በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

አሳዛኝ ሁኔታ ተከሰተ

አሳዛኝ ሁኔታ ተከሰተ

አሳዛኝ ሁኔታ ተከሰተ

የሁለት ዓመት ከስድስት ወር ዕድሜ ያለው ኦወን መታጠቢያ ቤት ገብቶ እየተጫወተ ነበር። ወላጆቹ አይደርስበትም ብለው ባሰቡት የመድኃኒት መደርደሪያ ላይ እንደምንም ተንጠላጥሎ ደረሰ። በመደርደሪያው ውስጥ ካሉት ዕቃዎች መካከል ትኩረቱን የሳበውን አንድ ብልቃጥ ከፍቶ በውስጡ ያለውን ጠጣ። በዚህም ምክንያት አሳዛኝ ሁኔታ ተከሰተ።

የሚያሳዝነው ነገር ብልቃጡ የያዘው መርዛማ አሲድ በመሆኑ ሕፃኑ ኦወን ለሕልፈተ ሕይወት ተዳረገ። በዚህ ጊዜ የወላጆቹ ልብ በሐዘን ተሰበረ። የኦወን አባት ፐርሲ መጽናኛ ማግኘት ስለፈለገ የቤተ ክርስቲያናቸውን ቄስ “ይህ ዓይነቱ ሁኔታ የተፈጠረው ለምንድን ነው?” ብሎ ጠየቃቸው። ቄሱም “አምላክ ትንሽ መልአክ ስለፈለገ ወደ ሰማይ ወስዶታል” ብለው መለሱለት። በሐዘን የተዋጠው አባት እንዲህ ያለው ድርጊት ኢፍትሐዊ እንደሆነ ተሰማው። አምላክ ይህ አሳዛኝ ሁኔታ እንዲከሰት በእርግጥ ይፈልግ ነበር? ፐርሲ በጣም ስላተበሳጨ ቤተ ክርስቲያን መሄዱን አቆመ።

ፐርሲ ‘ልጄ አሁንም እየተሰቃየ ይሆን? ወደፊትስ አገኘው ይሆን?’ በማለት ስለ ሁኔታው ይጨነቅ ነበር።

አንተም ‘አንድ ሰው ሲሞት ምን ይሆናል? በሞት ካጣናቸው የምንወዳቸው ሰዎች ጋር እንደገና መገናኘት እንችል ይሆን?’ ብለህ ትጠይቅ ይሆናል። የአምላክ ቃል የሆነው መጽሐፍ ቅዱስ ለእነዚህ ጥያቄዎች መልስ ይሰጣል። እንዲሁም ይህን የመሰለ አሳዛኝ ሁኔታ ለገጠማቸው ሰዎች ግልጽና የሚያጽናኑ ሐሳቦችን ይዟል። ከዚህም በላይ አምላክ ከፊታችን ሊያደርግልን ቃል ስለገባው አስደሳች ተስፋ ማለትም ስለ ትንሣኤ ያብራራል።

ስለዚህ ግሩም ተስፋ ይበልጥ ማወቅ እንድትችል እባክህ የሚቀጥለውን ርዕስ አንብብ።