በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መስማት ለተሳናቸው ወንጌልን ይሰብካሉ

መስማት ለተሳናቸው ወንጌልን ይሰብካሉ

መስማት ለተሳናቸው ወንጌልን ይሰብካሉ

“መንፈሳዊ ሰው አድርገዋችኋል!” በማድሪድ፣ ስፔን ናቫልካርኔሮ ውስጥ የሚገኝ አንድ የአረጋውያን እንክብካቤ ማዕከል ዳይሬክተር ወደዚያ የሚመጡ የይሖዋ ምሥክሮችን አስመልክተው በቅርቡ ይህን ተናግረው ነበር። እንዲህ እንዲሉ ያነሳሳቸው ምንድን ነው?

በሮሳስ ዴል ካሚኖ ማዕከል ያሉ ብዙ ነዋሪዎች መስማት የተሳናቸው ናቸው። ይሁን እንጂ የይሖዋ ምሥክሮቹ ተጣጥረው የስፓንኛን የምልክት ቋንቋ ስለተማሩ ከእነዚህ ነዋሪዎች ጋር መግባባት ችለዋል። ዳይሬክተሩ የይሖዋ ምሥክሮች የተለየ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች መንፈሳዊ ትምህርቶችን ያለ ክፍያ ለማስተማር ጊዜያቸውን መሥዋዕት በማድረጋቸው አድንቀዋቸዋል። እኚህ ሰው የመንግሥቱ ወንጌል በነዋሪዎቹ ላይ በጎ ተጽዕኖ ማሳደሩን አስተውለዋል። ነዋሪዎቹም ቢሆኑ በተለይ ደግሞ የማየት ወይም የመስማት ችግር ያለባቸው ሰዎች የይሖዋ ምሥክሮች እየመጡ ለሚሰጧቸው ትምህርት ከፍተኛ አድናቆት አላቸው።

ማየትም ሆነ መስማት የተሳናቸው ዩሎሂኦ የተባሉ አንድ ነዋሪ በአሁኑ ጊዜ ከይሖዋ ምሥክሮች ጋር መጽሐፍ ቅዱስን እያጠኑ ነው። አንድ ቀን እያጠኑ ሳለ አንድ አዛውንት መጡና ነዋሪዎቹ አድናቆታቸውን ለመግለጽ የጻፉትን ግጥም ለይሖዋ ምሥክሩ ሰጡት። የግጥሙም ርዕስ “የይሖዋ ምሥክር መሆን” የሚል ነበር። በከፊል እንዲህ ይላል:- “ጥሩና ሥርዓታማ ሕይወት ይመራሉ፣ አስደሳች ጥበብም ከይሖዋ ያገኛሉ፣ በእርሱ ስለሚታመኑም ሳይታክቱ ወደ ሰዎች ቤት ይሄዳሉ።”

በመላው ዓለም የሚገኙ ብዙ የይሖዋ ምሥክሮች በአገራቸው የሚገኙ መስማት የተሳናቸው ሰዎች የሚግባቡበትን የምልክት ቋንቋ ለመማር ያነሳሳቸው በይሖዋ ላይ ያላቸው ይኸው እምነት ነው። በዚህ መንገድ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኘውን የሚያበረታታ የተስፋ መልእክት እንዲህ ላሉ ሰዎች ያካፍላሉ።