አሁንና ለዘላለም እውቀት ማካበት
አሁንና ለዘላለም እውቀት ማካበት
ኧልሪክ ሽትሩንስ የተባሉ ጀርመናዊ ሐኪም ዘላለም ወጣት (እንግሊዝኛ) በሚል ርዕስ በጻፏቸው ተከታታይ መጻሕፍት ላይ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ፣ የተመጣጠነ ምግብ መመገብ እንዲሁም ጎጂ ከሆኑ ልማዶች መራቅ የተሻለ ጤንነት ለማግኘትና ረጅም ዘመን ለመኖር እንደሚያስችል ገልጸዋል። ያም ሆኖ እኚህ ሐኪም ከላይ የተገለጹትን ምክሮች ተግባራዊ ማድረግ ለዘላለም ለመኖር እንደሚያስችል ቃል አልገቡም።
ይሁን እንጂ የዘላለም ሕይወት ተስፋ የሚሰጥ አንድ ዓይነት እውቀት አለ። በአንጻሩ ለዘላለም ኖረህ ቢሆን ደግሞ ጠቃሚ የሆነ እውቀት ለዘላለም ማካበት ትችል ነበር። ኢየሱስ ለአምላክ ባቀረበው ጸሎት “እውነተኛ አምላክ የሆንኸውን አንተንና የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ሕይወት ናት” ብሎ ነበር። (ዮሐንስ 17:3) እስቲ በቅድሚያ “የዘላለም ሕይወት” ሲባል ምን ማለት እንደሆነ እንመርምር፤ ከዚያም የዘላለም ሕይወት የሚያስገኘው ይህ እውቀት ምን ነገሮችን እንደሚጨምርና ይህንን እውቀት እንዴት ማግኘት እንደምትችል እንመለከታለን።
ፈጣሪ በቅርቡ ምድርን ወደ ገነትነት እንደሚለውጣት መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል፤ ይህም ለረጅም ዘመናት ለመኖር አመቺ ሁኔታ ይፈጥራል። ምድርን ወደ ገነትነት ለመለወጥ በኖኅ ዘመን እንደመጣው የጥፋት ውኃ ያለ ሥር ነቀል እርምጃ መውሰድ ያስፈልጋል። ማቴዎስ ምዕራፍ 24 ከቁጥር 37 እስከ 39 እንደሚያሳየው ኢየሱስ ያለንበትን ዘመን “በኖኅ ዘመን” ከነበረው ሁኔታ ጋር አወዳድሮታል፤ በዚያን ዘመን የነበሩት ሰዎች ያሉበት ሁኔታ ምን ያህል አሳሳቢ እንደሆነ “ሳያውቁ” ማለትም ሳያስተውሉ ቀርተዋል። ኖኅ ለሚሰብከው መልእክትም ጆሯቸውን መስጠት አልፈለጉም ነበር። ‘ኖኅ ወደ መርከቡ በገባበት ቀን’ የጥፋት ውኃው ለመስማት ፈቃደኛ ያልነበሩትን ሰዎች በሙሉ ጠራርጎ አጠፋቸው። ኖኅና ከእርሱ ጋር ወደ መርከቡ የገቡት ግን በሕይወት ተረፉ።
ኢየሱስ በዚህ ዘመንም ተመሳሳይ “ቀን” እንደሚመጣ ተናግሯል። ስለዚህ ክንውን የሚገልጸውን እውቀት በትኩረት የሚያዳምጡ ሰዎች ከጥፋቱ ከመትረፍም አልፎ ለዘላለም የመኖር ተስፋ ይኖራቸዋል። ከዚህም በላይ በሞት አንቀላፍተው ያሉ ሰዎችም እንደገና ሕይወት የሚያገኙ ሲሆን ከዚያ በኋላ ለዘላለም የመኖር ተስፋ ይኖራቸዋል። (ዮሐንስ 5:28, 29) ኢየሱስ እነዚህን ሁለት ሐሳቦች እንዴት አድርጎ እንደገለጻቸው ተመልከት። ስለ ሙታን ትንሣኤ ከማርታ ጋር እየተወያየ ሳለ እንዲህ አለ:- “በእኔ የሚያምን ቢሞት እንኳ በሕይወት ይኖራል፤ በእኔ የሚኖር፣ የሚያምንብኝም ከቶ አይሞትም።” መረጃዎቹ በሙሉ እንደሚያሳዩት ለውጥ የሚመጣበት ይህ “ቀን” በጣም ቀርቧል፤ ይህም ሲባል አንተም ‘ከቶ ላትሞት’ ትችላለህ ማለት ነው።—ዮሐንስ 11:25-27
