በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

“ወይን ጠጅ ቀለም ያለው ሦስት ማዕዘን ምልክት ምን ትርጉም አለው?”

“ወይን ጠጅ ቀለም ያለው ሦስት ማዕዘን ምልክት ምን ትርጉም አለው?”

“ወይን ጠጅ ቀለም ያለው ሦስት ማዕዘን ምልክት ምን ትርጉም አለው?”

በሴኡል፣ ኮሪያ ሪፑብሊክ ፍትሕ ሚኒስቴር ውስጥ የሚሠራ አንድ የመንግሥት ሠራተኛ እንዲህ ሲል ጽፏል:- “ከጥቂት ቀናት በፊት ከአንዲት የይሖዋ ምሥክር መጠበቂያ ግንብ ወስጄ ነበር። መጽሔቱን ሳነብ በናዚና በኮሚኒስት አገዛዝ ሥር የይሖዋ ምሥክሮች ስደት ደርሶባቸው እንደነበር ተረዳሁ። ሆኖም አንድ ጥያቄ አለኝ። የመጽሔቱ ሽፋን፣ የይሖዋ ምሥክሮች ኮታቸው ላይ በስተ ግራ በኩል የወይን ጠጅ ቀለም ያለው የተገለበጠ ሦስት ማዕዘን ምልክት እንዳደረጉ ያሳያል። ይህ የወይን ጠጅ ቀለም ያለው ሦስት ማዕዘን ምልክት ምን ትርጉም አለው?”

በጀርመን፣ በናዚ አገዛዝ ሥር የይሖዋ ምሥክሮች ሃይል ሂትለር (ሂትለር አዳኝ ነው) ለማለት ፈቃደኞች አልነበሩም፤ እንዲሁም ከማንኛውም ፖለቲካዊም ሆነ ወታደራዊ ጉዳይ ገለልተኛ ነበሩ። በዚህ ምክንያት ናዚዎች ጭካኔ በተሞላበት መልኩ አሳደዋቸዋል፤ 12, 000 የሚሆኑ የይሖዋ ምሥክሮችን ወደ እስር ቤትና የማጎሪያ ካምፖች በማጋዝ አንዳንዶቹን ለአጭር ሌሎቹን ደግሞ ረዘም ላለ ጊዜ እንዲታሰሩ አድርገዋል። ከእነዚህ መካከል በመቶዎች የሚቆጠሩት የተገደሉ ሲሆን በአጠቃላይ ወደ 2, 000 የሚጠጉ የይሖዋ ምሥክሮች ሕይወታቸውን አጥተዋል።

በእስር ቤት ልብሳቸው ላይ የነበረው የወይን ጠጅ ቀለም ያለው ሦስት ማዕዘን ምልክት ምን ትርጉም ነበረው? አናቶሚ ኦቭ ዘ ኤስ ኤስ ስቴት የተባለው መጽሐፍ እንዲህ በማለት ይገልጻል:- “[በናዚ] ካምፖች ውስጥ የሚገኙ እስረኞች በሙሉ ልብሳቸው ላይ መለያ ምልክት ይደረግላቸው ነበር። ከጦርነቱ በፊት የተጀመረው መለያ ምልክት የማድረግ ዘዴ በእያንዳንዱ እስረኛ ልብስ ላይ ሦስት ማዕዘን ቅርጽ ያለው ጨርቅ መስፋትን ይጨምር ነበር። የምልክቶቹ ቀለም እንደ እስረኞቹ ምድብ ይለያያል:- ለፖለቲካ እስረኞች ቀይ፣ ለይሖዋ ምሥክሮች ወይን ጠጅ፣ ጸረ-ኅብ​ረተሰብ አቋም ላላቸው ጥቁር፣ ለወን​ጀለኞች አረንጓዴ፣ ለግብረ ሰዶማውያን ሮዝ እንዲሁም ለስደተኞች ሰማያዊ ቀለም ያለው ሦስት ማዕዘን ምልክት ይሰፋላቸው ነበር። ለአይሁዳውያን እስረኞች ደግሞ፣ የዳዊትን ኮከብ ለመሥራት ሲባል ቢጫ ቀለም ያለው ሌላ ሦስት ማዕዘን ምልክት ተደርቦ ስለሚሰፋላቸው ባለ ስድስት ማዕዘን ምልክት ያለው አርማ ያደርጉ ነበር።”

ፕሮፌሰር ጆን ሮት ሆሎኮስት ፖለቲክስ በተባለው መጽ​ሐፋቸው ላይ እንዲህ በማለት ጽፈዋል:- “በሁሉም ቦታ የሚኖሩ ሰዎች ከወይን ጠጁ ምልክት የሚገኘውን ትምህርት በማስታወስ ትክክል የሆነውን ለማድረግ ቆርጠው ከተነሱ፣ ምልክቱ ወደፊት መጥፎ ድርጊት ከመፈጸም ጥበቃ ይሆነናል፤ ከዚህም በላይ የሰው ልጆች በሙሉ የላቀ አክብሮት ሊሰጡት የሚገባውን መልካም ምግባር እንድንከተል መመሪያ ሊሆነን ይችላል።” የይሖዋ ምሥክሮች ሽልማት ያስገኘውን የይሖዋ ምሥክሮች የናዚን ጥቃት በጽናት ተቋቁመዋል የሚለውን የቪዲዮ ፊልም አዘጋጅተዋል። አንድ የይሖዋ ምሥክር ይህን ፊልም እንዲያሳይህ ለምን አትጠይቀውም?