በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ማንኛውንም ፈተና መቋቋም እንችላለን!

ማንኛውንም ፈተና መቋቋም እንችላለን!

ማንኛውንም ፈተና መቋቋም እንችላለን!

በአሁኑ ወቅት በሕይወትህ ውስጥ ፈተና የሆነብህ ነገር አለ? ያጋጠመህን ነገር ልትወጣው እንደማትችል ተሰምቶህ ተስፋ ቆርጠሃል? እንዲያውም አንዳንድ ጊዜ ያጋጠመህ ችግር በአንተ ላይ ብቻ የደረሰ እንደሆነና መፍትሄ እንደሌለው ይሰማሃል? እንደዚህ የሚሰማህ ከሆነ ተስፋ አትቁረጥ! ምንም ዓይነት ፈተና ቢያጋጥመን በአምላክ እርዳታ አማካኝነት ልንቋቋመው እንደምንችል መጽሐፍ ቅዱስ ማረጋገጫ ይሰጠናል።

የአምላክ አገልጋዮች “ልዩ ልዩ መከራ” እንደሚደርስባቸው መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ ይናገራል። (ያዕቆብ 1:2) እዚህ ላይ “ልዩ ልዩ” (በግሪክኛ ፓይኪሎስ) የሚለውን ቃል ልብ በል። የመጀመሪያው የግሪክኛ ቃል ቀደም ሲል “በርካታ” ወይም “ባለ ብዙ ፈርጅ” የሚል ትርጉም የነበረው ሲሆን “ፈተናዎች ብዙ ገጽታ” ያላቸው መሆኑንም ጎላ አድርጎ ይገልጻል። በቀላል አነጋገር “ብዙ መልክ ያለው” ማለት ነው። በመሆኑም “ልዩ ልዩ መከራ” ሲባል መከራ በተለያየ መልክ እንደሚመጣ ያሳያል። ሆኖም ይሖዋ እያንዳንዱን ፈተና መቋቋም እንድንችል ይደግፈናል። እንዲህ ብለን በእርግጠኝነት መናገር የምንችለው ለምንድን ነው?

“የእግዚአብሔር ልዩ ልዩ ጸጋ”

ሐዋርያው ጴጥሮስ ክርስቲያኖች “በብዙ ዐይነት ፈተና . . . መከራን” እንደሚቀበሉ ተናግሯል። (1 ጴጥሮስ 1:6) ቆየት ብሎም በመንፈስ አነሳሽነት በጻፈው ደብዳቤ ላይ ስለ “እግዚአብሔር ልዩ ልዩ ጸጋ” ገልጿል። (1 ጴጥሮስ 4:10) “ልዩ ልዩ” ለሚለው ሐረግ የገባው የመጀመሪያው የግሪክኛ ቃል ቀደም ሲል በክርስቲያኖች ላይ ስለሚደርሰው መከራ ከተገለጸበት ቃል ጋር ተመሳሳይ ነው። አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ምሑር ይህን ቃል አስመልክተው ሐሳብ ሲሰጡ እንዲህ ብለዋል:- “ይህ ድንቅ ሐሳብ ነው። . . . የአምላክ ጸጋ ፓይኪሎስ እንደሆነ መገለጹ ይህ ጸጋ ሊያሸንፈው የማይችል ምንም ዓይነት ሰብዓዊ ሁኔታ አለመኖሩን የሚያሳይ ነው።” አክለውም እንዲህ ሲሉ ተናግረዋል:- “የአምላክ ጸጋ መፍትሄ የማያገኝለትና የማያሸንፈው ምንም ዓይነት ሁኔታ፣ ችግር እንዲሁም ድንገተኛ ወይም አጣዳፊ ክስተት የለም። በሕይወት ውስጥ የአምላክ ጸጋ የማይቋቋመው ምንም ነገር የለም። ይህ ገላጭ የሆነ ፓይኪሎስ የተባለ ቃል የአምላክ ጸጋ ብዙ ገጽታ ያለው እንደሆነና ሁሉንም ዓይነት ችግሮች እንድንቋቋም እንደሚረዳን ያስታውሰናል።”