ቀጥሎም ኢየሱስ “ይህን ታምኛለሽን?” በማለት ማርታን ጠየቃት። እርሷም “አዎን ጌታ ሆይ” የሚል ምላሽ ሰጠች። ዛሬ ኢየሱስ ይህንኑ ጥያቄ ለአንተ ቢያቀርብልህ ኖሮ ምላሽህ ምን ይሆን ነበር? ፈጽሞ ሳይሞቱ መኖር ይቻላል ብሎ ማመን ይከብድህ ይሆናል። እንደዚያ ቢሰማህም እንኳ በዚህ ተስፋ ለማመን እንደምትፈልግ ጥርጥር የለውም። ‘ከቶ የማትሞት’ ከሆነ ምን ያህል እውቀት ልታካብት እንደምትችል እስቲ አስበው። አሁን ልትማራቸውና ልታደርጋቸው ብትፈልግም ጊዜ በማጣት ምክንያት መማርም ሆነ ማድረግ ያልቻልካቸውን ነገሮች ስታከናውን በዓይነ ኅሊናህ ተመልከት! እንዲሁም በሞት ያጣሃቸውን የምትወዳቸውን ሰዎች እንደገና ስታገኛቸው ምን እንደሚሰማህ አስብ! እነዚህ ሁሉ ነገሮች እውን እንዲሆኑ የሚያስችለው ምን ዓይነት እውቀት ነው? ይህንንስ እውቀት እንዴት ልታገኘው ትችላለህ?
ሕይወት ሰጪ የሆነውን እውቀት ማግኘት ከአቅማችን በላይ አይደለም
ስለ አምላክና ስለ ክርስቶስ የሚናገረውን ይህንን እውቀት መቅሰም ከአቅማችን በላይ ነው? በፍጹም። በእርግጥ ስለ ፈጣሪያችን ሥራዎች የሚገልጸው እውቀት ማብቂያ የለውም። ሆኖም ኢየሱስ ‘እውቀት’ እና “የዘላለም ሕይወት” እንደሚዛመዱ ሲናገር በከዋክብት ጥናት ወይም በሌላ የሳይንስ መስክ ስለሚገኘው እውቀት መጥቀሱ አልነበረም። ምሳሌ ምዕራፍ 2 ቁጥር 1 እና 5 በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኘውን ‘ቃል’ እና ‘ትእዛዝ’ መማር ስለ ‘አምላክ ለማወቅ’ መሠረታዊ ነገር እንደሆነ ይናገራል። ዮሐንስ 20:30, 31 ደግሞ ‘ሕይወት እንዲኖረን’ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለ ኢየሱስ የተጻፉትን ነገሮች ማወቃችን በቂ መሆኑን ይገልጻል።
እንግዲያው የዘላለም ሕይወት ማግኘት የምትችለው እንዴት እንደሆነ ለመረዳት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለ ይሖዋ እና ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ተመዝግቦ የሚገኘው እውቀት በቂ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ በዓይነቱ ልዩ የሆነ መጽሐፍ ነው። ፈጣሪያችን በመንፈሱ አማካኝነት መጽሐፍ ቅዱስን ያስጻፈበት መንገድ ደግነቱን ያንጸባርቃል፤ አጋጣሚ ባለማግኘታቸው ብዙም ያልተማሩ ሰዎች እንኳ ይህንን መጽሐፍ አንብበው የዘላለም ሕይወት ለማግኘት የሚያስችላቸውን እውቀት መቅሰም ይችላሉ። በሌላ በኩል ደግሞ ፈጣን አእምሮ እንዲሁም በቂ ጊዜና አቅም ያላቸው ሰዎችም ቢሆኑ በመንፈስ አነሳሽነት ከተጻፈው ከዚህ መጽሐፍ ምንጊዜም አዳዲስ እውቀት ማግኘት ይችላሉ። ይህንን መጽሔት ማንበብ መቻልህ መማር እንደምትችል ያሳያል፤ ሆኖም ይህን ችሎታህን እንዴት ልትጠቀምበት ይገባል?
