በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የአዲስ ዓመት ዛፍ—የሩሲያ ልማድ ነው ወይስ የክርስትና?

የአዲስ ዓመት ዛፍ—የሩሲያ ልማድ ነው ወይስ የክርስትና?

የአዲስ ዓመት ዛፍ—የሩሲያ ልማድ ነው ወይስ የክርስትና?

“በ1830ዎቹ መጀመሪያ አካባቢ ቅጠላቸው የማይረግፍ ዛፎችን [ኤቨር ግሪን ትሪ] የመጠቀም ባሕል ‘ጀርመኖች ያመጡት ተወዳጅ ልማድ’ በመባል ይታወቅ ነበር። በዚያ አሥርተ ዓመት መገባደጃ አካባቢ ግን በሴይንት ፒተርስበርግ የሚኖሩ ታላላቅ ሰዎች ቤታቸውን [በእነዚህ ዛፎች] ማስጌጥን ‘ልማድ አደረጉት።’ . . . በ19ኛው ክፍለ ዘመን ይህን ልማድ ተከትለው ዛፉን በቤቶቻቸውና በጎጆዎቻቸው ላይ ያላደረጉት ቀሳውስቱና ገበሬዎች ብቻ ነበሩ። . . .

“[ከ19ኛው ክፍለ ዘመን] በፊት ይህ ዛፍ . . . ምንም ዓይነት ልዩ ክብር የሚሰጠው አልነበረም። በሩሲያውያን ባሕል መሠረት የሞት ምልክት ተደርጎ የሚታይ ከመሆኑም በተጨማሪ ‘ከሙታን ዓለም’ ጋር ተያያዥነት አለው ብለው ያምኑ ነበር፤ እንዲሁም በመጠጥ ቤቶች ጣሪያ ላይ ይቀመጥ ነበር። ሆኖም በ19ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ ላይ ከዚህ ፈጽሞ የተለየ የአመለካከት ለውጥ ተደረገ። . . .  ከሌሎች አገሮች የመጣውን [ቤታቸውን በዛፍ ቅጠሎች የማሳመር ልማድ] ሲቀበሉ ይህ ባሕል በምዕራቡ ዓለም ለገና ዛፍና ለገና በዓል ከሚሰጠው ትርጉም ጋር ተመሳሳይ እየሆነ እንደመጣ መረዳት ይቻላል። . . .

“በሩሲያ ይህ ዛፍ በክርስትና እምነት ውስጥ ተቀባይነት እንዲያገኝ ማድረግ ቀላል አልነበረም። ከኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ተቃውሞ ገጥሞታል። ቀሳውስቱ በዚህ አዲስ ክብረ በዓል ላይ የሚያዩት ነገር ‘አጋንንታዊ ተግባር፣’ የአረማውያን ልማድ እንዲሁም ከአዳኛችን ጋር ምንም ተዛማጅነት የሌለውና የምዕራቡ ዓለም ባሕል እንደሆነ ተሰምቷቸው ነበር።”—በሴይንት ፒተርስበርግ ዩኒቨርሲቲ፣ በቋንቋ ታሪክና እድገት ጥናት ዶክተር የሆኑት ፕሮፌሰር ዬሌና ዱሸንችኪና

[በገጽ 32 ላይ የሚገኝ የሥዕል ምንጭ]

ፎቶግራፍ:- Nikolai Rakhmanov