የአንባቢያን ጥያቄዎች
የአንባቢያን ጥያቄዎች
ዘዳግም 14:21 “የሞተውን ሁሉ አትብላ” ይላል። ይህ ጥቅስ “ማንም ሰው ከበድኑ ቢበላ ልብሱን ይጠብ፤ ሆኖም እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ነው” ከሚለው ከዘሌዋውያን 11:40 ጋር ይጋጫል?
እነዚህ ሁለት ጥቅሶች አይጋጩም። በመጀመሪያው ጥቅስ ላይ፣ አውሬ ዘንጥሎት የሞተን እንስሳ ሥጋ መብላት የሚከለክለው ሕግ በድጋሚ ተገልጿል። (ዘፀአት 22:31፤ ዘሌዋውያን 22:8) በሁለተኛው ጥቅስ ላይ ደግሞ አንድ እስራኤላዊ በሆነ አጋጣሚ ይህን ሕግ ቢጥስ ማድረግ የሚችለው ነገር ሰፍሯል።
አንድ ነገር በሕጉ መከልከሉ አልፎ አልፎ ሊጣስ አይችልም ማለት እንዳልሆነ እሙን ነው። ለምሳሌ ያህል መስረቅን፣ መግደልን፣ በሐሰት መመስከርንና የመሳሰሉትን ድርጊቶች የሚከለክሉ ሕጎች ነበሩ። ከዚሁ ጎን ለጎን ደግሞ እነዚህን መለኮታዊ ሕጎች መጣስ ቅጣት ያስከትል ነበር። እንዲህ ያሉት ቅጣቶች ሕጎቹን የሚያጠናክሩ ከመሆናቸውም በላይ ምን ያህል ከባድ እንደሆኑ አስገንዝበዋል።
ሞቶ የተገኘን እንስሳ ሥጋ መብላት የሚከለክለውን ሕግ የጣሰ ሰው በይሖዋ ዓይን ርኩስ ይሆን ስለነበር ተገቢውን የመንጻት ሥርዓት መፈጸም ነበረበት። ይህን ሥርዓት በሚገባ ሳይፈጽም ቢቀር ግን “ኀጢአት ሠርቶአልና ይጠየቅበታል።”—ዘሌዋውያን 17:15, 16