በዓለም ዙሪያ ከሚገኙ ከተለያዩ ሰዎች ምሳሌ መመልከት እንደሚቻለው ይህንን እውቀት ለመቅሰም ከሁሉ ይበልጥ ውጤታማ የሆነው መንገድ ትምህርቱን በደንብ በሚያውቀው ሰው እርዳታ መጽሐፍ ቅዱስን በግለሰብ ደረጃ ማጥናት ነው። ኖኅ በዘመኑ ለነበሩት ሰዎች ያወቀውን ለማሳወቅ ይጥር እንደነበረ ሁሉ የይሖዋ ምሥክሮችም ቤትህ ድረስ መጥተው መጽሐፍ ቅዱስን አብረውህ ለማጥናት ፈቃደኞች ናቸው። አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው? በተባለው ብሮሹር ወይም ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራ እውቀት በተባለው መጽሐፍ በመጠቀም a ምድር ገነት በምትሆንበት ወቅት ታማኝ ሰዎች ‘ከቶ እንደማይሞቱ’ የሚገልጸው የመጽሐፍ ቅዱስ ሐሳብ ለማመን አዳጋች ቢሆንብህም መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናትህ በዚህ ተስፋ ላይ እምነት እንድታዳብር ይረዳሃል። እንግዲያው ለዘላለም ለመኖር የምትፈልግ ከሆነ አሊያም በዚህ ተስፋ ለማመን የሚያበቃ ምክንያት መኖሩን ለማረጋገጥ ከፈለግህ ምን ማድረግ ይኖርብሃል? መጽሐፍ ቅዱስ እንድታጠና የቀረበልህን ግብዣ ተቀበል።
ሊያስጠኑህ ይችላሉ።እንደዚህ ያለው ጥናት ምን ያህል ጊዜ ይወስዳል? ከላይ የተገለጸው ባለ 32 ገጽ ብሮሹር በመቶ በሚቆጠሩ ቋንቋዎች የሚገኝ ሲሆን 16 አጫጭር ትምህርቶችን የያዘ ነው። ወይም ደግሞ በየሳምንቱ ለጥናት አንድ ሰዓት ያህል መመደብ ከቻልክ ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራ እውቀት በተባለው መጽሐፍ በመጠቀም በጥቂት ወራት ውስጥ ዋና ዋና የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶችን ማወቅ ትችላለህ። እነዚህ ጽሑፎች ብዙዎች ሰፋ ያለ እውቀት እንዲቀስሙና ለአምላክ ጥልቅ ፍቅር እንዲያዳብሩ ረድተዋቸዋል። ፈጣሪ ከልባቸው የሚወድዱትን ሰዎች የዘላለም ሕይወት በመስጠት ይባርካቸዋል።
በእርግጥም ሕይወት ሰጪ የሆነውን እውቀት ማግኘት ከአቅማችን በላይ አይደለም፤ እንዲያውም በቀላሉ ተዘጋጅቶ ቀርቦልናል። መጽሐፍ ቅዱስ ሙሉውን ወይም በከፊል ከ2,000 በሚበልጡ ቋንቋዎች ተተርጉሟል። በ235 አገሮች የሚገኙ የይሖዋ ምሥክሮች መንፈሳዊ የእውቀት አድማስህን ማስፋት እንድትችል በግላቸው ሊረዱህም ሆነ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረቱ ጽሑፎችን ሊያመጡልህ ፈቃደኞች ናቸው።
የግል ጥናት
