በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

“በጣም ከተደሰትኩባቸው ቀናት አንዱ”

“በጣም ከተደሰትኩባቸው ቀናት አንዱ”

“በጣም ከተደሰትኩባቸው ቀናት አንዱ”

በአውስትራሊያ የሚገኝ ቢዮንድብሉ የተባለ መንግሥታዊ ድርጅት “ጭንቀት በወጣቶች ዘንድ በጣም እየተለመደ የመጣና ምናልባትም በጣም አሳሳቢ የሆነ የአእምሮ ችግር ነው” ብሏል። ጥናቶች እንደሚያሳዩት በየዓመቱ 100,000 የሚያህሉ አውስትራሊያውያን ወጣቶች በጭንቀት ይሠቃያሉ።

ወጣት ክርስቲያኖችም ጭንቀት ሊይዛቸው ይችላል። ይሁን እንጂ ብዙዎቹ በይሖዋ ላይ እምነት ማሳደራቸው አፍራሽ አስተሳሰቦችን እንዲያሸንፉም ሆነ በወጣትነት ጊዜያቸው ስኬት እንዲያገኙ ረድቷቸዋል። ይህንንም በማድረጋቸው በሌሎች ዘንድ አድናቆት ለማትረፍ ችለዋል። እንዴት?

የ18 ዓመቷን ወጣት የክሌርን ተሞክሮ ተመልከት። ክሌርና እናቷ በሜልቦርን የሚገኝ አንድ የይሖዋ ምሥክሮች ጉባኤ አባላት ናቸው። ክሌር አባቷ ቤተሰቡን ጥሎ በመሄዱ በጣም ተጨንቃ ነበር። ይሁን እንጂ በሰማይ ባለው አባቷ፣ በይሖዋ ላይ ያላት ጠንካራ እምነት አልቀነሰም። አንድ ቀን ሊዲያ የተባለችው የቤተሰቡ ዶክተር ታምማ የነበረችውን የክሌርን እናት ለመመርመር ቤታቸው መጣች። ሊዲያ ጨርሳ ልትወጣ ስትል ክሌርን በመኪናዋ ወደ ገበያ አዳራሽ ልታደርሳት እንደምትችል ነገረቻት። በጉዞ ላይ ሳሉ ሊዲያ የወንድ ጓደኛ ያላት መሆን አለመሆኑን ክሌርን ጠየቀቻት። ክሌርም የይሖዋ ምሥክር በመሆኗ ያለአንዳች ዓላማ ከወንዶች ጋር ተቀጣጥራ እንደማትጫወት ነገረቻት። ዶክተሯ በሁኔታው ተደነቀች። ክሌር በሕይወቷ ውስጥ ጥበብ የሞላበት ውሳኔ ለማድረግ መጽሐፍ ቅዱስ እንዴት እንደረዳት ገለጸችላት። በመጨረሻም በጣም የጠቀማትን በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረተ አንድ መጽሐፍ ልታመጣላት እንደምትችል ነገረቻት። መጽሐፉም ወጣቶች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎችና ተግባራዊ መሆን የሚችሉ መልሶች የሚል ነው።

ሊዲያ መጽሐፉን ከወሰደች ከሦስት ቀናት በኋላ ለክሌር እናት ደውላ ባነበበችው ነገር መደሰቷን ነገረቻት። እንዲሁም ለሥራ ባልደረቦቿ ሌላ ስድስት ቅጂ ጠየቀች። ክሌር መጽሐፉን ስታደርስላት ዶክተሯ በእምነቷ ምን ያህል እንደተደነቀች ነገረቻት። ክሌር መጽሐፍ ቅዱስ አብረው እንዲያጠኑ ጋበዘቻት፤ እርሷም በሐሳቡ ተስማማች።

ክሌር በዶክተሯ የምሳ ሰዓት ላይ እየሄደች ለበርካታ ወራት አስጠንታታለች። ሊዲያ በወጣቶች ላይ የሚያጋጥመውን ጭንቀት አስመልክቶ በሚካሄድ አንድ ሴሚናር ላይ ንግግር ማቅረብ ትችል እንደሆነ ክሌርን ጠየቀቻት። ክሌር ሁኔታው ቢያስፈራትም ንግግሩን ለማቅረብ ተስማማች። ከ60 በላይ የሚሆኑ ሰዎች በሴሚናሩ ላይ ተገኝተው ነበር። በቅድሚያ የአእምሮ ጤና ባለሙያ የሆኑ አራት ሰዎች በተከታታይ ንግግር አቀረቡ። ከዚያም ክሌር የምትናገርበት ተራ ደረሰ። ወጣቶች ከአምላክ ጋር ዝምድና መፍጠራቸው ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ ጎላ አድርጋ ተናገረች። ይሖዋ አምላክ ለወጣቶች በጥልቅ እንደሚያስብና ድጋፍና መጽናኛ ፈልገው ወደ እርሱ ለሚዞሩ ሁሉ እርዳታ እንደሚሰጥ አብራራች። በተጨማሪም ይሖዋ ማንኛውንም ዓይነት አካላዊና አእምሯዊ ሕመም በቅርቡ እንደሚያስወግድ ያላትን እምነት ገለጸች። (ኢሳይያስ 33:24) ከዚህ ግሩም ምሥክርነት የተገኘው ውጤት ምንድን ነው?

ክሌር እንዲህ በማለት ተናግራለች:- “ከስብሰባው በኋላ ብዙዎቹ ወደ እኔ እየመጡ ከወጣት አንደበት ስለ አምላክ በመስማታቸው እንደተደነቁ ይነግሩኝ ጀመር። ወጣቶች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎች የተባለውን መጽሐፍ 23 ቅጂ አበረከትኩ። ከተሰበሰቡት ውስጥ ሦስት ወጣቶች የስልክ ቁጥራቸውን ሰጥተውኛል። ከእነዚህም ውስጥ አንዷ በአሁኑ ወቅት መጽሐፍ ቅዱስን በማጥናት ላይ ትገኛለች። በሕይወቴ በጣም ከተደሰትኩባቸው ቀናት አንዱ ነበር።”