በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ሰዎች ድህነትን ሊያስወግዱ ይችላሉ?

ሰዎች ድህነትን ሊያስወግዱ ይችላሉ?

ሰዎች ድህነትን ሊያስወግዱ ይችላሉ?

ድህነት ምን እንደሆነ ሳያውቁ ያደጉ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች አሉ። በሕይወታቸው ውስጥ አንድም ቀን ጦማቸውን አድረው አያውቁም፤ ወይም በብርድ ተቆራምደው ለመተኛት የተገደዱበት ጊዜ የለም። እንደዛም ሆኖ ብዙዎቹ ለድሆች በጣም ከማዘናቸው የተነሳ እነሱን ለመርዳት ከፍተኛ ጥረት ያደርጋሉ።

ሆኖም በእርስ በርስ ጦርነት፣ በጎርፍ መጥለቅለቅ፣ በድርቅና በሌሎች ችግሮች ሳቢያ ብዙ ሰዎች በድህነት እየተሠቃዩ ይኖራሉ። እነዚህ ሁኔታዎች ከዕለት ጉርስ በማያልፍ የግብርና ሥራ ለሚተዳደሩ የአፍሪካ ገበሬዎች አስከፊ ገጠመኞች ናቸው። አንዳንዶች ቤታቸውን ለቀው ወደ ትልልቅ ከተሞች ለመሄድ ወይም በሌላ አገር ስደተኞች ሆነው ለመኖር ተገደዋል። ሌሎች የገጠር ነዋሪዎች ደግሞ የተሻለ ሕይወት እንደሚገኝ ተስፋ በማድረግ ወደ ከተማ ሄደዋል።

አብዛኛውን ጊዜ በሰው የተጨናነቁ ከተሞች ለድህነት መስፋፋት አመቺ ሁኔታ ይፈጥራሉ። እህል ለመዝራት ቢፈለግ እንኳን ያለው ቦታ በጣም ትንሽ ሲሆን እርሱም ከተገኘ ነው። ሥራ ማግኘት በጣም አስቸጋሪ ነው። ብዙዎች ተስፋ በመቁረጥ ወደ ወንጀል ያመራሉ። የከተማ ነዋሪዎች ለእርዳታ ቢጮኹም ሰብዓዊ መንግሥታት እየተስፋፋ ላለው ድህነት ምንም መፍትሔ ሊያመጡ አልቻሉም። የለንደኑ ዚ ኢንዲፔንደንት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በኅዳር 2003 ያወጣውን ሪፖርት በመጥቀስ እንዲህ ብሎ ነበር:- “ከጊዜ ወደ ጊዜ ቁጥራቸው እየጨመረ የሚሄድ ሰዎች እየተራቡ ነው። . . . በዛሬው ጊዜ በዓለም ዙሪያ በቂ ምግብ የማያገኙ 842 ሚሊዮን የሚሆኑ ሰዎች እንደሚኖሩ ሲገመት ይህ ቁጥር ደግሞ በየዓመቱ በ5 ሚሊዮን ጭማሪ ያሳያል።”

በደቡብ አፍሪካ የሚገኘው የይሖዋ ምሥክሮች ቅርንጫፍ ቢሮ አንዳንድ ጊዜ ድህነት ካጠቃቸው ሰዎች ደብዳቤዎች ይደርሱታል። ለምሳሌ በብሉምፎንቴን የሚኖር አንድ ሰው እንዲህ ሲል ጻፈ:- “ሥራ የለኝም፤ ከተማ ውስጥ ለመስረቅ አጋጣሚዎችን ካገኘሁ ወደ ኋላ አልልም። ካልሰረቅሁ ግን አጥንት የሚሰብረው የብርዱ ነገር ሳይነሳ ለብዙ ቀናት እንራባለን። ሥራ የሚባል ነገር በፍጹም የለም። ብዙ ሰዎች ሥራና የሚቀመስ ነገር ለመፈለግ በየመንገዱ ይንከራተታሉ። ሌሎች ምግብ ፍለጋ ወደ ቆሻሻ መጣያ እንደሚሄዱም አውቃለሁ። አንዳንዶቹም ራሳቸውን ይገድላሉ። እንደ እኔ የተጨነቁና ተስፋ የቆረጡ ብዙ ሰዎች አሉ። ለወደፊቱ ጊዜ ምንም ዓይነት ተስፋ ያለ አይመስልም። የመመገብና የመልበስ ፍላጎት እንዲኖረን አድርጎ የፈጠረን አምላክ ይህን ሁሉ አያይም?”

ይህን ሰው ላሳሰቡት ነገሮች አጽናኝ መልሶች አሉ። የሚቀጥለው ርዕስ እንደሚያሳየው መልሶቹን የአምላክ ቃል ከሆነው ከመጽሐፍ ቅዱስ ማግኘት ይቻላል።