ከአምላክ ጋር የምትመሠርተው ዝምድና በአንተና በፈጣሪ መካከል የሚኖር የግል ጉዳይ ነው። ይህ ዝምድና እንዳይቋረጥ ማድረግም ሆነ ግንኙነታችሁን ማጠናከር የምትችለው አንተ ብቻ ስትሆን የዘላለም ሕይወት ደግሞ ከእርሱ ሌላ ማንም ሊሰጥህ አይችልም። እንግዲያው በጽሑፍ የተቀመጠውን ቃሉን በግልህ ማጥናትህን መቀጠል ይኖርብሃል። አንድ ሰው በቋሚነት ወደ ቤትህ እየመጣ እንዲያስጠናህ ፕሮግራም በማውጣት ለጥናት ጊዜ መመደብ ትችላለህ።
መጽሐፍ ቅዱስም ሆነ መጽሐፍ ቅዱስን ለማጥናት እንዲረዱ ተብለው የተዘጋጁት ጽሑፎች ‘አምላክን ለማወቅ’ ስለሚረዱ በጥንቃቄ መያዛቸው በጣም አስፈላጊ ነው። (ምሳሌ 2:5) በዚህ መንገድ ከያዝካቸው ለዓመታት ልትጠቀምባቸው ትችላለህ። የምትኖረው በማደግ ላይ በሚገኙ አገሮች ውስጥ ከሆነ በትምህርት ቤት የመማሪያ መጽሐፍ ማግኘት አስቸጋሪ በመሆኑ በዋነኝነት የተማርከው በማዳመጥና በመመልከት ሊሆን ይችላል። ለምሳሌ በቤኒን ከ50 የሚበልጡ ቋንቋዎች ይነገራሉ። ሰዎች አራት ወይም አምስት ቋንቋዎችን አቀላጥፈው ሲናገሩ መስማት የተለመደ ሲሆን የሚያስገርመው ግን እነዚህ ሰዎች በግላቸው ቋንቋውን የሚማሩበት መጽሐፍ ፈጽሞ አግኝተው የማያውቁ መሆኑ ነው። በማዳመጥ፣ በመመልከትና ትኩረት ሰጥተን በመከታተል የመማር ችሎታችን ከፈጣሪ ያገኘነው ስጦታ ነው። ያም ቢሆን ግን መጻሕፍት ለጥናትህ ትልቅ አስተዋጽኦ ያደርጋሉ።
የምትኖረው ጠባብ ቤት ውስጥ ቢሆንም እንኳ መጽሐፍ ቅዱስህንና መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጽሑፎችህን የምታስቀምጥበት ተስማሚ ቦታ አዘጋጅ። በቀላሉ ልታገኛቸው በምትችልበት ሆኖም በማይበላሹበት ቦታ አስቀምጣቸው።
የቤተሰብ ጥናት
ወላጅ ከሆንክ አንተ የምታገኘውን እውቀት ልጆችህም እንዲያገኙ ልትረዳቸው ይገባል። በማደግ ላይ ባሉ አገሮች ውስጥ አብዛኛውን ጊዜ ወላጆች ለልጆቻቸው ለኑሮ አስፈላጊ የሆኑትን ሙያዎች የማስተማር ልማድ አላቸው። ምግብ ማብሰል፣ እንጨት መልቀም፣ ውኃ መቅዳት፣ ማረስ፣ ዓሣ ማጥመድ እንዲሁም ከገበያ ዕቃ መግዛት ያስተምሯቸዋል። እንዲህ ያለው ትምህርት በሕይወታቸው ውስጥ እንደሚጠቅማቸው እሙን ነው። ሆኖም በርካታ ወላጆች ልጆቻቸው ከዚህ ሥልጠና በተጨማሪ ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራውን እውቀት እንዲቀስሙ አይረዷቸውም።
ያለህበት ሁኔታ ምንም ይሁን ምን ትርፍ ጊዜ እንደሌለህ ይሰማህ ይሆናል። ፈጣሪም ቢሆን ይህንን ይገነዘባል። አምላክ ለልጆች የእርሱን መንገዶች እንዴት ማስተማር እንደሚቻል ሲገልጽ ከረጅም ዘመናት በፊት እንዲህ ብሎ ነበር:- “ለልጆችህም አስጠናቸው፤ በቤትህ ስትቀመጥ፣ በመንገድም ስትሄድ፣ ስትተኛና ስትነሣም ስለ እነርሱ ተናገር።” (ዘዳግም 6:7) በዚህ ሐሳብ መሠረት እንደሚከተለው ያለ የማስተማሪያ ፕሮግራም ማውጣት ትችላለህ:-
