በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ኢየሱስ አምላክ ነው ወይስ ሰው?

ኢየሱስ አምላክ ነው ወይስ ሰው?

ኢየሱስ አምላክ ነው ወይስ ሰው?

“እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ፤ የሚከተለኝም የሕይወት ብርሃን ይሆንለታል እንጂ ከቶ በጨለማ አይመላለስም።” (ዮሐንስ 8:12) እነዚህን ቃላት የተናገረው ኢየሱስ ክርስቶስ ነበር። በአንደኛው መቶ ዘመን ይኖር የነበረ አንድ የተማረ ሰው ስለ ኢየሱስ እንዲህ ሲል ጽፏል:- “የተሰወረ የጥበብና የዕውቀት ሀብት ሁሉ የሚገኘው በእርሱ ዘንድ ነው።” (ቈላስይስ 2:3) በተጨማሪም መጽሐፍ ቅዱስ “እውነተኛ አምላክ የሆንኸውን አንተንና የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ሕይወት ናት” ይላል። (ዮሐንስ 17:3) መንፈሳዊ ፍላጎታችንን ለማርካት ስለ ኢየሱስ ትክክለኛ እውቀት ማግኘት ያስፈልገናል።

በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ሰዎች ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ሰምተው ያውቃሉ። ኢየሱስ በሰው ልጆች ታሪክ ላይ ተጽዕኖ ያሳደረ መሆኑ ፈጽሞ የማያጠያይቅ ነው። እንዲያውም፣ በበርካታ የዓለም ክፍሎች የሚሠራበት የቀን መቁጠሪያ ኢየሱስ ተወልዶበታል ተብሎ የሚታሰበውን ዓመት መሠረት በማድረግ የተዘጋጀ ነው። ዘ ዎርልድ ቡክ ኢንሳይክሎፒዲያ እንደሚገልጸው “አብዛኞቹ ሰዎች [ኢየሱስ ከመወለዱ] በፊት የነበረውን ጊዜ ከክርስቶስ ልደት በፊት ብለው ሲጠሩት ከዚያ በኋላ ያለውን ደግሞ አኖ ዶሚኒ (በጌታችን ዓመት) በማለት ይጠሩታል።”

ሆኖም የኢየሱስን ማንነት በተመለከተ በርካታ የሚቃረኑ ሐሳቦች አሉ። አንዳንዶች በታሪክ ውስጥ የማይረሳ ሥራ አከናውኖ ያለፈ ታላቅ ሰው ብቻ እንደሆነ ይሰማቸዋል። ሌሎች ደግሞ ሁሉን ቻይ አምላክ ነው በማለት ያመልኩታል። በሌላም በኩል አንዳንድ የሂንዱ እምነት ተከታዮች ኢየሱስ ክርስቶስን ክሪሽና ከተባለው ሥጋ ለብሶ እንደመጣ ከሚነገርለት የሂንዱ አምላክ ጋር ያመሳስሉታል። ታዲያ ኢየሱስ ተራ ሰው ነበር ወይስ ሊመለክ የሚገባው አካል? ኢየሱስ በትክክል ማን ነበር? የመጣውስ ከየት ነው? ምን ዓይነት ባሕርያት ነበሩት? አሁን ያለው የት ነው? የሚቀጥለው ርዕስ እንደሚያሳየው ስለ ኢየሱስ በርካታ ሐሳቦች ከያዘው መጽሐፍ ለእነዚህ ጥያቄዎች ትክክለኛ መልስ እናገኛለን።