በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ሐቀኛ የሆኑ ሰዎች ለይሖዋ ውዳሴ ያመጣሉ

ሐቀኛ የሆኑ ሰዎች ለይሖዋ ውዳሴ ያመጣሉ

የመንግሥቱ አዋጅ ነጋሪዎች ሪፖርት

ሐቀኛ የሆኑ ሰዎች ለይሖዋ ውዳሴ ያመጣሉ

ወጣትም ሆኑ አረጋውያን የይሖዋ ምሥክሮች በዓለም ዙሪያ በሐቀኝነታቸው ይታወቃሉ። ለአብነት ያህል፣ ቀጥሎ የቀረቡትን ከሦስት አህጉራት የተገኙ ተሞክሮዎች ተመልከት።

በናይጄሪያ የምትኖረው የ17 ዓመቷ ኦሉሶላ አንድ ቀን ከትምህርት ቤት ስትመለስ መንገድ ላይ ቦርሳ ወድቆ አገኘች። ቦርሳውን ለትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር ሰጥታ በውስጡ ያለውን ገንዘብ ሲቆጥረው 6,200 ናይራ (390 ብር ገደማ) ሆኖ ተገኘ። ከዚያም ርዕሰ መምህሩ ቦርሳው ጠፍቶበት ለነበረ አንድ አስተማሪ መለሰለት። አስተማሪው በአድናቆት ተገፋፍቶ የትምህርት ቤት ክፍያዋን እንድትከፍል በመንገር 1,000 ናይራ (60 ብር ገደማ) ለኦሉሶላ ሰጣት። ሆኖም ሌሎች ተማሪዎች ስለ ሁኔታው በሰሙ ጊዜ አፌዙባት። ከጥቂት ሳምንታት በኋላ አንድ ተማሪ ገንዘብ እንደተሰረቀበት በመናገሩ አስተማሪዎቹ ሁሉንም ተማሪዎች መፈተሽ ጀመሩ። በዚህ ወቅት አስተማሪው ለኦሉሶላ “አንቺ እዚሁ ሁኚ፤ የይሖዋ ምሥክር እንደመሆንሽ መጠን እንደማትሰርቂ አውቃለሁ” አላት። በመጨረሻም የጠፋው ገንዘብ በኦሉሶላ ሲያፌዙ በነበሩ ሁለት ወንዶች ልጆች ላይ ተገኘ፤ እነሱም ከባድ ቅጣት ተቀበሉ። ኦሉሶላ “ፈጽሞ ከማይሰርቁት የይሖዋ ምሥክሮች እንደ አንዷ ሆኜ በመቆጠሬና በዚህም ይሖዋ መከበር መቻሉ እጅግ አስደስቶኛል” ስትል ጽፋለች።

የአርጀንቲና ተወላጅ የሆነው ማርሴሎ አንድ ቀን ከቤቱ የጓሮ በር ጥቂት ሜትሮች ራቅ ብሎ የወደቀ ቦርሳ አገኘ። ቦርሳውን ወደ ቤቱ ካስገባ በኋላ ከባለቤቱ ጋር በመሆን በጥንቃቄ ከፈተው። በውስጡ ዳጎስ ያለ ጥሬ ገንዘብ፣ ክሬዲት ካርዶችና የተፈረሙ የባንክ ቼኮች መኖራቸውን ሲመለከቱ በጣም ተደነቁ። እንዲያውም አንደኛው ቼክ አንድ ሚሊዮን ፔሶ ዋጋ (2,800,000 ብር ገደማ) አለው። ከቦርሳው ውስጥ ባገኙት ፋክቱር ላይ ያለውን ስልክ ቁጥር በመጠቀም ባለቤቱ እቃውን ወደ ማርሴሎ መሥሪያ ቤት መጥቶ እንዲረከብ ዝግጅት አደረጉ። ባለቤቱ ሲመጣ የተረበሸ ይመስል ስለነበር የማርሴሎ አሠሪ ማርሴሎ የይሖዋ ምሥክር በመሆኑ እንዲረጋጋ ነገረው። የንብረቱ ባለቤት ወሮታውን ለመመለስ በማሰብ ለማርሴሎ 20 ፔሶ (51 ብር ገደማ) ብቻ ሰጠው። ይህ ሁኔታ በማርሴሎ ሐቀኝነት በጣም ተደንቆ የነበረውን አሠሪ በጣም አስቆጣው። ማርሴሎ ያገኘውን አጋጣሚ የይሖዋ ምሥክር እንደመሆኑ መጠን በማንኛውም ወቅት ሐቀኛ መሆን እንደሚፈልግ ለማብራራት ተጠቀመበት።

የሚከተለው ተሞክሮ ደግሞ ከኪርጊስታን የተገኘ ነው። የ6 ዓመቱ ሪናት በአቅራቢያቸው የምትኖር ሴት ንብረት የሆነ ቦርሳ አገኘ። ይህ ቦርሳ በውስጡ 1,100 ሶም (216 ብር ገደማ) ይዟል። ሪናት ጠፍቶ የተገኘውን ቦርሳ ለሴትየዋ በመለሰላት ጊዜ ውስጡ ያለውን ገንዘብ ቆጠረችና 200 ሶም (43 ብር ገደማ) መጉደሉን ለሪናት እናት ነገረቻት። ሪናት ገንዘቡን እሱ እንዳልወሰደ በመናገሩ ሁሉም ቀሪውን ገንዘብ ለመፈለግ ሄዱ። በመጨረሻም የጎደለውን ገንዘብ ቦርሳው ወድቆ ከነበረበት አካባቢ ብዙም ሳይርቅ አገኙት። ሴትየዋ በሁኔታው በጣም ተደነቀች። ስለሆነም በመጀመሪያ የጠፋባትን ገንዘብ ስለመለሱላት ቀጥላም ልጇን ጥሩ ክርስቲያናዊ ሥልጠና ሰጥታ ስላሳደገች ሪናትንና እናቱን አመሰገነቻቸው።