1. “በቤትህ ስትቀመጥ”:- መጽሐፍ ቅዱስን ስታጠና አንድ ሰው እንደረዳህ ሁሉ አንተም ቋሚ ፕሮግራም አውጥተህ
ልጆችህን ለማስጠናት ጥረት አድርግ፤ ይህንንም በሳምንት አንድ ጊዜ ቤትህ ሆነህ ልታደርገው ትችል ይሆናል። የይሖዋ ምሥክሮች በየትኛውም የዕድሜ ክልል ለሚገኙ ልጆች የሚሆኑ የተለያዩ የማስተማሪያ መጻሕፍት አሏቸው።2. “በመንገድም ስትሄድ”:- በሕይወት ውስጥ አስፈላጊ ስለሆኑት ነገሮች በተለያየ አጋጣሚ ለልጆችህ እንደምትነግራቸው ወይም እግረ መንገድህን መመሪያዎች እንደምትሰጣቸው ሁሉ ስለ ይሖዋም ባገኘኸው አጋጣሚ ሁሉ ንገራቸው።
3. ‘ስትተኛ’:- ሁልጊዜ ማታ ማታ ከልጆችህ ጋር አብራችሁ ጸልዩ።
4. “ስትነሣም”:- በርካታ ቤተሰቦች በየዕለቱ ጠዋት በአንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ላይ አብረው መወያየታቸው ጠቅሟቸዋል። የይሖዋ ምሥክሮች ቅዱሳን ጽሑፎችን በየዕለቱ መመርመር b በተባለው ቡክሌት በመጠቀም በየቀኑ አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ያነብባሉ።
በማደግ ላይ ባሉ አገሮች የሚገኙ ወላጆች ከልጆቻቸው አንዱ ጥሩ ሰብዓዊ ትምህርት እንዲያገኝ ለመርዳት ከፍተኛ ጥረት ያደርጋሉ። በዚህ መንገድ ወላጆች በዕድሜ ሲገፉ የሚጦራቸው ልጅ ያገኛሉ። ሆኖም አንተ መጽሐፍ ቅዱስን ካጠናህና ልጆችህ በሙሉ እንዲያጠኑ ከረዳሃቸው አንተም ሆንክ መላው ቤተሰብህ የዘላለም ሕይወት ማግኘት እንድትችሉ የሚረዳችሁን እውቀት ትቀስማላችሁ።
ሁሉን ነገር ማወቅ የምንችልበት ጊዜ ይኖር ይሆን? አይኖርም። ምድራችን ዳርቻ በሌለው አጽናፈ ዓለም ውስጥ የምታደርገውን ጉዞ እስከቀጠለች ድረስ እኛም እውቀት መቅሰማችንን አናቆምም። በእርግጥም መክብብ 3:11 እንዲህ ይላል:- “[አምላክ] ሁሉንም ነገር በጊዜው ውብ አድርጎ ሠራው፤ በሰዎችም ልብ ዘላለማዊነትን አኖረ፤ ይሁን እንጂ እግዚአብሔር ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ያደረገውን ማወቅ አይችሉም።” እውቀት መቅሰም ማብቂያ የሌለው አስደሳች ሥራ ነው።
[የግርጌ ማስታወሻዎች]
a ሁለቱም የተዘጋጁት በይሖዋ ምሥክሮች ነው።
b በይሖዋ ምሥክሮች የተዘጋጀ።
[በገጽ 5 ላይ የሚገኝ የተቀነጨበ ሐሳብ]
“. . . ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ሕይወት ናት”
[በገጽ 7 ላይ የሚገኝ ሥዕል]
ቤተሰብህ አሁንም ሆነ ለዘላለም እውቀት እንዲቀስም አድርግ