በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የበዓል ሰሞን—እንደምትጠብቀው ሆኖ ታገኘው ይሆን?

የበዓል ሰሞን—እንደምትጠብቀው ሆኖ ታገኘው ይሆን?

የበዓል ሰሞን—እንደምትጠብቀው ሆኖ ታገኘው ይሆን?

“[ታላቁ] ጴጥሮስ በሁሉም አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ ጥር 1 ቀን፣ ለየት ያለ የዘመን መለወጫ በዓል የአምልኮ ሥርዓት እንዲካሄድ ትእዛዝ አወጣ። ከዚህም በላይ ሰዎች የቤታቸውን በር መቃን ቅጠላቸው በማይረግፍ ዛፎች ቅርንጫፍ [ኤቨር ግሪን ትሪ] እንዲያስውቡና የሞስኮ ነዋሪዎች ሁሉ ‘ደስታቸውን ለመግለጽ ድምጻቸውን ከፍ አድርገው እንኳን ለአዲስ ዓመት አደረሰህ’ እንዲባባሉ አዘዘ።”—ፒተር ዘ ግሬት—ሂስ ላይፍ ኤንድ ወርልድ

በብዙ የዓለም ክፍሎች ገና እና የዘመን መለወጫ በዓል የሚከበሩት በአንድ ሰሞን ነው። ስለዚህም ይህ ጊዜ ረዘም ያለ የበዓል ወቅት ነው። በዓለም ዙሪያ የሚኖሩ ሰዎች ይህ ወቅት በገና በዓል ማለትም በተለምዶ ኢየሱስ ተወልዶበታል ተብሎ በሚታሰብበት ቀን ላይ ትኩረት ያደረገ እንደሆነ ይናገራሉ። ወላጆች ከሥራ ልጆች ደግሞ ከትምህርት ቤት የሚያርፉበት ወቅት በመሆኑ ቤተሰቡ አንድ ላይ ሆኖ ጥሩ ጊዜ የሚያሳልፍበት ምቹ አጋጣሚ ይመስል ይሆናል። ሌሎች ግን በዓመቱ ውስጥ በዚህ ጊዜ ክርስቶስን ለማክበር ስለሚፈልጉ ወቅቱ የኢየሱስ “የልደት በዓል” እንደሆነ ሲናገሩ ይደመጣሉ። ምናልባት አንተም የገና በዓል ዋነኛው ገጽታ ይኸው እንደሆነ ይሰማህ ይሆናል።

በዓለም ዙሪያ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ባሎች፣ ሚስቶችና ልጆች ክርስቶስን ለማወደስም ይሁን ከቤተሰብ ጋር ጥሩ ጊዜ ለማሳለፍ አሊያም ሁለቱን ምክንያት በማድረግ ይህን ወቅት በጉጉት ይጠብቁታል። በዚህ ዓመትስ? ቤተሰቦች እንደጠበቁት ልዩ ጊዜ ይሆንላቸው ይሆን? አምላክስ ይህን ጊዜ እንደ ልዩ ወቅት ይመለከተዋል? ቤተሰቡ አንድ ላይ ሆኖ የሚዝናናበት ፕሮግራም ካለው አንተ እንዳሰብከው የምትደሰትበት ጊዜ ይሆን ወይስ የጠበቅኸው ሳይሆን ቀርቶ የምታዝንበት?

ገናም ሆነ የዘመን መለወጫ በዓል ሃይማኖታዊ በሆነ መንገድ እንዲከበሩ የሚፈልጉ ሰዎች የእነዚህ በዓላት አከባበር ለኢየሱስ ክብር የሚያመጣ እንዳልሆነ ማስተዋል ችለዋል። ከዚህ በተለየ መልኩ የበዓል ሰሞን ለአንዳንዶች ስጦታ የሚለዋወጡበት፣ ለክርስቶስ ክብር የማያመጡ አንዳንድ ድግሶች የሚዘጋጁበት ወይም በዋነኝነት ቤተ ዘመድ አንድ ላይ የሚሆንበት አጋጣሚ ነው። አብዛኛውን ጊዜ በእነዚህ ዓይነት ግብዣዎች ላይ አንዱ አሊያም በርከት ያሉ የቤተሰቡ አባላት ከልክ በላይ ይበላሉ ወይም ይጠጣሉ፤ ይህም በቤተሰብ ውስጥ ጭቅጭቅና ጠብ እንዲፈጠር ምክንያት ይሆናል። ይህ ዓይነቱ ክስተት ወይ በራስህ አሊያም በሌላ ሰው ላይ ሲደርስ ተመልክተህ ሊሆን ይችላል።

ዛሬ ያለው ሁኔታ በመግቢያችን ላይ በተጠቀሰው የሩሲያ ዛር በሆነው በታላቁ ጴጥሮስ ዘመን ከነበረው ምንም ያልተለየ እንደሆነ ይሰማህ ይሆናል። በአሁኑ ጊዜ በሚያዩት ነገር የሚረበሹ ብዙ ሰዎች፣ የበዓላት ወቅት ስለ መንፈሳዊ ነገር የሚያስቡበት እንዲሁም ቤተሰቦች ጥሩ ጊዜ የሚያሳልፉበት እንዲሆን ይመኛሉ። እንዲያውም አንዳንዶች በዚህ ወቅት “በዓሉ የጌታ ነው” የሚል መርህ በማንገብ ጭምር ለውጥ ለማምጣት ይጥራሉ። ታዲያ ጥረታቸው ተሳክቶላቸዋል? በእርግጥ እንዲህ በማድረጋቸው ለክርስቶስ ክብር አምጥተዋል? በዓላቱን በተመለከተ የተለየ አመለካከት እንዲኖረን የሚያስችል ምክንያት ይኖራል?

ለእነዚህ ጥያቄዎች አጥጋቢ የሆነ መልስ ለማግኘት ጉዳዩን ለዚህ ወቅት ልዩ ግምት ከሚሰጡት ሰዎች አንጻር እንመልከተው።