በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ዲያብሎስ በእርግጥ አለ?

ዲያብሎስ በእርግጥ አለ?

ዲያብሎስ በእርግጥ አለ?

ስለ ዲያብሎስ ምን አመለካከት አለህ? ዲያብሎስ የሰው ልጆች መጥፎ ነገሮችን እንዲያደርጉ የሚፈትን እውን አካል ነው ወይስ አንድ ዓይነት የክፋት ባሕርይ? ዲያብሎስ ሊፈራ የሚገባው ፍጡር ነው ወይስ ከአጉል እምነት ወይም ከአፈ ታሪክ የመነጨ ሐሳብ እንደሆነ በማሰብ ችላ ሊባል የሚገባው አካል? “ዲያብሎስ” የሚለው ቃል በአጽናፈ ዓለም ውስጥ የሚገኝን ሕልውና የሌለው አጥፊ የሆነ ኃይል የሚያመለክት ነው? በርካታ ዘመናዊ የሃይማኖት ምሑራን እንደሚሉት ቃሉ በሰዎች ውስጥ የሚያድር የክፋት ባሕርይን የሚያመለክት ነው?

የዲያብሎስን ማንነት በተመለከተ ሰዎች የተለያየ አመለካከት መያዛቸው የሚያስደንቅ አይደለም። ራሱን በመደበቅ ረገድ ጥሩ ችሎታ ያለውን ሰው እውነተኛ ማንነት ማወቅ ምን ያህል አስቸጋሪ እንደሚሆን መገመት አያዳግትም! በተለይ ደግሞ ግለሰቡ እውነተኛ ማንነቱን ደብቆ ለመኖር ከቆረጠ ሁኔታው ይበልጥ አስቸጋሪ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ ዲያብሎስን የሚገልጸው በዚህ መንገድ ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ዲያብሎስ ሰይጣን ተብሎም የሚጠራ ሲሆን ስለ እርሱም “ሰይጣን ራሱ የብርሃን መልአክ ለመምሰል ራሱን ይለዋውጣል” በማለት ይናገራል። (2 ቆሮንቶስ 11:14) ዲያብሎስ ክፉ ቢሆንም ጥሩ እንደሆነ አድርጎ ራሱን በማቅረብ ሌሎችን ያታልላል። ሰዎች ዲያብሎስ የለም ብለው እንዲያምኑ ማድረግ ከቻለ ደግሞ ዓላማውን ለማሳካት ይበልጥ ተስማሚ ይሆንለታል።

ታዲያ ዲያብሎስ ማን ነው? ወደ ሕልውና የመጣውስ መቼ እና እንዴት ነው? በዛሬው ጊዜ በሰዎች ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድረው እንዴት ነው? ይህንን ተጽዕኖ ለመቋቋም ልናደርገው የምንችለው ነገር ይኖር ይሆን? መጽሐፍ ቅዱስ ከመጀመሪያው አንስቶ የዲያብሎስን እውነተኛ ታሪክ የሚናገር ከመሆኑም ሌላ ከላይ ላሉት ጥያቄዎች ትክክለኛ መልስ ይሰጣል።

[በገጽ 3 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

ራሱን ደብቆ ለመኖር የቆረጠን ሰው እውነተኛ ማንነት ማወቅ ምን ያህል አስቸጋሪ እንደሚሆን መገመት አያዳግትም!