በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መጀመሪያ ቢቃወሟቸውም በኋላ ግን ተቀበሏቸው

መጀመሪያ ቢቃወሟቸውም በኋላ ግን ተቀበሏቸው

መጀመሪያ ቢቃወሟቸውም በኋላ ግን ተቀበሏቸው

ከተወሰኑ ዓመታት በፊት ሳንቲያጎ እና ባለቤቱ ሉርደስ የመጽሐፍ ቅዱስ መልእክት የያዘውን ተስፋ ለሰዎች ለማካፈል በፔሩ ወደምትገኘው ዌልካፓታ የምትባል ውብ ከተማ ተዛውረው ነበር። ሆኖም ብዙም ሳይቆዩ አንድ ቄስ ከኩስኮ ከተማ መጣና የዌልካፓታ ነዋሪዎችን ስብሰባ ጠራ። ከዚያም የይሖዋ ምሥክሮች በአካባቢው መኖራቸው ለቀሳፊ ወረርሽኝ እንደሚዳርጋቸው እንዲሁም ከባድ በረዶ ዘንቦ ከብቶቻቸውንና ሰብላቸውን እንደሚያጠፋባቸው ተናገረ።

ብዙዎቹ ይህን “ትንቢት” አምነው ስለነበር አንድ ዓመት ከመንፈቅ ለሚበልጥ ጊዜ አንድም የከተማው ነዋሪ ሳንቲያጎና ሉርደስ መጽሐፍ ቅዱስን ለማስጠናት ያቀረቡትን ግብዣ አልተቀበለም። እንዲያውም ሚጌል የተባለው የከተማው ምክትል አስተዳዳሪ በሳንቲያጎና በሉርደስ ላይ ድንጋይ እየወረወረ መንገድ ለመንገድ አሳዷቸው ነበር። እነርሱ ግን ምንጊዜም ሰላማዊ በመሆን ጥሩ ክርስቲያናዊ ባሕርይ ያሳዩ ነበር።

እያደር አንዳንድ የከተማው ነዋሪዎች መጽሐፍ ቅዱስ ለማጥናት ተስማሙ። ሌላው ቀርቶ ሚጌል እንኳ አመለካከቱ ተቀይሮ ነበር። ይህ ሰው ከሳንቲያጎ ጋር መጽሐፍ ቅዱስ ማጥናት የጀመረ ሲሆን ከልክ በላይ መጠጣቱን በማቆም ሰላማዊ ሰው ሆነ። በመጨረሻም ሚጌልና ባለቤቱ ከሁለት ልጆቻቸው ጋር የመጽሐፍ ቅዱስን እውነት ተቀበሉ።

በዛሬው ጊዜ በዚህች ከተማ ውስጥ ጥሩ እድገት የሚታይበት አንድ የይሖዋ ምሥክሮች ጉባኤ ይገኛል። ሚጌል የዚያን ጊዜ የወረወራቸው አብዛኞቹ ድንጋዮች ሳንቲያጎንና ሉርደስን ሳይመቷቸው በመቅረታቸው የተደሰተ ሲሆን ባልና ሚስቱ ሰላማዊ በመሆን ረገድ ላሳዩት ግሩም ምሳሌ አመስጋኝ ነው።

[በገጽ 32 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

ሳንቲያጎና ሉርደስ (ከላይ) ሰላማዊ በመሆናቸው የሚጌል (በስተ ቀኝ) አመለካከት ተቀይሯል