በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ከቤተሰብህ ጋር ትጨዋወታለህ?

ከቤተሰብህ ጋር ትጨዋወታለህ?

ከቤተሰብህ ጋር ትጨዋወታለህ?

 “በፖላንድ በየሳምንቱ የሚታተም ፖሊቲካ የተባለ መጽሔት “ከቤተሰቦቻችን ጋር ያለን ሐሳብ ለሐሳብ የመለዋወጥ ችሎታ በፍጥነት እያሽቆለቆለ መጥቷል” ብሏል። በዩናይትድ ስቴትስ የሚገኙ የትዳር ጓደኛሞች በቀን ውስጥ እርስ በርሳቸው ትርጉም ያለው ጭውውት በማድረግ የሚያሳልፉት ጊዜ 6 ደቂቃ ብቻ እንደሆነ ይገመታል። አንዳንድ በመስኩ የተሰማሩ ባለሙያዎች እንደሚገምቱት ከሆነ ይህ ችግር ከጠቅላላው ፍቺና መለያየት ውስጥ ግማሽ ለሚሆኑት ምክንያት ሆኗል።

በወላጆችና በልጆች መካከል ስለሚደረገው የሐሳብ ልውውጥ ምን ለማለት ይቻላል? ብዙውን ጊዜ “ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር የያዙት መጨዋወት ሳይሆን፤ ትምህርት እንዴት ነው? ጓደኞችህስ? እንደሚሉት ያሉ ጥያቄዎችን በመደርደር ምርመራ ማካሄድ ሆኗል” ሲል ቀደም ብሎ የተጠቀሰው ሪፖርት አስተያየቱን አስፍሯል። ቀጠል አድርጎም “ታዲያ ልጆቻችን ስሜታዊ ትስስርን ማዳበር እንዴት ይማሩ?” ሲል ይጠይቃል።

ጥሩ የሐሳብ ልውውጥ የማድረግ ችሎታ እንዲሁ የማይገኝ ከሆነ፣ በጥሩ ሁኔታ ለመጨዋወት የሚያስችለንን ክህሎት እንዴት ማዳበር እንችላለን? ክርስቲያኑ ደቀ መዝሙር ያዕቆብ “ሰው ሁሉ ለመስማት የፈጠነ፣ ለመናገር የዘገየ፣ ለቊጣም የዘገየ ይሁን” ሲል ጠቃሚ ምክር ሰጥቶናል። (ያዕቆብ 1:19) አዎን፤ ከሌሎች ጋር የሚያንጽ ጭውውት ለማድረግ በጥሞና ማዳመጥ፣ ተናግረው እስኪጨርሱ በትዕግሥት መጠበቅና ዘሎ መደምደሚያ ላይ ከመድረስ መቆጠብ ይኖርብናል። ጭውውቱ ባጭሩ እንዳይቀጭ ነቃፊ ከመሆን ራቅ። ኢየሱስ በዘዴ ጥያቄዎችን የማቅረብ ልማድ የነበረው ቢሆንም እንኳ ይህን የሚያደርገው አድማጮቹ የልባቸውን አውጥተው እንዲናገሩና በመካከላቸው ያለው ትስስር ይበልጥ እንዲጠናከር ለማድረግ እንጂ እነሱን መመርመር ፈልጎ አልነበረም።—ምሳሌ 20:5፤ ማቴዎስ 16:13-17፤ 17:24-27

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙትን ግሩም መመሪያዎች በሥራ ላይ ማዋልህ ጭውውት ለመጀመር ቀዳሚ በመሆን ከምትወዳቸው ሰዎች ጋር ጥሩ የሐሳብ ግንኙነት እንድታደርግ ያስችልሃል። ይህም ለበርካታ ዓመታት አልፎ ተርፎም ዕድሜ ልክ የሚዘልቅ የሞቀ ወዳጅነት እንድትመሠርት ሊረዳህ ይችላል።