኢየሱስ በአሁኑ ጊዜ በምድር ለሚኖሩት ሰዎችም በቅርቡ ተመሳሳይ ነገር እንደሚያደርግላቸው የሚናገረውን የመጽሐፍ ቅዱስ ተስፋ “ሲሰሙ” በጣም ተደሰቱ። ብዙዎቹ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረቱትን ጽሑፎች ደስ ብሏቸው የወሰዱ ሲሆን የምልክት ቋንቋ የሚችል የይሖዋ ምሥክር እንዲጎበኛቸውም ዝግጅት ተደርጓል።
ከመቄዶንያ ቋንቋ በተጨማሪ በአልባኒያ፣ በእንግሊዝኛና በቱርክ ቋንቋዎች ጽሑፎች ቀርበው ነበር። የመቄዶንያ ቋንቋ መናገር የማይችል አንድ ሰው የእንግሊዝኛ ጽሑፎችን ጠይቆ መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶችን ከወሰደ በኋላ የቱርክ ቋንቋ መናገር እንደሚችል ነገራቸው። በራሱ ቋንቋ የተዘጋጀውን ጽሑፍ ባሳዩት ጊዜ ዓይኑን ማመን አቃተው! የይሖዋ ምሥክሮች ሁሉንም ሰዎች ለመርዳት እንደሚፈልጉም ተገነዘበ።
በዚህ ዝግጅት አማካኝነት በጣም ግሩም ምሥክርነት ለመስጠት ከመቻሉም በላይ ብዙ ሰዎች ለመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ፍላጎት ማሳየታቸው በእርግጥም በጣም የሚያበረታታ ነው! አዎን፣ ይሖዋ የመንግሥቱን ምሥራች በመቄዶንያ ይበልጥ እንዲዳረስ መንገዱን ከፍቷል።
[የግርጌ ማስታወሻዎች]
a ሁሉም የተዘጋጁት በይሖዋ ምሥክሮች ነው።
[በገጽ 8 ላይ የሚገኝ ሣጥን/ሥዕል]
ጉልህ ስፍራ የሚሰጠው ክንውን!
ግንቦት 17, 2003 በመቄዶንያ የአምላክን መንግሥት ምሥራች ለሰው ሁሉ ለማዳረስ በሚደረገው ጥረት ረገድ ከፍተኛ እገዛ የሚያደርግ ክንውን ተፈጽሟል። በዚህ ቀን በስኮፕዬ የይሖዋ ምሥክሮች ቢሮ ተወስኗል። የግንባታው ሥራ ለመጠናቀቅ ሁለት ዓመታት የፈጀ ሲሆን የበፊቱን ሕንፃ በአራት እጥፍ አስፍተውታል።
ቢሮው ሦስት የተለያዩ ሕንፃዎችን ያካተተ ሲሆን እነዚህም ለአስተዳደርና ለትርጉም ቢሮዎች እንዲሁም ለመኖሪያ ክፍሎች፣ ለወጥ ቤትና ለልብስ ንጽሕና ክፍል ያገለግላሉ። የውሰናውን ንግግር የሰጠው የይሖዋ ምሥክሮች የበላይ አካል አባል የሆነው ጋይ ፒርስ ነበር። በውሰናው ፕሮግራም ላይ ከአሥር አገሮች የተውጣጡ እንግዶች ተገኝተው ነበር። ሁሉም በጣም የሚያምረውን አዲሱን ቢሮ በማየታቸው ተደስተዋል።
[በገጽ 8 ላይ የሚገኝ ሥዕል]
ቡልጋሪያ
መቄዶንያ
ስኮፕዬ
አልባኒያ
ግሪክ
[በገጽ 8 ላይ የሚገኝ ሥዕል]
ስኮፕዬ፣ መቄዶንያ