የአምላክ ጸጋ ፈተናዎችን ለመቋቋም ይረዳናል

ጴጥሮስ በተናገረው መሠረት የአምላክ ጸጋ የሚገለጥበት አንዱ መንገድ በተለያዩ የክርስቲያን ጉባኤ አባላት አማካኝነት ነው። (1 ጴጥሮስ 4:11) እያንዳንዱ የአምላክ አገልጋይ በአሁኑ ጊዜ ፈተና እያጋጠማቸው ላሉ ክርስቲያኖች የብርታት ምንጭ ሆኖ ለማገልገል የሚያስችል መንፈሳዊ ስጦታ ወይም ችሎታ አለው። (ሮሜ 12:6-8) ለምሳሌ አንዳንድ የጉባኤው አባላት የተዋጣላቸው የመጽሐፍ ቅዱስ አስተማሪዎች ናቸው። ማስተዋል የተሞላበት ንግግራቸው ሌሎች እንዲበረታቱና እንዲጸኑ ይረዳቸዋል። (ነህምያ 8:1-4, 8, 12) ሌሎች ደግሞ እርዳታ የሚያስፈልጋቸውን አዘውትረው ቤታቸው እየሄዱ እረኝነት ያደርጉላቸዋል። እንደነዚህ የመሰሉት ጉብኝቶች ለማበረታታትና ‘ልብን ለማጽናናት’ የሚያስችሉ አጋጣሚዎች ናቸው። (ቈላስይስ 2:2) የበላይ ተመልካቾች እንደዚህ የመሰሉ እምነት የሚያጠናክሩ ጉብኝቶችን ሲያደርጉ መንፈሳዊ ስጦታን ያካፍላሉ። (ዮሐንስ 21:16) በጉባኤ የሚገኙ ሌሎችም በፈተናዎች ላዘኑት የእምነት አጋሮቻቸው ሞቅ ያለ ፍቅር፣ ርኅራኄና አሳቢነት በማሳየት የታወቁ ናቸው። (የሐዋርያት ሥራ 4:36፤ ሮሜ 12:10፤ ቈላስይስ 3:10) እንደነዚህ የመሳሰሉት አፍቃሪ ወንድሞችና እህቶች የሚያሳዩት ርኅራኄና የሚያደርጉት እርዳታ የአምላክ ጸጋ የሚገለጽበት መንገድ ነው።—ምሳሌ 12:25፤ 17:17

“የመጽናናትም ሁሉ አምላክ”

ከሁሉም በላይ ይሖዋ ማጽናኛ ይሰጠናል። “የመጽናናትም ሁሉ አምላክ . . . እርሱ በመከራችን ሁሉ ያጽናናናል።” (2 ቆሮንቶስ 1:3, 4) ይሖዋ እንዲረዳን ለምናቀርበው ጸሎት በዋነኝነት መልስ የሚሰጠው በመንፈሱ ባስጻፈው በቃሉ ውስጥ በሚገኘው ጥበብና በቅዱስ መንፈሱ አማካኝነት በሚሰጠን ጥንካሬ ነው። (ኢሳይያስ 30:18, 21፤ ሉቃስ 11:13፤ ዮሐንስ 14:16) ሐዋርያው ጳውሎስ እንደሚከተለው በማለት በመንፈስ አነሳሽነት የጻፈው ተስፋ ያበረታታናል:- “እግዚአብሔር ታማኝ ነው፤ ስለዚህ ከምትችሉት በላይ እንድትፈተኑ አይተዋችሁም፤ ነገር ግን በምትፈተኑበት ጊዜ ፈተናውን መታገሥ እንድትችሉ፣ መውጫ መንገዱን ያዘጋጅላችኋል።”—1 ቆሮንቶስ 10:13

በእርግጥም የደረሰብን ፈተና ምንም ዓይነት “መልክ” ቢኖረው የአምላክ ጸጋ እንድንቋቋመው ያስችለናል። (ያዕቆብ 1:17) የይሖዋ አገልጋዮች የሚደርሱባቸው ፈተናዎችና አስቸጋሪ ሁኔታዎች የተለያዩ ቢሆኑም አምላክ በወቅቱ የሚሰጣቸው አስፈላጊ የሆነ እርዳታ “ብዙ ገጽታ ያለው የእግዚአብሔር ጥበብ” አንዱ መግለጫ ነው። (ኤፌሶን 3:10) በዚህ አባባል አትስማማም?

[በገጽ 31 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

ይሖዋ ፈተናዎችን እንድንቋቋም ይረዳናል