በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

“አንዳንዶቹ በመርከብ ወደ ባሕር ወረዱ”

“አንዳንዶቹ በመርከብ ወደ ባሕር ወረዱ”

“አንዳንዶቹ በመርከብ ወደ ባሕር ወረዱ”

በማሳቹሴትስ፣ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በሚገኘው በግላስተር ወደብ ፊት ለፊት፣ በማዕበል በሚናወጥ ባሕር ላይ መርከብ እየነዳ ያለን ሰው የሚያሳይ ከነሐስ የተሠራ የመታሰቢያ ሐውልት ቆሟል። ሐውልቱ በባሕር ሕይወታቸው ላለፈ በሺህ ለሚቆጠሩ የግላስተር ዓሣ አስጋሪዎች መታሰቢያነት የቆመ ነው። በሐውልቱ ግርጌና በአቅራቢያው በሚገኝ የመታሰቢያ ድንጋይ ላይ “አንዳንዶቹ በመርከብ ወደ ባሕር ወረዱ፤ በታላቅም ውሃ ላይ ሥራቸውን አከናወኑ፤ የእግዚአብሔርን ሥራ በዚያ አዩ፤ ድንቅ አድራጎቱንም በጥልቁ ውስጥ ተመ[ለ]ከቱ” የሚለው የመዝሙር 107:23, 24 ሐሳብ ሰፍሮ ይገኛል።

በአትላንቲክ ውቅያኖስ ላይ የዓሣ ክምችት ባለባቸው የማስገሪያ ቦታዎች አካባቢ መሥራት አደገኛ ነው። ባለፉት ዓመታት በባሕር ላይ ዓሣ ሲያሰግሩ 5,368 የሚያክሉ ወንዶች ሕይወታቸውን ያጡ ሲሆን ዛሬ በግላስተር ካለው ወደ 30,000 ገደማ ከሚደርስ የሕዝብ ብዛት አንፃር ሲታይ ቁጥሩ ብዙ ነው። በመታሰቢያው ድንጋይ ላይ ያለው ጽሑፍ እንዲህ ይላል:- “አንዳንዶች ከሰሜን ምስራቅ በተነሳ አውሎ ነፋስና በኃይለኛ ማዕበል ተዋጡ። ሌሎቹ ደግሞ በትንሽ ጀልባ ሆነው ከባሕሩ ዳር ይዛቸው ከመጣችው አነስተኛ መርከብ ርቀው ስለነበር እጣ ፈንታቸው በዚያው መቅረት ሆነ። አንዳንድ መርከቦች በማዕበል ተመትተው ሰመጡ። ሌሎች ደግሞ በትላልቅ መርከቦች ተገጩ።”

ይህ የመታሰቢያ ሐውልት ዓሣ አስጋሪዎች ለዘመናት ተቋቁመው ያሳለፉትን አድካሚና አደገኛ ሥራ ያስታውሳል። ባሎቻቸውን፣ አባቶቻቸውን፣ ወንድሞቻቸውንና ልጆቻቸውን በማጣታቸው በሐዘን ተደቁሰው እንባቸውን ያፈሰሱትን እስቲ አስብ። ይሁን እንጂ ይሖዋ አምላክ መበለቶችን፣ ወላጅ አልባ ልጆችን ወይም በባሕር ላይ ሕይወታቸውን ያጡትን አይረሳም። ሐዋርያው ዮሐንስ የወደፊቱን ጊዜ አስመልክቶ “ባሕርም በውስጡ የነበሩትን ሙታን ሰጠ፤ ሞትና ሲኦልም በእነርሱ ውስጥ የነበሩትን ሙታን ሰጡ” በማለት ተናግሯል። (ራእይ 20:13) እነዚያ ‘በመርከብ ወደ ባሕር የወረዱት’ ትንሣኤ በሚያገኙበት ወቅት በእርግጥም ድንቅ የሆነውን “የእግዚአብሔርን ሥራ” ያያሉ።